Get Mystery Box with random crypto!

ቅኝት በኳስ ሜዳ | Kegnit be Kuas Meda

የቴሌግራም ቻናል አርማ kegnitbekuasmeda — ቅኝት በኳስ ሜዳ | Kegnit be Kuas Meda
የቴሌግራም ቻናል አርማ kegnitbekuasmeda — ቅኝት በኳስ ሜዳ | Kegnit be Kuas Meda
የሰርጥ አድራሻ: @kegnitbekuasmeda
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.72K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በአፍሩ ፊልም ፕሮሞሽንና ኢንተርቴይመንት ተዘጋጅቶ በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች በቀጥታ የሚቀርቡበት ቻናል ነው።

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-11 09:19:54
2.1 አሴሜትሪካል 4 1 4 1 አርቴታ የተወሰኑ የተጨዋቾች ቦታ በመለወጥ ለመከላከል።በዚህም ዚንቼኮ ሄንደርሰንን እንዲቆጣጠር ማግሀሌሽ ሳላህ ማርቲኔሊ ኮናቴን ዣካ አርኖርድን እንዲይዙ በማድረግ እንደ ሁኔታው በሚቀያየር ቅርፅ ለመከላከል ።
608 views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 09:19:53
2 አርሰናል አሴሜትሪካል 3 2 4 1 ቅርፅ መነሻ የሊቨርፑል ተጨዋቾች ሰው ለ ሰው በመያዝ ለመከላከል ።
618 views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 17:43:34 “…ከራሴም፣ ከቀጣሪዎቼም፣ ከነፍሴም ጋር ተነጋግሬ ቆይታዬን ወደፊት የምመልሰው ይሆናል” ውበቱ አባተ

አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከጊኒው ጨዋታው መልስ በሀገር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታውን ወደ ሞሮኮ በማምራት ከጊኒ አቻው ጋር አድርጎ ያለምንም ነጥብ መመለሱ ይታወቃል። ቡድኑ ባሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰ ከቀናት በኋላ ደግሞ የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ለብዙሃን መገናኛ አባላት መግለጫ ሰጥተዋል።

አሠልጣኙ በቅድሚያ “የምድብ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታችንን ከጊኒ ብሔራዊ ቡድን ጋር አድርገን ተመልሰናል። ወደ ቦታው ስንሄድ በውድድሩ ላይ የሚያቆየንን ውጤት ለማስመዝገብ ነበር ፤ ነገርግን እንደተከታተላችሁት ያሰብነውን ማሳካት አልቻልንም። በተለይ የመጀመሪያው ጨዋታ መጥፎ ነበር። በሁለተኛው ጨዋታ የተሻለ አቀራረብ ነበረን። ነገርግን በነጥብ ደረጃ ያሰብነውን ማሳካት አልቻልንም።” የሚል አጠር ያለ ገለፃ ካደረጉ በኋላ ተከታዮቹ አንኳር ጥያቄዎች ከጋዜጠኞች ቀርበዋል።

ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ስኬታማ ነኝ ብለው ያስባሉ?

ስኬታማነት አንፃራዊ ነው። እኛ እየመራን ያለነው ብሔራዊ ቡድን ትክክለኛ መደላደል ላይ ያለ ቡድን አይደለም። ከመጀመሪያው የኒጀር ጨዋታ ጀምሮ ያሉት ነገሮችን ማየት አለብን። ነገርግን ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአፍሪካ ዋንጫ እና በቻን ውድድር ማለፋችን ትልቅ ነገር ነው። እርግጥ በውድድሮቹ አልፈን ረጅም ርቀት መጓዝ አልተቻለም። ይህንን ለዋሉ ሰዎች ክሬዲቱን መስጠት አለብን። ብሔራዊ ቡድናችን እንደነግብፅ በየሁለት ዓመቱ በአህጉራዊ ውድድሮች ሲሳተፍ የነበረ አይደለም።

በብሔራዊ ቡድኑ ይቀጥላሉ?

ይሄ የብዙዎች ጥያቄ እንደሆነ አስባለው። ይህ በእኔ ብቻ የሚወሰንም አይደለም። ድንገት አሁን ተነስቶ ይሄ ነው ማለት ከባድ ነው። ምክንያቱም የሁለት ዓመት ውል ነው ያለኝ። ስለዚህ ከቀጣሪዎቼ ጋር ያለውን ነገር መነጋገር አለብን። ከራሴም፣ ከቀጣሪዎቼም፣ ከነፍሴም ጋር ተነጋግሬ ቆይታዬን ወደፊት የምመልሰው ይሆናል።

ከግብፁ ጨዋታ አንፃር ቡድኑ ወጥ ያልሆነበት መንገድ…?

ከግብፁ ጨዋታ አሁን አምስት ተጫዋቾች በጊኒው ጨዋታ አልተጫወቱም። ሌሎች ብሔራዊ ቡድኖች በዓመታት ውስጥ የሚኖራቸው የተጫዋች ለውጥ በጣም ጥቂት ነው። አሁን ከጉዳት እና ከሌሎች ነገሮች ጋር ተያይዞ እንዳልኩት ተጫዋቾችን አጥተናል።

ያሰቡትን ነጥብ ስላለማሳካታቸው…?

ወደየትኛውም ጦርነት እሸነፋለው ብለህ አትገባም። እኛም ጊኒም እናሸንፋለን ብለን ነበር። እኛ ተሸንፈናል። አዎ መሸነፍ አልነበረብንም። እንደየትኛውም አሠልጣኝ በውድድሩ ውስጥ ለመቆየት የሚያስችል ነጥብ ማግኘት ነበረብን ፤ ግን አልሆነም። ከውድድሩ ወጥተን ሊሆን ይችላል። ግን ከዚህ ቀደም ተዋርደን የወጣንባቸው አጋጣሚዎች ነበሩን። አሁንም ቀጣይ የግብፅን ጨዋታ በጥሩ ዝግጅት ለመቅረብ እንጥራለን።

አሁን ያለንን ሊግ ማሳደር አለብን። በተለያየ አቅጣጫ ብሔራዊ ቡድኑን ለማሳደግ ስራዎች መሰራት አለባቸው። እየሰራን ያለነውም ነገር ፍፁም ነበር ማለት አልችልም።

ስለቀጣይ ጨዋታዎች…?

ውድድሩ ውስጥ እስካለን ድረስ ቀጣይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ነው የምናስበው። እርግጥ ሁለት ቡድኖች ርቀውን 9 ነጥብ ይዘዋል። እነሱ ላይ መድረስ ከባድ እንደሆነ ይገባኛል።

ከተጫዋቾች ጋር ስላላቸው ግንኙነት…?

የማሰልፋቸው ተጫዋቾች ለእኔ ጥሩ ነገር አላቸው። የማስቀምጣቸው ግን ሊደብራቸው ይችላል ብዬ አስባለው። ይሄ ያለ ነው። 23 ተጫዋች ቢኖርም የሚጫወቱት 11 ብቻ ናቸው። ሁሉም ተጫዋቾች እንዲያድጉ ነው ፍላጎቴ። በግልም እደውላለው የማየውን እናገራለው። እንደእኔ ሁሉንም ተጫዋቾች አንድ ነገርላይ እኩል እንዲሆኑ እፈልጋለው። አንድ ነገርግን ሁሉም ዲሲፕሊን እንዲሆኑ እፈልጋለው። ከዚህ ውጪ የተለየ ግንኙነት የለንም።

ስለመጀመሪያው ጨዋታ…?

በመጀመሪያ ጨዋታ ላይ ከፍተኛ የሆነ የኳስ ብክነት ነበር። ዳር ላይ ሆኜ ለማስተካከል ስጥር ነበር። ጨዋታው ከቁጥጥራችን ውጪ ነው የነበረው። እረፍት ላይም ነግሬያቸው ነበር። ተጫዋቾቹ አዳምጠውኛል ፤ ነገርግን ተግብረውታል ማለት አልችልም። በአጠቃላይ የመጀመሪያው ጨዋታ ከቀለማችን ውጪ ነበር። ለዚህ ነው እንደዚህ ለመጫወት አሠልጣኝ አያስፈልጋችሁም ያልኳቸው። እንደ መጀመሪያው ጨዋታ ለመጫወት ስልጠናም እኔም አላስፈልጋቸውም።

ከሚዲያ ጋር ስላላቸው ግንኙነት…?

ሁሉንም ሚዲያ አንድ ላይ መፈረጅ አልፈልግም። ሙያዊ ትችት የሚሰጡ፣ ያላየሁትን ነገር የሚጠቁሙ እና የሚያስተምሩኝ አሉ። አይደለም እነሱን የሚሰድቡኝንም አከብራለው። ስድብ የምለው ቃል በቃል ስድብ ስለሆነ ነው። የእኔንም የቤተሰቤንም ስም የሚያጠፉ እና አስተዳደጋቸውን በሚዲያቸው የሚያሳዩ አሉ። በእነሱ ደረጃ መባለግ አልፈልግም። ኳስ ያለ ሚዲያ ምንም ነው። ሁሉንም አከብራለው። ከማንም ጋር የተለየ ግንኙነት የለኝም። ሁሉንም አከብራለው። ከተቀጠርኩበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን በታሰበበት ሁኔታ ጥቃት ሲደርስብኝ ነበር። ግን ማለፍ ነው።

በመጨረሻ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ-አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ አጠር ያለ ገለፃ አድርገዋል። አቶ ባህሩ ለሞሮኮ መንግስት እና እግርኳስ ፌዴሬሽን ምስጋና አቅርበው ከአሠልጣኝ ቆይታ ጋር ተያይዞ “አዲስ ውል ከተፈራረምን በኋላ የተመዘገቡት ውጤቶች መሰረታዊ ናቸው። በዚህ ሂደት ውስጥ የኢትዮጵያ እግርኳስ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተዋዋልነውን ነገር የሚመለከት ይሆናል። በቀጣይ የሚኖረውንም ነገር የምትሰሙ ይሆናል። ከዚህ ውጪ ምንም ማለት አልፈልግም።” በማለት ከአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ቆይታ ጋር ተያይዞ የተነሳላቸውን ጥያቄ መልሰዋል።

ሶከር ኢትዮጵያ
576 views14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 22:19:45
➥ ቼልሲ ግርሃም ፖተርን አሰናብቷል

የምዕራብ ለንደኑ ቡድን ቼልሲ እንግሊዛዊዉን አሰልጣኝ ግርሃም ፖተርን ማሰናበቱን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ከቶማስ ቱኸል ስንብት በኋላ ስታንፎርድ ብሪጅ የደረሱት ፖተር በሰማያዊዎቹ ቤት የታሰበውን ውጤት ባለማስመዝገባቸው የስንብት ደብዳቤ ደርሷቸዋል።

ቼልሲ የፊታችን ማክሰኞ በፕሪሚየር ሊጉ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ከሊቨርፑል ጋር ይጫወታል።


ቅኝት በኳስ ሜዳ
1.0K views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 21:21:38
የቅኝት በኳስ ሜዳ ተንታኝ ሳላህ መሐመድ ከምሽቱ የኒውካስል ዩናይትድና ማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ተከታዩን ሀሳብ ሰጥቷል

የዛሬው ጨዋታ ያስታወሰኝ ከአመት በፊት በሴንት ጄምስ ፓርክ ኒውካስል አርሰናልን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፎ የአርሰናል ከአመታት በኋላ የቻምፒዮንስ ሊግ ላይ የመሳተፍ ህልሙን ያጨናገፈበት ጨዋታ ነው፤በዛ ጨዋታ ላይ በጨዋታው ለቻምፒዮንስ ሊግ ቦታ ይጫወት የነበረው ቡድን አርሰናል ሳይሆን የሚመስለው ኒውካስል ነበር አስገራሚ ተነሳሽነት የማሸነፍ ፍላጎት በጨዋታ ላይ አስመልክተውናል።


ኤዲ ሀው በተጨዋቾቹ ያሰረፁት መንፈስ እጅግ አስገራሚ ነው።በትንሽ ጊዜ ውስጥ ላለመውረድ ይጫወት የነበረ ቡድን በአንዴ ለቶፕ ፎር ተፎካካሪ ማድረግ ቀላል ስራ አይደለም።


ቅኝት በኳስ ሜዳ
983 views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 18:45:00
➥ ኦርጅናል የጎፈሬ ማልያ የሚያስገኝ ጥያቄ

1. ከሰሞኑ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ Hall Of Fame የክብር መዝገብ ላይ የሰፈሩ ሁለት አሰልጣኞች እነማን ናቸው?

A. ፈርጉሰንና ቬንገር B. ሞሪንሆና ክሎፕ C. ጋርዲዮላና ሆድሰን

መልሱን 7379 ላይ OK ብለው ተመዝግበው ብቻ ይመልሱ?





ቅኝት በኳስ ሜዳ
1.0K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 16:38:33
➥ ሌይስተር ሲቲ አሰልጣኙን አሰናብቷል

ሌይስተር ሲቲ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስን በይፋ ማሰናበታቸውን ገልፀዋል።

ቀበሮዎቹ ትናንት በ29ኛ ሳምንቱ በደቡብ ለንደኑ ክሪስታል ፓላስ 2-1 ከተሸነፉ በኋላ በወራጅ ቀጠናው ላይ በመገኘታቸው የ50 ዓመቱን ሰሜን አየርላንዳዊውን አሰልጣኝ ለማሰናበት ተገደዋል።



ቅኝት በኳስ ሜዳ
1.0K views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 11:31:42
➥ የቅኝት በኳስ ሜዳ ቀጥታ ስርጭት.....

Newcastle United Vs Manchester United

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት መርሐግብር በሴንት ጄምስ ፓርክ ኒውካስል ዩናይትድ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ቅኝት በኳስ ሜዳ ከ12:00 ጀምሮ በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ በአገር አቀፍ ስርጭት በቀጥታ ወደ እርስዎ እናደርሳለን።




ቅኝት በኳስ ሜዳ
1.1K views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 06:32:57 ማንቸስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል ድህረ-ጨዋታ ትንታኔ በቅኝት በኳስ ሜዳ

   ከአገራት ጨዋታዎች በኋላ 29ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ  በኢቲሀድ ማንቸስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል ባደረጉት ጨዋታ ጅማሮውን አድርጓል፤የሳምንቱ የመጀመሪያ ጨዋታ በነበረው በዚህ መርሀግብር ላይ በደጋፊያቸው ፊት ጨዋታውን ያደረጉት ውኃ ሰማያዊዮቹ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት ተጋጣሚያቸው የሆነው የመርሲሳይዱ ሊቨርፑልን ረተዋል።

  እንግዳዎቹ ሊቨርፑሎች ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋቾች መሀመድ ሳላህ በ 17ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት አስደናቂ ጎል አማካኝነት ጨዋታውን መምራት ጀምረው የነበረ ሲሆን ባለሜዳዎቹ ሲትዝኖቹ ጎል ካስተናገዱ ከ11 ደቂቃ በኋላ ዋነኛ የፊት መስመር አጥቂያቸው ሀላንድ በመጎዳቱ ምክንያት እሱን ተክቶ ጨዋታውን በቋሚነት የጀመረው አርጀቲናዊው የፊት አጥቂ ሁሊያን አልቫሬዝ ከግሪሊሽ የተላከለትን ኳሶ ወደ ግብነት በመቀየር ዳግም ውሀ ሰማያዊዮቹ ወደ ጨዋታው እንዲመለሱ አድርጓቸዋል።የመጀመሪያው አጋማሽም ተጨማሪ ጎሎች ሳይቆጠርበት 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል።

  ከመልበሻ ክፍል እንደተመለሱ በ 46ተኛው ደቂቃ ላይ ኬቨን ዴብራይን ከሰባት ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ሌላኛው የመሀል ሜዳ ተጨዋቾች ጉንዱኃን አማካኝነት በተከታታይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ሁለተኛው አጋማሽ በአስደናቂ ሁኔታ የጀመሩት ማንቸስተር ሲቲዎች በዕለቱ የጨዋታው ኮከብ ተጨዋቾች ያስባለውን ምርጥ እንቅስቃሴ እያደረገ የነበረው እንግሊዛዊው የማንቸስተር ሲቲ ውዱ ተጨዋቾች ጃክ ግሪሊሽ 73ተኛው ደቂቃ ላይ ተጨማሪ ጎል በማስቆጠር ከሙሉ የጨዋታ ብልጫ ጋር 4 ለ 1 ተጋጣሚያቸው የመርሲ ሳይዱን ሊቨርፑል በመርታት ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማሳካት ችለዋል።
ውኃ ሰማያዊዮቹም በምሳ ሰአቱ ጨዋታ ላይ ድል ማስመዝገባቸው ተከትሎ በስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የአሰልጣኝነት ዘመን በሜዳቸው ያስመዘገቡት 100ኛ ድል ሆኖ ተመዝግቦላቸዋል።

በ ጨዋታው  ላይ ሁለቱ ቡድኖች ወደ ሜዳ ይዘውት የገቡትን የጨዋታ አቀራረብ በጥልቀት በቀጣይ እንመለከታለን ።
የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች በብዛት የሚጠቀሙበት 4 3 3 ፎርሜሽን መነሻ የመጀመሪያ 11ድ ተጨዋቾቻቸውም በመምረጥ ወደ ሜዳ ይዘው ገብተዋል።ቡድኖቹ በወረቀት ላይ 4 3 3 መነሻ የተጨዋቾች አደራደር ይዘው ወደ ሜዳ ይግቡ እንጂ ሜዳ ውስጥ ከኳስ ጋር ያለ ኳስ የተለያየ አይነት ቅርፆች በመያዝ ነበር ይጫወቱ የነበሩት።
   ረጅም ደቂቃውን ከኳስ ጋር ያሳለፉት ባለሜዳዎቹ ማንቸስተር ሲቲዎች ከኳስ ጋር በሚሆኑበት ወቅት የቀኝ የመስመር ተከላካዩን ወደ መሀል በማስገባት ከተከላካይ አማካኙ ሮድሪ ጎን በማድረግ ሁለቱ #8 ቁጥሮች ዴብሪያንና ጉንዱሀን ወደ ፊት ተጠግተው በመስመሮች መሀል እንዲጫወቱ ያደረጉ ሲሆን ሜዳውን ወደ ጎን ለጥጠው መስመሩን ይዘው ሁለቱ የመስመር አጥቂዎቹን ማህሬዝና ግሪልሽ ከ ፊት አጥቂው አልቫሬዝ ጋር ወደ ፊት ተጠግተው እንዲቆሙ በማድረግ 3 2 2 3 ቅርፅ በመያዝ ለማጥቃት ይሞክሩ ነበር።
  ኳሱን ከኋላ መስመርተው በሚወጡበት ጊዜ በቁጥር ከሊቨርፑል ተጨዋቾች ከኋላ በዝተው ነፃ ተጨዋቾች ኳሱ አካባቢ መሀል ለመሀል አልያ መስመር ላይ(በተለይ የመሀል ተጨዋቾቹ ከመሀል ወደ መስመር በመውጣት ነፃ ሆነው ኳሱን ከያዘው ተጨዋቾች በቀጥታ አልያም ሶስተኛ ሰው በመቀበል )የሊቨርፑል የመጀመሪያ ጫና በማለፍ በእርጋታ ኳሱን ወደ ፊት ይዘው በመውጣት በተቻላቸው አቅም ጨዋታው ከራሳቸው የግብ ክልል እርቆ መሀል ሜዳ አካባቢ ና በሊቨርፑል የመከላከል ቀጠና ላይ በማድረግ ለመጫወት ይጥሩ ነበር።

  መሀል ሜዳና የሊቨርፑል የመከላከል ቀጠና ላይ ኳሱን በሚይዙበት ወቅት በኳሱ አካባቢ በቁጥር በዝተው አጭር ቅብብሎሾችን በማድረግ የሊቨርፑል ተጨዋቾች ወደ ኳሱ አካባቢ ከሳቡ በኋላ ከኳስ በተቃራኒ መስመር የቁጥር ብልጫ በመውሰድ ኳሱ ወደዛ መስመር በመቀየር እድሎችን ለመፍጠር ለማጥቃት ጥረት ያደርጉ ነበር።
  ሊቨርፑሎች የመሀል ለመሀል የሲቲ የኳስ ቅብብሎች ለመዝጋት ወደ መሀል ተሰብስበው በሚከላከሉበት ወቅት ሲቲዎች ከሊቨርፑል የመስመር ተከላካዮች ፊት ያለውን ቦታ ላይ ከመሀል ወደ መስመር ወጥተው የመሀል ተጨዋቾቹ ተቀብለው መልሰው ወደ መሀል በማስገባት ማጥቃቱን ወደ ሌላ መስመር ለመቀየር አልያም ደሞ ኳሱን በቀጥታ ለመስመር አጥቂዎቹ በመስጠት ከመስመር ወደ መሀል የመስመር አጥቂዎቹ ኳሱን ይዘው እየነዱ በመግባት እድሎችን እንዲፈጥሩ በማድረግ ለማጥቃት ጥረት ያደርጉ ነበር።

  ማንቸስተር ሲቲዎች በጨዋታው ተጋጣሚያቸው ሊቨርፑል ላይ የበላይነቱን እንዲወስዱ የበለጠ ጨዋታው የሊቨርፑል ሜዳ ላይ እንዲሆንና ተደጋጋሚ አደጋዎች እንዳይፈጠርባቸው ያደረጋቸው ከኳስ ውጪ የነበራቸው የመከላከል ስትራቴጂ ነበር።
ማንቸስተር ሲቲዎች ከፍ ብለው በሊቨርፑል ግብ ክልል አካባቢ በሚከላከሉበት ወቅት ሊቨርፑሎች ከኋላ ጊዜና ቦታ አግኝተው በምቾት ኳሱን ተቀባብለው እንዳይወጡ ለማድረግ በፍጥነት ኳስ የያዘው ተጨዋችን ጫና አድርጎ ኳስ ለመቀማት እንዲያመች ፊት ላይ በቁጥር በዝተው ለመከላከል ይሞክሩ ነበር ለዚህ እንዲረዳቸው የቀኝ የመስመር ተከላካዩ ጆን ስቶንስን ወደ ፊት ተጠግቶ የሊቨርፑል የመስመር ተከላካይ ላይ ጫና እያደረገ እንዲጫወት በሚያደርጉበት ሰአት የቡድኑ የመከላከል ቅርፅ አሴሜትሪካልና በጣም ተለዋዋጭ ቢሆንም 3 4 1 2 , 3 2 3 2 ይሆን ነበር ።
  
  ባልተለመደ ሁኔታ ብዙ ሰአታቸውን ከኳስ ውጪ ያሳለፉት ሊቨርፑሎች ወደ ፊት ተጠግተው ለመከላከል በሚሞክሩበት ጊዜ 4 4 2(4 2 3 1 , 4 2 4) በተቻላቸው አቅም የመሀል ለ መሀል የማቀበያ መስመር በመዝጋት ኳስ የያዙት ተጨዋች ላይ ጫና ለማድረግ ይሞክሩ ነበር ። አንፃራዊ ያለኳስ ወደ ራሳቸው ሜዳ ተጠግተው በ 4 4 2 ቅርፅ በሚከላከሉበት ጊዜ በተደራጀ ሁኔታ በመከላከል ተደጋጋሚ አደጋዎች እንዳይፈጠርባቸው በተለይ በመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ማድረግ ቢችሉም እንኳን እንደዚህ ቀደሙ አብዛኛውን ደቂቃ ወደ መሀል ተጠግተው በመከላከል ተጋጣሚያቸውን ቦታ በማሳጣት ኳስ በመቀበል በፈጣን ሽግግር እድሎችን ለመፍጠር ተቸግረው ነበር ።
 
  " Wow. They could whatever they wanted and we were lucky they weren’t in the most greedy mood."የርገን ክሎፕ


ቅኝት በኳስ ሜዳ
1.2K views03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 06:32:44
1.0K views03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ