2022-08-23 00:59:04
➔ ኤሪክ ቴን ሀግ የመጀመሪያ ድላቸውን አስመዝግበዋል
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት መርሃግብር በኦልድትራፎርድ ስቴዲየም ማንቸስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 2-1 በማሸነፍ በውድድር አመቱ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል።
በሊጉ ሁለት ተከታታይ የመክፈቻ ጨዋታዎችን በብራይተንና ብሬንትፎርድ የተሸነፉት ማንቸስተር ዩናይትድ በዛሬው ጨዋታ ሀሪ ማጓየርንና ክሪስቲያኖ ሮናልዶን በተቀያሪ ቦታ በማስቀመጥ የጀመሩ ሲሆን ጎል ለማስቆጠርም 16 ደቂቃ ብቻ ፈጅቶባቸዋል፤በጄደን ሳንቾ አማካኝነት 16ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረው ገና በጊዜ መሪ መሆን ችለዋል።
ከዕረፍት መልስ ማርከስ ራሽፎርድ ተጨማሪ ጎል ለዩናይትድ በማስቆጠር የጎል ልዩነቱን ወደ ሁለት ከፍ ያደረገ ሲሆን ወደ ጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ ሊቨርፑል በመሀመድ ሳላህ አማካኝነት ጎል በማስቆጠር ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ቢያደርጉም ተጨማሪ ጎል ሳያስቆጥሩ ጨዋታው በማንቸስተር ዩናይትድ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ሊቨርፑል በ2022 ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪሚየር ሊጉ ተሸንፏል
ኤሪክ ቴን ሀግ በዩናይትድ ቤት የመጀመሪያ ድላቸውን አሳክተዋል
ማንቸስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ ሊቨርፑልን ሲያሸንፍ ከ2018 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው
መሀመድ ሳላህ ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ 10 ጎሎችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው የሊቨርፑል ተጫዋች ሆኗል።
ማርከስ ራሽፎርድ ለማንቸስተር ዩናይትድ በሁለም ውድድሮች ጎል ሲያስቆጥር ከ997 ደቂቃዎች በኋላ ነው
በቀጣይ ማንቸስተር ዩናይትድ በ4ኛ ሳምንት በመጪው ቅዳሜ ወደ ሴንት ሜሪ በማቅናት ከሳውዛፕተን ጋር 8:30 ላይ ሲጫወት ሊቨርፑል ደግሞ በአንፊልድ የስኮት ፓርከሩን ቦርንማውዝን ይገጥማል።
ቅኝት በኳስ ሜዳ
220 viewsTadesse Abiyu, 21:59