2023-03-20 22:11:29
የሎስ ብላንኮዎቹ ጭላንጭል የዋንጫ ተስፋ ያከሰመች የመጨረሻ ደቂቃ የኬሲ ጎል....
ድህረ-ጨዋታ ምልከታ➥በቅኝት በኳስ ሜዳ
የስፔን ላሊጋ የ 26ኛ ሳምንት መርሀግብሮች ከአርብ ምሽት ጀምሮ መካሄድ የጀመሩ ሲሆን በብዙዎች በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ጨዋታ የሳምንቱ መዝጊያ ጨዋታ የነበረው የሊጉን መሪ የዣቪው ባርሴሎና ከ ተከታያቸው የካርሊቶው ሪያል ማድሪድ ጋር በስፖቲፋይ ካምፕ ኑ ያገናኘው መርሀግብር ነበር።
ነጮቹ የሊጉ ዋንጫ ላይ እስከመጨረሻ ሳምንት ድረስ ከብሩግራናዎቹ ጋር ተፎካካሪ ሆነው ለመቀጠል ከሜዳቸው ውጪ ተጉዘው ከዣቪ ልጆች ላይ በደጋፊያቸው ፊት ነጥብ በመውሰድ ከጨዋታው በፊት የነበረውን የዘጠኝ ነጥብ ልዩነት አጥበው ወደ ቤርናቢዩ በተስፋ ለመመለስ እስከመጨረሻው ደቂቃ ድረስ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ ቢሆንም በእለቱ ከተጠባባቂ ወንበር ተነስቶ ጨዋታው ላይ ለዣቪው ባርሴሎና ግልጋሎትን የሰጠው አይቮሪያዊው የመሀል ሜዳ ተጨዋቾች ፍራንክ ኬሲ በመጨረሻ ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ሎስብላንኮዎቹ ለዋንጫው የነበራቸው ጭላንጭ ተስፋ አክስሞባቸዋል።
ሁለቱ የስፔን ኃያላን ቡድኖች መሀል አስደናቂ ተጋድሎ በተመለከትንበት ኤልክላሲኮ ላይ የነበረውን የቡድኖችን ታክቲካዊ አቀራረብ በቀጣይ የምንመለከት ሲሆን በመጀመሪያ የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ እንመለከታለን።
ሁለቱም አሰልጣኞች በ 4 3 3 ፎርሜሽን መነሻ ቋሚ 11ድ ተጫዋቾቻቸውን መርጠዋል፤የባለሜዳዎቹ አሰልጣኝ ዣቪ ሄርናንዴዝ በግብ ጠባቂነት ጀርመናዊውን የግብ ዘብ ቴርስቴገንን በማድረግ ከሱ ፊት በአብዛኛው በሊጉ ላይ አዘውትሮ የሚጠቀምባቸውን የኋላ አራት ተጨዋቾች በዚህም ጨዋታ ላይ ተጠቅሟል፤በዚህም በግራ ስፔናዊውን ወጣት የመስመር ተከላካይ ባልዴን ሲጠቀም በቀኝ መስመር ተከላካይ ትልልቅ ጨዋታዎች ላይ የተቃራኒ ጠንካራ ተጫዋችን የማቆም ኃላፊነትን የሚወጣውን አራሆን መስመር ላይ በማድረግ መሀል ላይ ኩንዴና ክሪስተንሰንን ከኋላ መስመሩን እንዲመሩ መርጧቸዋል ፣ በተከላካይ አማካኝነት ቡስኬትን በማድረግ ከሱ ጎን በ#8 ቁጥር ሚና ዲዮንግንና ሁለገቡን ሰርጂ ሮቤርቶን የመሀል ክፍሉ ላይ አጣምሯል ፣ ፖላንዳዊውን የፊት አጥቂ ሌቫንዶቪስኪን ከ ራፊናና ጋቪ ጋር በመሆን ፊት መስመሩ ላይ በማጣመር በ 4 3 3 መነሻ የተጨዋቾች አደራደር በመያዝ ወደ ሜዳ ገብቷል።
የእንግዳዎቹ ሎስብላካዎቹ ጣልያናዊው አሰልጣኝ ካርሊቶ በ 4 3 3 መነሻ የተጨዋቾች አደራደር በግብ ጠባቂነት ቤልጄማዊውን የግብ ዘብ ኩርቱዋ በማድረግ ከሱ ፊት በጉዳት ምክንያት ሙሉ ለ ሙሉ ለጨዋታ ዝግጁ የሆነ ተፈጥሯዊ የግራ መስመር ተከላካይ አለመኖሩን ተከትሎ ኋላ መስመር ላይ ሁለገብ የሆነውን ስፔናዊው የመሀል ተከላካይ ናቾ ወደ ግራ በማውጣት የተጠቀሙት ሲሆን በቀኝ መስመር ካርቫሀልን በማድረግ ከነሱ መሀል ሚሊታኦን ከ ሩዲገር የኋላ መስመራቸው ላይ አጣምረዋል ፣ በወረቀት ላይ በተከላካይ አማካይነት ወጣቱን ፈረንሳያዊውን ካማቬንጋን ከአንጋፋዎቹ የመሀል ሜዳ ተጨዋቾች ክሩስና ሞድሪች ጋር በማጣመር የመሀል ሜዳውን እንዲመሩላቸው የመረጡ ሲሆን ፣ ቤንዜማን ከሁለገቡ ቫልቬርዴና ቪኒሺየሽ ጋር ሆነው የፊት መስመራቸውን እንዲመራቸው ወደ ሜዳ አስገብተዋቸዋል።
" We will try to have control with the ball. We want to be better than the Copa del Rey match. ዣቪ ከጨዋታ በፊት የተናገረው ።
ከሳምንታት በፊት በቤርናቢዩ በተከናወነው የኮፓ ዴላሬ ጨዋታ ላይ የዣቪው ባርሴሎና ከሪያል ማድሪድ ጫና ከተቋቋመው ኳስ መስመርተው ለመውጣት ተቸግረው የኳስ ቁጥጥር የበላይነቱንም በሪያል ማድሪዶች ተወስዶባቸው ተመልክተናል።በዚህ ጨዋታ ላይ ባርሴሎናዎች ከኋላ መስመርቸው ለመውጣት በሚሞክሩበት ጊዜ የሪያል ማድሪድን ሀይ ፕረሲንግ ለማለፍ ቀጥተኛ ኳሶችን ምርጫ አድርገዋል።በዚህም ቴርስቴገን ረጅም ኳሶችን ወደ ፊት ሌቫንዶቪስኪን ታሳቢ ያደረገ ኳስ አልያም ወደ መስመር ነፃውን የባርሴሎና ተጨዋቾች ታሳቢ ያደረገ አግድሞሽ ኳሶችን በመጠቀም የመጀመሪያ የሪያል ማድሪድ ጫና በመውጣት ኳሱን ወደ ፊት መውሰድ ችለዋል።
ኳሱን መሀል ሜዳና የተቃራኒ ሳጥን አካባቢ በሚሆንበት ጊዜ ባርሴሎናዎች ግራ መስመር ማጥቃቱን በማድረግ በቁጥር በዝተው በቦታ ልወውጦች ነፃ ተጨዋቾች በመፈለግ ለነሱ ኳሶችን በመስጠት ለማጥቃት።ከዚህ በተጨማሪ ሪያል ማድሪድን ወደ ግራ በመሳብ በቀኝ መስመር ላይ ራፊና ጊዜና ቦታ እንዲኖረው በማድረግ ኳሶችን ከግራ ወደ ቀኝ በመገልበጥ እድሎችን ለመፍጠር ጥረት ያደርጉ ነበር።ምንም እንኳን የመጨረሻ ሜዳ ላይ ከደረሱ በኋላ የባርሴሎና ተጨዋቾች ውሳኔ አፈፃፀም ላይ የነበረባቸው ድክመት እንደነበራቸው የበላይነት በተደጋጋሚ መልኩ የሪያል ማድሪድ ቀጠና ላይ እንደመድረሳቸው ጥራት ያላቸው እድሎች እንዳይኖር አድርጓቸዋል።
Ronald Araujo: "Yes, Xavi plays me as a right back against wingers that are 1v1 specialists, which I think is a capacity of mine. You can see it with players like Vinicius. What I do is that I analyze them, I watch a lot of videos and plays."
የሪያል ማድሪድ አደገኛው ተጨዋቾች መሀል አንደኛው ብራዚላዊው የመስመር አጥቂ ቪኒሺየሽ ጁንየር ነው። ቪኒ የሚገኝበት የግራ መስመር የሪያል ማድሪድ ዋነኛ የማጥቂያ መስመር ነው። ዣቪ ይህን የሪያል አደገኛ ተጨዋቾች ለመቆጣጠር የአንድ ለ አንድ መከላከል ላይ ጥሩ ብቃት ያለውን አራሆን ከመሀል ወደ መስመር በማውጣት ቪኒን እንዲቆጣጠር ሀላፊነት ተሰጥቶታል።ነገር ግን ባርሴሎና ያለ ኳስ በተለይ ወደ ላይ ከፍ ብለው በሚከላከሉበት ወቅት አግሬሲቭ የሆነ የሰው ለ ሰው መከላከሉ የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ከኋላ በምቾት መስርተው እንዳይወጡ አድርጓቸዋል።ምንም እንኳን በተለይ የመሀል ተጨዋቾቹ በጫና ውስጥ ኳሶችን ተቆጣጥረው ወደ ፊት የመውሰድ አቅም ያላቸው ቢሆኑም እንኳን የባርሴሎና ያለኳስ የነበራቸው ታታሪነት ሪያል በተደጋጋሚ ከኋላ መስመርተው ኳሶችን ወደ ፊት ይዘው በመውጣት ተደጋጋሚ አደጋ ለመፍጠር እንዳይችሉ አድርገዋቸዋል።
ሪያል ማድሪዶች ቅያሪዎችን በኋላ የተሻለ መንቀሳቀስ እድሎችን ለመፍጠር ጥረት አድርገዋል። በመጨረሻ ደቂቃ ላይ የሪያል ማድሪድ የመከላከል ስህተት በስተመጨረሻም ልፋታቸውን ፋይዳ ቢስ አድርጎባቸው ባርሴሎናዎችም ከተከታያቸው ያላቸውን ነጥብ ወደ 12 ከፍ ማድረግ ችለዋል።
ቅኝት በኳስ ሜዳ
1.2K views19:11