2022-07-13 15:24:17
➔ ማንቸስተር ሲቲን በ2022/23 በምን መልኩ ልንመለከተዉ እንችላለን?
ለትንታኔያችን እንደ መንደርደሪያ የምንጠቀመዉ የማንቸስተር ሲቲ ዋና ስራ አስኪያጅ ፋራን ሶሪያኖ በቅርቡ ከሰጡት ሀሳብ ይሆናል። " the current squad is very good. we need to change only what we need to change and we need to change two things : we need a striker we have it and we need a replacement for fernandinho. we have one rodri ,but we need another because the season is very long.
ማንቸስተር ሲቲ በአውሮፓ ላይ ጥሩ የተጨዋቾች ስብስብ ከያዙ ቡድኖች አንዱ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፤ይህ ቢሆንም ግን ቡድኑ ጥገናዎች አይፈልግ ማለት ግን አይደለም፤ እውን በአመት በሊግ ላይ ብቻ ከ 90 በላይ ጎል ያስቆጠረ ቡድን አጥቂ ለማስፈረም ወደ ገበያ መውጣት ያስፈልገው ነበር ? ያስቆጠረውን የጎል ብዛት ብቻ ከተመለከትን ምናልባት ኧረ በፍፁም ምን አጥቶ ልንል እንችላለን፤ነገር ግን የፊት አጥቂ ወደ ቡድኑ መቀላቀሉ አስፈላጊ ነው የምንለው ትክክለኛ የፊት አጥቂ ባለመያዙ ውጤት ያጣባቸው ጨዋታዎች ስንት ናቸው ? ብለን ስንጠይቅ ነው።
በተለይ የተሻሉ ተጨዋቾች ከያዙ ቡድኖች ጋር ? የሚለውን በምንመለከት ጊዜ በተለይ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ የሚመክኑት ኳሶች ቡድኑን ዋጋ እንዳስከፈሉት የምንረዳ ሲሆን የሲቲ መልማዮችም ወደ ቡድናቸው የፊት አጥቂ መጨመራቸው በጎ የሚያስብል ስራ እንደሆነ ልብ እንላለን።
ፔፕ ጓርዲዮላ "የፊት መስመር አጥቂ አይፈልግም ወይም ያለ አጥቂ የተሻለ ቡድን ነው የሚሰራው" የሚሉ ሀሳቦች በተደጋጋሚ በመገናኛ ለብዙኀን የሚሰራጩ መረጃዎች እንደሆኑ ይታወቃል።
እንደውም በተጠናቀቀው የውድድር አመት ቡድኑ ያለ አጥቂ እየተጫወተ ጎሎችን እያስቆጠረ ውጤት እያስመዘገበ በነበረበት ወቅት ጓርዲዮላ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለ አጥቂ ከጋዜጠኞች ጥያቄ በተነሳበት ወቅት" I think the club need a striker ,definitely. You say we play fantastically well without a striker because we are winning. When we are not winning ,you say we need striker." ብሎ ነበር ለተነሳለት ጥያቄ መልስ የሰጠው። በዛው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፔፕ አጥቂ እንደሚያስፈልገው ብቻ ሳይሆን ያለ አጥቂ ቡድኑ ጥሩ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ሁሌ ይሳካል ማለት አለመሆኑ ወይም ከአቅም በላይ የሚሆኑበት ጨዋታዎች እንዳሉ አመላክቶ ነበር።
ስለዚህ መጠየቅ የሚኖርብን ፔፕ ምን አይነት አጥቂ ነው የሚፈልገው ? ወይም ከአጥቂዎች ጎል ብቻ ነው የሚጠይቀው ? የሚለውን ይመስለኛል። ፔፕ በአንድ ወቅት አጉዌሮ ጎሎች እያስቆጠረ በነበረበት ወቅት ስለ ፊት አጥቂው ጥያቄ በቀረበለት ሰዓት ተከታዩን ሀሳብ ነበር ያጋራው" to score five goals in two games is a good statistic. But he has to help us in the first pressure and run a lot and help us a lot with movements.you can't be brilliant when you disappear When you don't have the ball."
ስፔናዊው የማንቸስተር ሲቲ አለቃ ከአጥቂዎቹ ጎል ብቻ ሳይሆን ያለኳስ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ቦታዎችን በመፍጠር እንዲሁም የተቃራኒ ቡድኑ ኳስ በሚይዙበት ወቅት መከላከሉን በማስጀመር ቡድኑን እንዲያግዙለት ይፈልጋል።
አሰልጣኙ ከፊት መስመር አጥቂው ከጎል አዳኝነት በተጨማሪ ምን ይፈልጋል የሚለውን በዚህ መልኩ ካየን የመጡት ተጨዋቾች ለእርሱ የሚሆን ነገር አላቸው ወይ ? የሚለውን እና ማሻሻል የሚኖርባቸው ነገር ለመመልከት እንሞክራለን።
የአጥቂ አቅም ዋነኛ መለኪያ ጎል ነው የምንል ከሆነ እና ወደ ፔፕ ስብስብ የተቀላቀሉትን የፊት አጥቂዎቹ አልቫሬዝ እና ሀላንድ ሲጫወቱበት በነበረው ሊግ ላይ ለቡድናቸው ያስቆጠሯቸውን ጎሎች ከተመለከትን እንዲሁም ገና አቅማቸው ከዚህ በላይ የማደግ እድል እንዳለው ታሳቢ ካደረግን ግዢው ለቡድኑ ጠቃሚ መሆኑን እና ለቡድኑ የሚጨምሩት አንዳች ነገር እንዳለ መመስከር ያስችለናል። ሀላንድ የጀርመኑን ቦርሲያ ዶርትሙንድን ከተቀላቀለ በኋላ በጨዋታ ቢያንስ አንድ ጎል ያስቆጥር ነበር ፤ ካስቆጠራቸው ጎሎች መሐል የፍፁም ቅጣት ምት ጎሎችን አውጥተን ከፍፁም ቅጣት ምት ውጪ በጨዋታ ያስቆጠራቸው ጎሎች 0.81 ናቸው፤ ወጣቱ አርጀቲናዊው የፊት አጥቂ አልቫሬዝ ደግሞ በአርጀቲናው ሪቨር ፕሌት በሚጫወትበት ጊዜ በ 90 ደቂቃ በአማካይ 0.8 ጎሎች ያስቆጥር ነበር ተጫዋቹ ከጎል ጋር የሚገናኝበትን ደቂቃ አማካይ ስናሰላው ደግሞ በየ 120 ደቂቃው ይሆናል።
ቁጥሮቹን እንደወረደ አይተን አውዱን ወደ ፕሪሚየር ሊግ አምጥተን መጠቀም አስቸጋሪ ያደርገዋል፤በተለይ በሊጎቹ መሀል ያለው ልዩነት ደግሞ ይህንን እንዳንል ዋነኛው ምክንያታችን ነው።
ከጀርመን ወደ እንግሊዝ ዝውውሩን የፈፀመው ኖርዊያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሀላንድ በደጋፊዎችም ሆነ በሚዲያ የሚጠበቅበት ነገር ከፍ ያለ ነው። ለአንዳንዶች ይህ ዝውውር በጥርጣሬ እንዲመለከቱት የሚያደርግ ያለፉ ታሪኮችም አሉ። ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ከጀርመን ወደ እንግሊዝ ከመጡ በኋላ በጀርመን የነበራቸውን ብቃት ለመድገም ሲቸገሩ ያስተዋልናቸው ተጫዋቾች አሉ።
በቅርቡ ከ ጀርመን ወደ እንግሊዝ ከመጡ በኋላ የእንግሊዝን ህይወት ለመላመድ ከተቸገሩ ተጨዋቾች መካከል የቀድሞ የሀላንድ የቡድን አጋር እና ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ማንቸስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ጄደን ሳንቾ የመጀመሪያ አመት የማንቸስተር ህይወቱ ቀላል አልሆነለትም ነበር (የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም )። ሌላኛው ደግሞ ቲሞ ቨርነር ነው፤ ቨርነር በጀርመን ቡንደስሊጋው ላይ ጎሎችን በማስቆጠር በሎቫንዶቭስኪ ብቻ ነበር የሚበለጠው ፤ ወደ ለንደን ከመጣ በኋላ ግን በጀርመን ያሳየው ብቃት ለመድገም ተቸግሮ ነበር፤ ከሀላንድ በተቃራኒ የቆመው አንድ ጥናት የሚያሳየው ከጀርመን ቡንደስሊጋ ወደ ፕሪሚየር ሊግ የሚመጡ ወጣት አጥቂዎች በዘጠና ደቂቃ የሚያገኙት ጎል ሊሆኑ የሚችሉ እድሎች(XG) ወደ 0.07 ይወርዳል ይላል። ለዚህ ዋነኛ ምክንያት በሁለቱ ሊጎች መሀል ያለው የአጨዋወት መንገድ መለያየት እንደሆነም ይነሳል። በቡንደስሊጋ አጥቂዎች ከተቃራኒ ጀርባ ሰፊ የመሮጫ ቦታዎች አላቸው፤በእንግሊዝ በተለይ እንደ ማንቸስተር ሲቲና ሊቨርፑል ያሉ ቡድኖችን ጋር ሲጫወቱ የተቀሩት አብዛኞቹ ቡድኖች ለራሳቸው ጎል ተጠግተው ቦታ ለተጋጣሚያቸው ላለመስጠት በመከልከል ለመጫወት ስለሚሞክሩ አጥቂዎች ግልፅ የሚባሉ እድሎች የሚፈጥሩበትን መንገድ እንዲቀንስ ያደርገዋል።
እንደ ሀላንድ አይነት አጥቂ ፔፕ ጓርዲዮላ የፈለገበት ምክንያት አንደኛው ወደ ራሳቸው ሜዳ ተጠግተው የሚከላከሉ ቡድኖችን ለማስከፈት መሆኑ የሚታወቅ ነው። በፕሪምየር ሊጉ ባለፉት አምስት ዓመታት ከፍፁም ቅጣት ምት ጎሎች ውጪ የመሐል አጥቂዎች በግንባራቸው ያስቆጠሯቸው ጎሎች 19% ናቸው። የሲቲ አጥቂዎች ደግሞ 17% የሚሆነውን ጎል በጭንቅላት ነው ያስቆጠሩት። ይህንን መነሻ አድርገን ከተመለከትን ምናልባትም ሀላንድ ከሱ በፊት ከጀርመን ወደ ፕሪምየር ሊጉ መጥተው በሊጉ የአጨዋወት መንገድ ምክንያት ብቃታቸውን ለማሳየት እንደተቸገሩት ሌሎች
307 viewsTadesse Abiyu, 12:24