2022-06-26 22:44:29
የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ተሳታፊ ከሆኑ ቡድኖች ውስጥ የ"ቶፕ 6" የቅድመ ውድድር ዝግጅት መች ይጀምራሉ ? የወዳጅነት ጨዋታዎች ከማን ጋር ያደርጋሉ ?የቡድኖቹን የቅድመ ውድድር ዘመን እቅድ የምናጋራቹህ ይሆናል።
1. ማንቸስተር ሲቲ
ማንቸስተር ሲቲ በትክክል ወደ ቅድመ ልምምድ መቼ እንደሚመለሱ ባይቀመጥም ፣ ቅድመ ውድድር ልምምዳቸውን እንዲሁም የመጀመሪያ የአቋም መፈተሻ በአሜሪካ እንደሚያደርጉ ታውቋል።
ጁላይ 21 ከ ክለብ አሜሪካ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ጁላይ 24 ከባየርን ሙኒክ
ጁላይ 30 በኪንግ ፓወር በእንግሊዝ ኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ሊቨርፑል ካስተናገዱ ከሳምንት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ከዌስተሀም ጋር በሚደረግ ጨዋታ የ 2022/23 የውድድር አመት የሚጀምሩ ይሆናል።
2.ሊቨርፑል
የሊቨርፑል የቡድን አባላት july 4 ልምምድ መስሪያቸው በመሰብሰብ የቅድመ ውድድር ልምምዳቸውን የሚጀምሩት ቀዮቹ ፣ የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸው ለማድረግ ጁላይ 9 ወደ ታይላንድ በማቅናት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጁላይ 12 ከማንተስተር ዩናይትድ ጋር በባንኮክ የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ ያከናውናሉ።
ጁላይ 15 ከ ክሪስታል ፓላስ ጋር ሁለተኛ ጨዋታዎች ያከናውናሉ።
ጁላይ 27 ከ ሳልዝበር ጋር ጨዋታ ያደርጋሉ።
ጁላ 30 በኪንግ ፓወር ከማንቸስተር ሲቲ ጋር የኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ካደረጉ በኋላ በነጋታው ጁላይ 31 ከስትራስቡርግ ጋር በአንፊልድ የመጨረሻ የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
2.ቼልሲ
ቼልሲዎች ወደ አሜሪካ ጁላይ 9 ከመብረሩ በፊት በኮብሀም የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጁላይ 16 ከክለብ አሜሪካ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን ይጀምራሉ።
ጁላይ 20 ከ ቻርለት ጋር ሁለተኛ ጨዋታውን ለማድረግ መርሀግብር ወጥቶለታል።
ጁላይ 23 በአሜሪካ ከአርሰናል ጋር የመጨረሻ የአቋም መፈተሻቸውን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
4. ቶተንሀም ሆትስፐር
ቶተንሀም ሊጉ ከተጠናቀቀ በኋላ የሀገራት ጨዋታ ላይ ተሳትፎ ያላደረጉ ተጨዋቾች ጁላይ 4 የቅድመ ውድድር ልምምዳቸውን እንዲጀመሩ ተነግሯቸዋል፤የሀገራት ጨዋታ ተሳትፎ ያደረጉ ተጨዋቾች ጁላይ 9 ከቡድኑ ጋር በመቀላቀል ወደ ደቡብ ኮሪያ ከቡድኑ ጋር እንደሚጓዙ ታውቋል።
ጁላይ 13 ቲም ከ ሊግ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በደቡብ ኮሪያ በማድረግ ይጀምራሉ።
ጁላይ 16 ከሲቪያ ጋር ይጫወታሉ ።
ጁላይ 23 ከሪንጀርስ ጋር ይጫወታሉ።
ጁላይ 30 ከ ሮማ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ይፈፅማሉ።
5.አርሰናል
የሚኬል አርቴታ ልጆች ጁን 27 ወደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት ይመለሳሉ።
አርሰናል ወደ ጀርመን በማቅናት
ጁላይ 8 ከ ኖርበርግ ጋር የመጀሪያዉን የአቋም መፈተሻ ያደርጋል።
ጁላይ 16 ከኤቨርተን ጋር ይጫወታሉ።
ጁላይ 20 ከ ኦርላንዶ ሲቲ ጋር ይጫወታሉ።
ጁላዬ 23 ቼልሲ ጋር
ጁላይ 30 በኤምሬትስ ከ ሲቪያ ጋር ጨዋታ በማድረግ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ያጠቃልላሉ።
6.ማንቸስተር ዩናይትድ
አዲሱ ሆላንዳዊው የዩናይትድ አለቃ ተጨዋቾች በጊዜ ወደ ቅድመ ውድድር ዘመን እንዲመለሱ በማድረግ የበለጠ የመዘጋጃ ጊዜ ለማሳለፍ በማሰብ የቡድን አባላቶቹ ጁን 27 ወደ ልምምድ ማዕከል እንዲመጡ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
ወደ እስያ በማምራት በታይላንድ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያደርጋሉ።
ጁላይ 12 ከሊቨርፑል ጋር በሚያደርግጉት ጨዋታ የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን ይጀምራሉ።
ጁላይ 15 ሜልቦርን ቪክቶር ጋር ይጫወታሉ።
ጁላይ 19 ከክሪስታል ፓላስ ጋር ይጫወታሉ።
ጁላይ 23 አስቶን ቪላ ጋር ይጫወታሉ።
ጁላይ 30 ከ አትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ጨዋታ ካደረጉ በኋላ ጁላይ 31 በኦልትራፎርድ የመጨረሻ የቅድመ ውድድር ጨዋታውን ከ ራዮ ቫዬካኖ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።
ተጨማሪ ትኩስ የስፖርት መረጃዎችን በየዕለቱ ለማግኘት በስልክዎ ወደ 6655 Ok ብለዉ ይመዝገቡ!!
ቅኝት በኳስ ሜዳ
565 viewsTadesse Abiyu, 19:44