Get Mystery Box with random crypto!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የሰርጥ አድራሻ: @memehirhenok
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 12.40K

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-03 17:31:49 ባለ ውለታዎቼን ጋሽ ማርቆስ /ማርክ ዙከርበርግ/ እና ስቲቭ፣ ቻድ፣ ጃውድን ጠይቅያቸው መጣሁ!

#_ባለውለታዎቼ_ፌስ_ቡክ_ዩትዩብና_ጎግል!

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ተወዳጆች ሆይ ከማህበራዊ ሚዲያ ተደራሽ፣ ቀላሉና ግንባር ቀደም ከሆኑት ውስጥ ፌስ ቡክና ዩትዮብ ዋነኞቹ ናቸው። ፌስ ቡክን የመሠረተው ማርክ ዙከንበርግ ነው። ዮትዮብን የመሠረቱት ስቲቭ፣ ቻድ እና ጃውጅ ናቸው። እነሱ ደግሞ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለማህበራዊ ተጠቃሚ በሙሉ ባለውለታዎች ናቸው። በለተይ እኔን በግሌ ከምዕመናኑ አስተዋውቀውኛል። ትምህርቶቼን፣ አገልግሎቴን በቀላሉ በተለያዩ ዓለማት ላሉት አዳርሰውልኛል አሁንም እያዳረሱልኝ ነው።

እኔም ውለታቸውን ለማስታወስ በሳንፍራንሲስኮ የሚገኘውን ዋናውን መሥሪያ ቤታቸውን ሄጄ አየሁት። የከበረ ሰላምታዬን አቅርቤ ምስጋናዬን አድርሼ በርቱ ተበራቱ አልኳቸው። ፌስ ቡክ የቀድሞ ሎጎውን ሜታ ብሎ እንደቀየረ ታውቃላችሁ። መሥሪያ ቤቱ ከምነግራችሁ በላይ እጅግ በጣም ሰፊ ነው። ዋና መሥሪያ ቤቱ አሥር ሺ ሠራተኖች አሉት አለኝ ገረመኝ!

በተለይ ዩትዩብ ስሜን ጠይቆኝ፣ በስሜ የምጠቀመውንም ቻናል አሳይቼ በሌላ ጊዜ ስመጣ ከሠራተኞቹ ጋር እንደሚያስተዋውቀኝና አንዳንድ ነገር እንደሚያሳየኝ ቃል ገብቶልኝ፣ ስሜን መዝግቦልኝ በክብር ሸኝቶኛል። መረጃ የሚጎለጉለውን ጎግልንም አይቼው እግረ መንገዴን አመስግኛለሁ።

/ፌስ ቡክ ከሳንፍራንሲስኮ ትንሻ ወጣ ይላል፣ ጎግልና ዩትዩብ እዛው ከተማ ውስጥ ነው ያሉት/

መጋቢት 25-7-2015 ዓ.ም

ካሊፎርኒያ አሜሪካ!
866 views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 19:26:31
1.0K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 19:26:01 #_በካሊፎርኒያ_የነበረኝ_የንስሐ_አገልግሎት!

"ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር" /ማቴ 3፥6/

ተወዳጆች ሆይ በዚህ አገልግሎት እጅጉን ከምደሰትበት አንዱ የንስሐ እና የቄደር ጥምቀት አገልግሎት ነው። የመጥምቀ መለኮት ጥምቀት ሥጋዊ ፈውስ ወይም ሥጋዊ ድህነት ላይ ብቻ ያተኮረ አልነበረም። የነፍስ ፈውስ ላይም ያተኮረ ነበር።

ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ይመጣሉ ተጠምቀው ብቻ ሳይሆን ንስሐ ገብተውም ነው የሚመለሱት። ለዚህም ነው "ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር" ተብሎ የተጻፈው። /ማቴ 3፥6/

የጥምቀት አገልግሎት ከንስሐ ጋር ሲሆን ለተጠማቂው ሁለት ድህነት ይሰጠዋል። ንስሐ ገብቶ የሚጠመቅ ሰው በመጀመሪያ በነፍሱ ይድናል ወይም ከኃጢአት በሽታ ይፈወሳል። ሁለተኛው ከያዘው ደዌና ክፉ መንፈስ ይፈወሳል። አንዳንዴ ንስሐ ሳንገባ ጸበል ስለምንጠመቅ ድህነት ሊዘገይብን ይችላል። ስለዚህ የትኛውም ጸበል ስንጠመቅ በመጀመሪያ ንስሐ እንግባ በነፍሳችንም እንዳን። ነፍስ ከዳነች ሥጋ ቀላል ነው። ምክንያቱም የነፍስ ድህነት የሥጋን ድህነት ያስከትላልና።

የሚያሳዝነው ብዙዎች ንስሐ ለመግባት ይፈራሉ ይጨነቃሉ። "ኃጢአቴን እንዴት እናዘዛለሁ? ከየት ጀምሬ ነው የምናገረው? ይህን ሁሉ ኃጢአት እንዴት ልናዘዝ? የሚረዳኝ ካህን ይኖር ይሁን? ወዘተ" ጥያቄዎች ያስጨንቋቸዋል።

በዚህ ሰራሁት የምንለው ኃጢአት ያስጨንቀናል በወዲያ ንስሐ እንዳንገባ መናጢው ያስፈራራናል፣ እግዚአብሔር የይቅርታ አባት መሆኑን ያስረሳናል። ብቻ ንስሐ ለመግባት ጭንቅ ነው። ታዲያ የሰይጣንን ፈተና አልፈው፣ ንስሐ ለመግባት ወስነው መጥተው ንስሐ ሲገቡ፣ ሸክማቸው ሲቀል፣ የነፍስ ነፃነት፣ የኃጢአት ስርየት አግኝተው ሲሄዱ ከማየት የበለጠ ምንም ደስታ የለም።

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ የሆነውም እንደ ወይን አምባ ነው። የንስሐ እና የቄደሩን ጥምቀት ጥሪ ተመልክተው ብዙዎች መጥተው ንስሐ ገብተው ቄደር ተጠምቀው ነበር። በጣም የገረመኝን ልንገራችሁ። መደበኛውንና የቄደሩን ጥምቀት አጥምቄ፣ ቅብዓ ቅዱስ ቀብቼ ስንብት ላይ ሰንብቼ ሰዓት አልበቃ ብሎኝ ነበር። ነገር ግን ንስሐ የሚገቡት ሰዓት ቢሄድም ንስሐ ሳንገባ አንሄድም ብለው እስከ ምሽቱ 12፥30 ንስሐ ስሰጥ ነበር።

ምዕመናኑ ተራውን ጠብቆ ታግሶ ንስሐ ለመግባት ያሳዩኝ ትዕግስት ድንቅ ነበር። ደፈር ያለው ፊት ለፊት ይናገራል፣ ፈራው ደግሞ ኃጢአቷን በወረቅ ጽፋ ለቅዱስ ኤፍሬምና ለቅዱስ ባስልዮስ እንደሰጠቻቸው ደግ ሴት በወረቀት ጽፈው ይሰጡኝ ነበር።

ወዳጆቼ ምዕመናኑ ተይዟል መተንፈሻም አጥቷል ንስሐ የሚገቡበትን መርሃ ግብር ብናዘጋጅ፣ በሳምንት አንዱን ቀን ለንስሐ ብናውጅ ኃጢአቱ ያስጨነቀው፣ ያ መናጢ ግራ ያጋባው ሰው በሙሉ ልብ ቀን ቆርጦ ወስኖ ንስሐ ይገባል። በቤተ ክርስቲያን ንስሐ ግቡ ብለን ብቻ ማስተማር ሳይሆን ምዕመናኑ ንስሐ የሚገቡበትን አንድ ቀን ለእነሱ ብንሰጣቸው፣ ቀኑንም ተዘጋጅተን ብናዘጋጃቸው ንስሐ ይገባሉ። ሁላችንንም ለእውነተኛ ንስሐ ያብቃን!

መጋቢት 23-7-2015 ዓ.ም

ካሊፎርኒያ አሜሪካ!
1.1K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 00:24:46

805 views21:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 19:05:29
1.0K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 19:05:28
1.0K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 19:04:33 በአሜሪካ ካሊፎርኒያ አገልግሎቱ_በፎቶ_ይህን_ይመስላል!

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ተወዳጆች ሆይ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ በሳክራሚንቶ በቅዱስ ሚካኤል ወቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የነገረኝ አገልግሎት እጅግ በጣም መልካም ነው። ሰው ከሕመሙ ሲድን፣ ከክፉ መናፍስት ሲላቀቅ፣ ንስሐ ገብቶ፣ ከኃጢአት ጸድቶ ሲደሰት፣ የነፍስ ነፃነት ሲያገኝ ከዚህ የበለጠ ምን ደስታ አለ? የምቆይ የመሰላችሁ ብዙ ሰዎች አላችሁ። የፊታችን እሑድ የመጨረሻውን አገልግሎት ሰጥቼ የማበቃበት ነው።

ካሊፎርኒያ አሜሪካ!

Mar 29-2023
1.0K viewsedited  16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 10:16:42

1.5K views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 19:52:21
1.7K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 19:52:16 #_Apr_2_እሑድ_የመጨረሻው_ቀን_አገልግሎት_ነው!

ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ!

ተወዳጆች ሆይ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ በሳክራሚንቶ በደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ወቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከ March 10 ጀምሮ የትምህርት፣ የጥምቀት እና የቅብዓ ቅዱስ አገልግሎት እየሰጠሁ ቆይቻለሁ። የፊታችን እሑድ Apr 2 የመጨረሻው የአገልግሎት ቀን ነው። ስለዚህ እሑድ Apr 2 የመጨረሻውን አገልግሎት ሰጥቼ የማጠናቅቅበት ቀን ስለሆነ መጥታችሁ አገልግሎቱን ማግኘት ትችላላችሁ።

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም!
1.7K viewsedited  16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ