Get Mystery Box with random crypto!

ማንቸስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል ድህረ-ጨዋታ ትንታኔ በቅኝት በኳስ ሜዳ    ከአገራት ጨዋታዎች በኋላ | ቅኝት በኳስ ሜዳ | Kegnit be Kuas Meda

ማንቸስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል ድህረ-ጨዋታ ትንታኔ በቅኝት በኳስ ሜዳ

   ከአገራት ጨዋታዎች በኋላ 29ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ  በኢቲሀድ ማንቸስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል ባደረጉት ጨዋታ ጅማሮውን አድርጓል፤የሳምንቱ የመጀመሪያ ጨዋታ በነበረው በዚህ መርሀግብር ላይ በደጋፊያቸው ፊት ጨዋታውን ያደረጉት ውኃ ሰማያዊዮቹ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት ተጋጣሚያቸው የሆነው የመርሲሳይዱ ሊቨርፑልን ረተዋል።

  እንግዳዎቹ ሊቨርፑሎች ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋቾች መሀመድ ሳላህ በ 17ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት አስደናቂ ጎል አማካኝነት ጨዋታውን መምራት ጀምረው የነበረ ሲሆን ባለሜዳዎቹ ሲትዝኖቹ ጎል ካስተናገዱ ከ11 ደቂቃ በኋላ ዋነኛ የፊት መስመር አጥቂያቸው ሀላንድ በመጎዳቱ ምክንያት እሱን ተክቶ ጨዋታውን በቋሚነት የጀመረው አርጀቲናዊው የፊት አጥቂ ሁሊያን አልቫሬዝ ከግሪሊሽ የተላከለትን ኳሶ ወደ ግብነት በመቀየር ዳግም ውሀ ሰማያዊዮቹ ወደ ጨዋታው እንዲመለሱ አድርጓቸዋል።የመጀመሪያው አጋማሽም ተጨማሪ ጎሎች ሳይቆጠርበት 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል።

  ከመልበሻ ክፍል እንደተመለሱ በ 46ተኛው ደቂቃ ላይ ኬቨን ዴብራይን ከሰባት ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ሌላኛው የመሀል ሜዳ ተጨዋቾች ጉንዱኃን አማካኝነት በተከታታይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ሁለተኛው አጋማሽ በአስደናቂ ሁኔታ የጀመሩት ማንቸስተር ሲቲዎች በዕለቱ የጨዋታው ኮከብ ተጨዋቾች ያስባለውን ምርጥ እንቅስቃሴ እያደረገ የነበረው እንግሊዛዊው የማንቸስተር ሲቲ ውዱ ተጨዋቾች ጃክ ግሪሊሽ 73ተኛው ደቂቃ ላይ ተጨማሪ ጎል በማስቆጠር ከሙሉ የጨዋታ ብልጫ ጋር 4 ለ 1 ተጋጣሚያቸው የመርሲ ሳይዱን ሊቨርፑል በመርታት ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማሳካት ችለዋል።
ውኃ ሰማያዊዮቹም በምሳ ሰአቱ ጨዋታ ላይ ድል ማስመዝገባቸው ተከትሎ በስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የአሰልጣኝነት ዘመን በሜዳቸው ያስመዘገቡት 100ኛ ድል ሆኖ ተመዝግቦላቸዋል።

በ ጨዋታው  ላይ ሁለቱ ቡድኖች ወደ ሜዳ ይዘውት የገቡትን የጨዋታ አቀራረብ በጥልቀት በቀጣይ እንመለከታለን ።
የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች በብዛት የሚጠቀሙበት 4 3 3 ፎርሜሽን መነሻ የመጀመሪያ 11ድ ተጨዋቾቻቸውም በመምረጥ ወደ ሜዳ ይዘው ገብተዋል።ቡድኖቹ በወረቀት ላይ 4 3 3 መነሻ የተጨዋቾች አደራደር ይዘው ወደ ሜዳ ይግቡ እንጂ ሜዳ ውስጥ ከኳስ ጋር ያለ ኳስ የተለያየ አይነት ቅርፆች በመያዝ ነበር ይጫወቱ የነበሩት።
   ረጅም ደቂቃውን ከኳስ ጋር ያሳለፉት ባለሜዳዎቹ ማንቸስተር ሲቲዎች ከኳስ ጋር በሚሆኑበት ወቅት የቀኝ የመስመር ተከላካዩን ወደ መሀል በማስገባት ከተከላካይ አማካኙ ሮድሪ ጎን በማድረግ ሁለቱ #8 ቁጥሮች ዴብሪያንና ጉንዱሀን ወደ ፊት ተጠግተው በመስመሮች መሀል እንዲጫወቱ ያደረጉ ሲሆን ሜዳውን ወደ ጎን ለጥጠው መስመሩን ይዘው ሁለቱ የመስመር አጥቂዎቹን ማህሬዝና ግሪልሽ ከ ፊት አጥቂው አልቫሬዝ ጋር ወደ ፊት ተጠግተው እንዲቆሙ በማድረግ 3 2 2 3 ቅርፅ በመያዝ ለማጥቃት ይሞክሩ ነበር።
  ኳሱን ከኋላ መስመርተው በሚወጡበት ጊዜ በቁጥር ከሊቨርፑል ተጨዋቾች ከኋላ በዝተው ነፃ ተጨዋቾች ኳሱ አካባቢ መሀል ለመሀል አልያ መስመር ላይ(በተለይ የመሀል ተጨዋቾቹ ከመሀል ወደ መስመር በመውጣት ነፃ ሆነው ኳሱን ከያዘው ተጨዋቾች በቀጥታ አልያም ሶስተኛ ሰው በመቀበል )የሊቨርፑል የመጀመሪያ ጫና በማለፍ በእርጋታ ኳሱን ወደ ፊት ይዘው በመውጣት በተቻላቸው አቅም ጨዋታው ከራሳቸው የግብ ክልል እርቆ መሀል ሜዳ አካባቢ ና በሊቨርፑል የመከላከል ቀጠና ላይ በማድረግ ለመጫወት ይጥሩ ነበር።

  መሀል ሜዳና የሊቨርፑል የመከላከል ቀጠና ላይ ኳሱን በሚይዙበት ወቅት በኳሱ አካባቢ በቁጥር በዝተው አጭር ቅብብሎሾችን በማድረግ የሊቨርፑል ተጨዋቾች ወደ ኳሱ አካባቢ ከሳቡ በኋላ ከኳስ በተቃራኒ መስመር የቁጥር ብልጫ በመውሰድ ኳሱ ወደዛ መስመር በመቀየር እድሎችን ለመፍጠር ለማጥቃት ጥረት ያደርጉ ነበር።
  ሊቨርፑሎች የመሀል ለመሀል የሲቲ የኳስ ቅብብሎች ለመዝጋት ወደ መሀል ተሰብስበው በሚከላከሉበት ወቅት ሲቲዎች ከሊቨርፑል የመስመር ተከላካዮች ፊት ያለውን ቦታ ላይ ከመሀል ወደ መስመር ወጥተው የመሀል ተጨዋቾቹ ተቀብለው መልሰው ወደ መሀል በማስገባት ማጥቃቱን ወደ ሌላ መስመር ለመቀየር አልያም ደሞ ኳሱን በቀጥታ ለመስመር አጥቂዎቹ በመስጠት ከመስመር ወደ መሀል የመስመር አጥቂዎቹ ኳሱን ይዘው እየነዱ በመግባት እድሎችን እንዲፈጥሩ በማድረግ ለማጥቃት ጥረት ያደርጉ ነበር።

  ማንቸስተር ሲቲዎች በጨዋታው ተጋጣሚያቸው ሊቨርፑል ላይ የበላይነቱን እንዲወስዱ የበለጠ ጨዋታው የሊቨርፑል ሜዳ ላይ እንዲሆንና ተደጋጋሚ አደጋዎች እንዳይፈጠርባቸው ያደረጋቸው ከኳስ ውጪ የነበራቸው የመከላከል ስትራቴጂ ነበር።
ማንቸስተር ሲቲዎች ከፍ ብለው በሊቨርፑል ግብ ክልል አካባቢ በሚከላከሉበት ወቅት ሊቨርፑሎች ከኋላ ጊዜና ቦታ አግኝተው በምቾት ኳሱን ተቀባብለው እንዳይወጡ ለማድረግ በፍጥነት ኳስ የያዘው ተጨዋችን ጫና አድርጎ ኳስ ለመቀማት እንዲያመች ፊት ላይ በቁጥር በዝተው ለመከላከል ይሞክሩ ነበር ለዚህ እንዲረዳቸው የቀኝ የመስመር ተከላካዩ ጆን ስቶንስን ወደ ፊት ተጠግቶ የሊቨርፑል የመስመር ተከላካይ ላይ ጫና እያደረገ እንዲጫወት በሚያደርጉበት ሰአት የቡድኑ የመከላከል ቅርፅ አሴሜትሪካልና በጣም ተለዋዋጭ ቢሆንም 3 4 1 2 , 3 2 3 2 ይሆን ነበር ።
  
  ባልተለመደ ሁኔታ ብዙ ሰአታቸውን ከኳስ ውጪ ያሳለፉት ሊቨርፑሎች ወደ ፊት ተጠግተው ለመከላከል በሚሞክሩበት ጊዜ 4 4 2(4 2 3 1 , 4 2 4) በተቻላቸው አቅም የመሀል ለ መሀል የማቀበያ መስመር በመዝጋት ኳስ የያዙት ተጨዋች ላይ ጫና ለማድረግ ይሞክሩ ነበር ። አንፃራዊ ያለኳስ ወደ ራሳቸው ሜዳ ተጠግተው በ 4 4 2 ቅርፅ በሚከላከሉበት ጊዜ በተደራጀ ሁኔታ በመከላከል ተደጋጋሚ አደጋዎች እንዳይፈጠርባቸው በተለይ በመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ማድረግ ቢችሉም እንኳን እንደዚህ ቀደሙ አብዛኛውን ደቂቃ ወደ መሀል ተጠግተው በመከላከል ተጋጣሚያቸውን ቦታ በማሳጣት ኳስ በመቀበል በፈጣን ሽግግር እድሎችን ለመፍጠር ተቸግረው ነበር ።
 
  " Wow. They could whatever they wanted and we were lucky they weren’t in the most greedy mood."የርገን ክሎፕ


ቅኝት በኳስ ሜዳ