2023-04-01 06:34:25
ማንቸስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል ቅድመ ጨዋታ ትንታኔ በቅኝት በኳስ ሜዳ
በአገራት ጨዋታ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የሊግ ጨዋታዎች የእንግሊዝ ሁለተኛው እርከን ጨምሮ የተለያዩ አገራቶች ጨዋታ አርብ ምሽት በተደረጉ ጨዋታዎች የተጀመሩ ሲሆን ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ በተጠባቂው የማንቸስተር ሲቲ ና የሊቨርፑል ጨዋታ ዛሬ በምሳ ሰአት ጨዋታ ይመለሳል።
አሁን ላይ ሁለቱን ቡድኖች እያሰለጠኑ የሚገኙት ፔፕ ጋርዲዮላና የርገን ክሎፕ በአጠቃላይ በሁሉም ጨዋታዎች ለ 28 ጊዜ ቅዳሜ ከሰዓት 8:30 ላይ በኢቲሀድ የሚገናኙ ሲሆን ፔፕ ጋርዲዮላ በአሰልጣኝነት ቆይታው የየርገን ክሎፕን ያህል ደጋግሞ በተቃራኒ የገጠመው አሰልጣኝ የለም፤በተመሳሳይ ጀርመናዊው አሰልጣኝ እንደ ስፔናዊው አሰልጣኝ ብዙ ጊዜ የገጠመው አንድም አሰልጣኝ የለም።
ታዲያ እነዚህ ሁለት የውብ እግርኳስ አቀንቃኞች በጀርመን ቡንደስሊጋ በነበሩበት ወቅት ይሁን በእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ላይ በሚገናኙበት ወቅት ሜዳ ላይ ከሚያስመለክቱን አስደናቂ ፉክክር የተሞላበት ማራኪ እግርኳስ በዘለለ በተለይ ወደ እንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ከመጡ በኋላ ከ 2020/21 የውድድር አመት ውጪ ላለፉት አምስት አመታት እነሱ የሚያሰለጥኗቸው ቡድኖች የሊጉ አሸናፊ ለመሆን ከፍተኛ ትንቅንቅ ያደርጉ የነበሩ መሆኑን ተከትሎ ሁለቱን ቡድኞች እርስ በእርስ የሚያገናኘው መርሀግብር በእግርኳስ ቤተሰቡ ዘንዴ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።
“That is why we love the game,” ሮይኪን APRIL 10 2022 በኢትሀድ 2 ለ 2 በሆነ ውጤት የተጠናቀቀውን ከሁለቱ ቡድኞች ማራኪ ጨዋታ በኋላ ጨዋታውን የገለፀበት መንገድ ነበር።
ከአመት በኋላ በ APRIL ወር ላይ በኢትሀድ ሁለቱ ቡድኖች ቅዳሜ ምሳ ሰአት ሲገናኙ በተመሳሳይ አቋም በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ሆነው እንዳልሆነ የሚታወቅ ቢሆንም በዚህ ጨዋታ ላይ የሚመዘገብ ውጤት ለማንቸስተር ሲቲ የዋንጫው አሸናፊ ለመሆን ከአርሰናል ጋር እያደረገ ላለው ትንቅንቅ ላይ በሊቨርፑል በኩል ደግሞ በሚቀጥለው አመት የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ የሚያደርገውን ቦታ ይዘው ለማጠናቀቅ ለሚያደርጉት ጥረት ስለሚረዳቸው ጨዋታው ተጠባቂ እንዲሆን አድርጎታል።
ባለሜዳዎቹ ሲትዝኖቹ በዚህ የውድድር አመት እያስመለከቱን ያሉት አቋም ከራሳቸው ያለፉት አመታት አቋም አንፃር መውረዶች ቢታዩበትም አሁንም የዋንጫው አሸናፊ ለመሆን ከመድፈኞቹ ጋር ከፍተኛ ፉክክር እያደረጉ እንዳለ የሚታወቅ ነው ምንም እንኳን አንድ ጨዋታ ከመድፈኞቹ ያነሰ ተጫውተው በ8 ነጥብ አንሰው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ቢቀመጡም ብዙዎች አሁንም የዋንጫ አሸናፊነት ግምታቸውን ለውሀ ሰማያዊዎቹ እየሰጡ ይገኛሉ።
ብዙዎች እየገመቱት እንዳሉት የ2022/23 የውድድር አመት የዋንጫ አሸናፊ ውሀ ሰማያዊዎቹ ለመሆን ግን በሚኬል አርቴታ ስር አስደናቂ ጊዜን እያሳለፉ የሚገኙት የሊጉ መሪ የሆኑት መድፈኞቹ ውጤት መጣል መጠበቅ በተጨማሪ የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ተከታታይ ድሎች በሊጉ ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል። በዘንድሮ የውድድር አመት ማንቸስተር ሲቲዎች ተከታታይ ድሎችን ወጥ የሆነ አቋም ለማሳየት መቸገራቸው ከሚያሳዩ ነገሮች አንዱ በዚህ የውድድር ዘመን ማንቸስተር ሲቲዎች በሊጉ ላይ አንድ ጊዜ በተከታታይ አራት ጨዋታዎችን አሸንፈው አያቁም፤በአገራት ጨዋታ የሊጉ ጨዋታ ከመቋረጡ በፊት ማንቸስተር ሲቲ አንፃራዊ ወጥ ተከታታይ ድሎችን ማስመዝገብ ችለው ነበር፤በሊጉ ላይ በመጨረሻ ያደረጉዋቸው ሶስት ጨዋታዎች ያሸነፉ ሲሆን ምናልባት በዛሬው የምሳ ሰአት ጨዋታ ላይ ድል ማስመዝገብ የሚችሉ ከሆነ በ2022/23 የውድድር አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በተከታታይ አራት ጨዋታዎችን ላይ ድል ማስመዝገብ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል ።
ከሜዳቸው ውጪ የቅርብ አመታት ተቀናቃኛቸውን የሚገጥሙት የሊቨርፑል አለቃ ጀርመናዊው የርገን ክሎፕ በአሰልጣኝነት ህይወታቸው ውስጥ ማስታወስ ከማይፈልጋቸው የውድድር አመታት አንዱ የዘንድሮው ሲሆን በ2022/23 የውድድር አመት ከመጀመሩ በፊት ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት ካገኙ ቡድኖች ውስጥ አንደኛው የክሎፑ ሊቨርፑል እንደነበር ይታወሳል፤በተለይ በ2021/22 የውድድር ዘመን ላይ ቡድኑ ካሳየው አቋም አሳክቶት ከነበረው ስኬት አንፃር ከፍተኛ ግምት ማግኘቱ ብዙ አስገራሚ አልነበረም።
በተለያዩ ምክንያቶች ሊቨርፑል በዚህ የውድድር ዘመን እያስመዘገበ ያለው ውጤትና የቡድኑ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ከተጠበቀው በተቃራኒ ሆኗል ።
"At the start of this season if you had asked us what we expected in March it would have been to be coming towards the climax of the title race.
Now it is going to be difficult to win a trophy this season. It looks impossible. We will need a miracle, really. So there is a different type of motivation and it is difficult to adjust.
“We have drawn a line and know the top four is everything now. የሊቨርፑል የቀኝ መስመር ተጨዋች አርኖርድ ከቴሌግራፍ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ወቅት የተናገረው ነው።
አሁን ላይ የሊቨርፑል አሰልጣኞችን ጨምሮ ተጫዋቾቹ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ተረድተው ቡድኑ በሚቀጥለው አመት የአውሮፓ ተሳታፊ ለማድረግ የሚያስችለውን ቦታ ለማግኘት በቀሩት ጥቂት መርሀግብሮች እያሳዩ ካሉት አቋም ከፍ በማድረግ የተቻላቸው ያህል መጣር ይኖርባቸዋል።የአውሮፓ ተሳትፎ ለማግኘት የመርሲሳይዱ ቡድን ከነገ ምሳ ሰአት ጀምሮ በሚቀጥሉት ቀናቶች የተጋረጡበትን ፈተናዎች መወጣት ይጠበቅባቸዋል።
ሊቨርፑሎች በዚህ የውድድር ዘመን ከሜዳቸው ወጥተው ባደረጉዋቸው 13 ጨዋታ ላይ መሰብሰብ የቻሉት ነጥብ 12 ብቻ ነው ይህም ከሜዳቸው ወጥተው በሊጉ ላይ ትንሽ ነጥብን ከሰበሰብ ቡድኖች መሀል አድርጎታል ሊቨርፑሎችን።
የክሎፕ ልጆች ዘንድሮ ከሜዳቸው ውጪ ያላቸውን ደካማ ሪከርድ አሻሽለው ከኢቲሀድ ውጤት ይዘው ይመለሱ ይሆን?
የሲትዝኖቹ ዋነኛ ጎል አስቆጣሪ ኖርዊያዊው የፊት አጥቂ ኤርሊግ ሀላንድ በዚህ ጨዋታ ላይ በጉዳት ምክንያት የመሰለፉ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል።
ስፔናዊው የማንቸስተር ሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ካለ ዋነኛ አጥቂያቸው ሊቨርፑል ለማሸነፍ ምን አይነት መፍትሔ ይዞ ይገባ ይሆን?
ለሁሉም መልስ ለመስጠት ዛሬ ቀን 8:30 ላይ ማንቸስተር ሲቲ ከሊቨርፑል የከባድ ሚዛኑን ፍልሚያ በኢቲሀድ ያደርጋሉ።
ቅኝት በኳስ ሜዳ
1.3K views03:34