2023-04-26 15:00:04
➥ በኡናይ ኤምሪ ስር የተነቃቃው አስቶንቪላ...በቅኝት በኳስ ሜዳ ዐይን
ክፍል ሁለት
ኤምሪ ቪላ ፓርክ ከደረሰ በኋላ በአስቶንቪላ ቤት ብዙ መሻሻሎችን ያሳየ ሲሆን ከነዛ መሀል አንዱ በክፍል አንድ እንደጠቀስነው የተናጠል ተጨዋቾች ብቃት መሻሻሎች አንዱ እንደነበር አቅርበናል ።
የኡናይ ኤምሪ የ ተጨዋቾች በተናጠል ከማሻሻል በተጨማሪ እንደቡድንም ኤምሪ በቪላ ቤት ጥሩ የሚባል እድገት ቡድኑ በተለያዩ የጨዋታ ፌዞች ላይ እንዲያመጣ አድርገውታል ።
ካሉት ተጨዋቾች አንፃር ሜዳ ላይ ተለዋዋጭ የሆነ ነገር የኡናይ ኤምሪ ቡድን ቢያስመለክተንም አሰልጣኙ ግን ኳስን ተቆጣጥሮ ከኋላ መስርቶ በእርጋታ ለመውጣት እንደሚፈልግ ይናገራል "Try to keep possession. If we have the ball, I feel better than being without the ball.
ከኤምሪ መምጣት በኋላ ቪላም ኳሱን ይዘው በመቆየት እረገድ ጥሩ መሻሻሎችን አስመልክተውናል በአማካኝ ኳሱ ከእግራቸው ሳይወጣ ለ 9.19 ሰከንዶች የሚቆዩ ሲሆን በነዛ ጊዜያት ላይ 3.26 የኳስ ቅብብሎችን ያደርጋል ፣ በተጨማሪ የኡናይ ኤምሪው ቪላ በሊጉ ላይ በዝግታ የሚወጣ ቡድን የኳስ ቅብብል ፍጥነቱ ወደ ፊት በሚሄዱበት ወቅት 1.27 ሜትር/ሰከንድ ከሱ ያነሰ በዝግታ ከኋላ መስርተው የሚወጡት ሁለት ቡድኖች ብቻ ናቸው የፔፕ ጋርዲዮላው ማን.ሲቲ 1.03 የዲዘርቢው ብራይተን 1.26 ከሚኬል አርቴታው አርሰናል ጋር ደግሞ ተመሳሳይ ቁጥር አለው።
የኤምሪ ፍላጎት በተቻለ አቅም ኳሱን ይዞ በአጭር ቅብብል መውጣት ቢሆንም ተጨዋቾች ይህ በሚያደርጉ ጊዜ ምቾት የማይሰማቸው ከሆነ ይህ ለማድረግ አስቸጋሪ ያደርገዋል፤ከዚህ በተጨማሪም እንደ ተጋጣሚ የመከላከል ስትራቴጂ የኡናይ ኤምሪ ቡድን ከኋላ በተለያዩ መንገድ በመጠቀም ለመውጣት ይሞክራል ። ቪላ በመልስ ምት ለመጀመር ከሞከራቸው 218 ኳሶች ውስጥ 41.28 በመቶውን በረጅም በመምታት እንደጀመሩ ቁጥሮች ያሳያሉ።
"The first step, the easiest step, is to organise defensively. That is easier than organising offensively.ኤምሪ
ከኳስ ጋር ያለውን የቡድን አደረጃጀት ወደ ምትፈልገውን መንገድ ለማምጣት ጊዜያቶች ያስፈልጋሉ።አንፃራዊ የመከላከል አደረጃጀት ማወቀር ቀላል እንደሆነ ኤምሪን ጨምሮ የተለያዩ አሰልጣኞች ይናገራሉ ።ኤምሪም ከስቴቨን ጄራርድ ከተረከበ በኋላ ቡድኑን የመከላከል መዋቅር (ቅርፁ) ላይ ለውጥ በማድረግ የተሻለ ጠጣር የተደራጀ የመከላከል አደረጃጀት ለመፍጠር ጥረት አድርጓል። በጄራርድ ጊዜ በ 4 3 2 1 ወይም 4 3 1 2 ቅርፅ እንደ ተጋጣሚዎቹ ቢሆንም በአብዛኛው በሚድ ብሎክ በመከላከል ለመጫወት ይሞክሩ ነበር ። ኤምሪ የመከላከል ቅርፁ ላይ ለውጥ በማድረግ ወደ ላይ ተጠግተው በሚከላከሉበት ወቅት 4 4 2 የመከላከል ቅርፅ በመያዝ ተጋጣሚን ለመጫን መሀል ሜዳ ና ወደራሳቸው ግብ ክልል ሲጠጉ እንደ ተጋጣሚ የማጥቃት ቅርፅ የሚለዋወጥ ቅርፅ በመያዝ ለመከላከል ይሞክራሉ ።
በስቴቨን ጄራርድ ስርም ጥሩ ከነበሩ ነገሮች አንዱ በኡናይ ኤምሪም ስር ከቀጠሉ ነገሮች መሀል የቆመ ኳስ አጠቃቀማቸው ነው ። በተለየ የቆመ ኳስ ማጥቃት ላይ የተለያዩ መንገድ በመጠቀም ለማጥቃት ይሞክራሉ ።አጭር ኮርናዎች ፣ ኢንስዊንግ ፣ አውትኢስዊንግ በመጠቀም የመጀመሪያ ቋሚ ሁለተኛ ቋሚ ፍፁም ቅጣት ምት መምቻው ላይ ታርጌት ማኖችን በመጠቀም እድሎችን ለመጠቀም ጥረት ያደርጋሉ ።
“My dream is to win a trophy with Aston Villa,” he says. “My second dream, my objective, will be to play in Europe.” ኤምሪ
በምስል የተደገፉ ግራፎችን ከስር ይመልከቱ
ቅኝት በኳስ ሜዳ
1.1K views12:00