Get Mystery Box with random crypto!

➔ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚሳተፉበት ወሳኝ ዉድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ በ18ኛዉ የአለም አትሌቲክ | ቅኝት በኳስ ሜዳ | Kegnit be Kuas Meda

➔ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚሳተፉበት ወሳኝ ዉድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ

በ18ኛዉ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን ትናንት በሴቶች 10 ሺህ ሜትር በለተሰንበት ግደይ አማካኝነት የመጀመሪያ ወርቅ ለኢትዮጵያ ያስገኙ ሲሆን ዛሬ ተጨማሪ ሜዳልያዎችን ለማግኘች ወሳኝ ዉድድሮችን ያከናውናሉ።

የማራቶን ወንዶች ቀን 10:15 ላይ
በማራቶን ዉድድሮች ስማቸዉ ከፍ ብሎ ከሚጠቀሱ ሃገራቶች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን ዛሬ በአራት አትሌቶቿ አማካኝነት ኦሪገን ላይ ደማቅ ታሪክ ለመጻፍ 10:15 ቀን ላይ ትፋለማለች።
በዚህ ዉድድር በኢትዮጵያ በኩል ሌሊሳ ዴሲሳ፣ ሞስነት ገረመዉ፣ሰይፉ ቱራ እና በታምራት ቶላ አማካኝነት ትወከላለች።

10 ሺህ ሜትር የወንዶች ፍጻሜ 5:00 ምሽት

ይህ ዉድድር በርካታ ኢትዮጵያዊያን በጉጉት የሚጠብቁትና ትናንት ምሽት ላይ በሴቶች የተፈጸመዉ አስደናቂ ገድል ዛሬም ኢትዮጵያ ሜዳልያ የምትጠብቅበት ርቀት ነዉ።

በእዚህ ርቀት ላይ ኢትዮጵያ በሪሁ አረጋዊ፣ሰለሞን ባረጋ እና ታደሠ ወርቁ ይወክሏታል።
የ10ሺህ ሜትር የወንዶች የፍጻሜ ዉድድር ዛሬ ምሽት 5:00 ላይ ይካሄዳል።

የወንዶች 1500 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ

➔ ዛሬ ለነገ አጥቢያ ከሚከናወኑ ዉድድሮች መካከል የ1500 ሜትር የወንዶች ግማሽ ፍጻሜ ዉድድር አንዱ ሲሆን በዚህ ርቀት ላይ ኢትዮጵያ በሳሙኤል ተፈራና ታደሠ ለሚ ትወከላለች።
ይህ የማጣሪያ ዉድድር ሌሊት 11:00 ላይ ይካሄዳል።

በእስካሁኑ 18ኛዉ የኦሪገን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ አንድ የወርቅ ሜዳልያ ማግኘት ችላለች።

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን....

➔ ለተጨማሪ የስፖርት መረጃዎች ወደ 6655 Ok ብለዉ ይላኩ

ቅኝት በኳስ ሜዳ