Get Mystery Box with random crypto!

#WolloUniversity እንሰትን የማላመድ ሙከራ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ድርቅን | 43 All University

#WolloUniversity

እንሰትን የማላመድ ሙከራ በወሎ ዩኒቨርሲቲ

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ድርቅን መቋቋም የሚችል የእንሰት ዝርያ ለማላመድ የሙከራ ምርምር ማካሄድ ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመተባበር የሙከራ ምርምሩን እያካሄደ ነው።

ለዚህም 6 የእንሰት ዝርያዎችን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በማምጣት በአራት ወረዳዎች የማላመድ ሥራ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

የእንሰት ዝርያዎቹ በደሴ ቲሹ ካልቸር ቤተ-ሙከራ በማሳደግ ከ3 እስከ 4 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ ይደረጋል ተብሏል።

የእንሰት ዝርያዎቹ የምግብ እጥረትን ከመቅረፍ ባለፈ ለመድኃኒት፣ ለእንሰሳት መኖ፣ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለቃጫ አገልግሎት እንደሚውሉ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ እና ተመራማሪ አያሌው ታለማ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch