Get Mystery Box with random crypto!

ቅኝት በኳስ ሜዳ | Kegnit be Kuas Meda

የቴሌግራም ቻናል አርማ kegnitbekuasmeda — ቅኝት በኳስ ሜዳ | Kegnit be Kuas Meda
የቴሌግራም ቻናል አርማ kegnitbekuasmeda — ቅኝት በኳስ ሜዳ | Kegnit be Kuas Meda
የሰርጥ አድራሻ: @kegnitbekuasmeda
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.72K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በአፍሩ ፊልም ፕሮሞሽንና ኢንተርቴይመንት ተዘጋጅቶ በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች በቀጥታ የሚቀርቡበት ቻናል ነው።

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-03-28 00:45:05 ➥ የዋልያዎቹ የሞሮኮ ቆይታ ያለነጥብ ተጠናቋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጊኒ አቻው ሁለተኛ ሽንፈት አስተናግዶ የምድቡ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።

በዛሬው ጨዋታ አሰልጣኝ ውበቱ ከባለፈው አንፃር ሚሊዮን ሰለሞን ፣ ጋቶች ፓኖም እና ቢንያም በላይን በረመዳን የሱፍ ፣ ታፈሰ ሰለሞን እና ቸርነት ጉግሳ ተክተው ገብተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ2-0ው ሽንፈት አንፃር ሲታይ የተሻለ እንቅስቃሴ ባሳየበት ጨዋታ ግብ የተቆጠረበት በመጀመርያ ደቂቃዎች ላይ ነበር። በአራተኛው ደቂቃ ላይ ናቢ ኬይታ ከተከላካዮች ጀርባ አፈትልኮ በመውጣት አስቆጥሮ ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል።
ብዙ ሙከራ ባልነበረው ጨዋታ በ24ኛው ደቂቃ ላይ ዋልያዎቹ በሽመልስ በቀለ አማካኝነት ግብ ለማስቆጠር ተቃርበው ነበር ፤ አማካዩ አቤል ያለው ያመቻቸለት ኳስ ተጠቅሞ ነበር ወደ ግብ ለማስቆጠር የተቃረበው። ከወርቃማው ዕድል በኋላም በሠላሳ አራተኛው ደቂቃ ቸርነት ጉግሳ እና አቤል ያለው በጥሩ መናበብ ተቀባብለው የፈጠሩት ዕድል ከነዓን ማርክነህ ወደ ግብነት ቀይሮ ዋልያዎቹ አቻ መሆን ችለዋል።

ብዙም ሳይቆይ ግን በአርባ ሁለተኛው ደቂቃ ተከላካዮች በፈጠሩት የአቋቋም ስህተት ኢላይሽ ሞሪባ ግብ አስቆጥሮ ጊኒዎች መሪ መሆን ችለዋል።

አቤል ያለው በይሁን እንደሻው ለውጠው ሁለተኛውን አጋማሽ የጀመሩት ዋልያዎቹ ምንም እንኳ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ቢወስዱም በአመዛኙ የኳስ ፍሰቱ በራሳቸው የሜዳ ክፍል ነበር። በዚህ ምክንያትም በርካታ ዕድሎች መፍጠር አልቻሉም። ሆኖም በረመዳን የሱፍ እና ዑመድ ኡኩሪ አማካኝነት ሙከራ አድርገዋል።

በጨዋታው በብዛት ጥንቃቄ መርጠው በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት የሞከሩት ጊኒዎችም በመሀመድ ባዮ አደገኛ ሙከራ ካደረጉ በኋላ በሰባኛው ደቂቃ ግብ አስቆጥረው ልዩነቱ ወደ ሁለት ከፍ ማድረግ ችለዋል።

ዋልያዎቹ ከግቡ መቆጠር በኋላ ሁለት ሙከራዎች ማድረግ ችለው ነበር። በተለይም ከነዓን ማርክነህ ያደረገው ሙከራ ለግብ የቀረበ ነበር። ጨዋታው ከመጠናቀቁ ከጥቂት ሰከንዶች በፊት ግን ጥረታቸው ሰምሮ ኪቲካ ጀማ ሱሌማን ሀሚድ ያሻገረለትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ የግብ ልዩነቱን ወደ አንድ ማጥበብ ችሏል።

ጨዋታው 3-2 በሆነ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ዋልያዎቹ ተከታታይ ሽንፈት አስተናግደው በግብ ክፍያ ከማላዊ በማነስ የማጣሪያው ምድብ አራት መጨረሻ ደረጃን ይዘዋል።

ሶከር ኢትዮጵያ
1.1K views21:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 08:10:06 “የዛሬውን ቀን እንደ አንድ ብልሹ ወይም መጥፎ ቀን ነው አድርጌ የምወስደው” ውበቱ አባተ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከጨዋታ በኋላ ተከታዩን አስተያየት በስፍራው ለተገኙ የብዙሃን መገናኛ አባላት ሰጥተዋል።

ስለጨዋታው…

በጨዋታው ጥሩ ቅርፅ ላይ አልነበርንም። ተጋጣሚያችን በብዙ ነገር የበላይነቱን ወስዶብን ነበር። ቡድናችን ከዚህ ቀደም እንደነበረው አልነበረም። በተለይ በመከላከሉ ረገድ የተቀናጀን አልነበርንም ፤ በተጨማሪም ከተጋጣሚ የሚመጣውን ጫና መቋቋም አልቻልንም። በመጀመሪያው አጋማሽ ደግሞ ጥሩ ሳንሆን አንድ ጎል አስተናግደናል። በአጠቃላይ በጨዋታው ጥሩ አልነበርንም ፤ ጊኒዎች ማሸነፍ ይገባቸው ነበር።

በጨዋታው ጥሩ ስላልተንቀሳቀሱበት ምክንያት…

አንዳንድ ጊዜ እንደዛሬው መጥፎ ቀናት አሉ። እንዳልኩት ከግብ ዘቡ ውጪ በሁሉም ነገሮች በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ አልነበርንም። በጣም በኃይለኛው ነበር ጫና ሲያሳድሩብን የነበረው። ይህንን ጫና መቋቋም አልቻልንም። በቀላሉ ኳሶችን እያጣን ለእነሱ እየሰጠንም ነበር። በአጠቃላይ በመጀመሪያው አጋማሽ ቡድናችን ጥሩ አልተንቀሳቀሰም። በአንፃሩ በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ ኳሱን ለመቆጣጠር ሞክረን ነበር። ግን ደግሞ በራሳችን የቅጣት ምት በሽግግር ሁለተኛውን ጎል አስተናግደናል። እንዳልኩት የዛሬው ቀን እንደ ሌላው ቀናችን አልነበረም። በእግርኳስ እንደዚህ አይነት ቀናት አሉ ፤ አንዳንድ ቀናት መጥፎ ናቸው። ዛሬ ሁሉም ነገሮች ለጊኒዎች ነበር። ማለት የምችለው የዛሬው ቀን ጥሩ ቀናችን አልነበረም።

ስለግብ ዘቡ ሰዒድ ብቃት…

ሰዒድ ልምምድ የሌለው ግብ ጠባቂ ነው። ግን በጥሩ ብቃት ወደፊቱን አሳይቶናል። በእርሱ የዛሬ ብቃትም ደስተኛ ነኝ።

ስለመጀመሪያው አጋማሽ እንቅስቃሴ መዳከም…

አንዳንድ ቀኖች በሁሉም ነገር ትበለጣለህ። ቡድናችን ደከም ያለው ከተጋጣሚያችን አንፃር ነው ብሎ መናገር ይከብደኛል ፤ ምክንያቱም ጊኒ ጠንካራ ቡድን እንደሆነ ብናውቅም ከጊኒ የበለጠ ከብዙ ጠንካራ ቡድኖች ጋርም ተጫውተን ጥሩ ብቃት ነበረን። ዛሬ ምናልባት ከስነ-ልቦና ጋር ተያይዞ ክፍተት ካለ እናያለን። ከዚህ በተረፈ ግን ከጨዋታ አቀራረብ ጋር ተያይዞ ሌላ ለውጥ አላደረግንም። የዛሬውን ቀን እንደ አንድ ብልሹ ወይም መጥፎ ቀን ነው አርጌ የምወስደው።

የማጥቃት አጨዋወቱ ስለመዳከሙ…

ስለአጥቂዎቹ ከማውራታችን በፊት ጨዋታው ከመሰረቱ ተበላሽቶ ነበር። እርግጥ ነው የተወሰኑ ዕድሎችን አግኝተናል ፤ ግን ጥራታቸው በቂ ነው ብሎ መናገር ግን ያስቸግረኛል። ስለዚህ ከመሰረቱ ነው የተበላሸው። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ከተጫዋቾች ቅያሪ በኋላ በተወሰነ መልኩ ወደምንፈልገው መንገድ ለመመለስ ሞክረናል። በሂደት ወደ ጨዋታው ለመመለስ ሞክረናል። ከፊትም ያሉንን ተጫዋቾች ነው ለዚህ ጨዋታ ይሆናሉ ብለን ያሰብናቸውን ያስገባነው። ጎል እስካላገባም ድረስ ተቀርፏል ማለት ባልችልም ጎል ለማግባት መንገዳችን መስተካከል ነበረበት። ሌላ ጊዜ በተደራጀ ሁኔታ መጥተን ነበር የምንስተው ዛሬ ግን በዚህ ደረጃ ጥሩ አልነበርንም። ስለዚህ አጥቂዎቹን መውቀስ አልፈልግም።

ስለተጫዋች ቅያሪ…

ጋቶች ቢጫ አይቶ ነበር። ከእረፍት በፊት ሶስት ቢጫ አይተናል። ይህንን ተከትሎ ከሚጫወትበት ቦታ አንፃር ለተጨማሪ ቢጫ የሚዳረግበት ዕድል ስለሚኖር አንዳቸውን መጠበቅ ነበረብን። በተጨማሪም ኳሱን ከመቆጣጠር ጋር ተያይዞ ሁለት የተከላካይ አማካይ ኖሮ ጫናውን መቀነስ ካልቻልን ቢያንስ ኳሱን የመያዝ አቅሙን የጨመረ ሰው እዛ ጋር በማስገባት የተሻለ ለመቆጣጠር በማሰብ ነው። ይህም ስኬታማ ነበር።

ስለቀጣዩ ጨዋታ…

የምድቡ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታዎች ወሳኝ ጨዋታዎች ናቸው። ዛሬ ተሸንፈናል ግን ነገ ሌላ ቀን ነው። ቀጣዩን ጨዋታ ለማሸነፍ ዕኩል ዕድል ነው ያለን። ለጨዋታውም በተሻለ ለመዘጋጀት ሞክረን ዛሬ የነበሩንን ክፍተቶች ለማየት እንጥራለን። ከጨዋታውም የተሻለ ነጥብ ለማግኘት እንሞክራለን።

ምንጭ:- ሶከር ኢትዮጵያ



ቅኝት በኳስ ሜዳ
117 views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 02:12:23
➥ ዋልያዎቹ በጊኒ ተሸንፈዋል

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አራት 3ኛ ጨዋታ በሞሮኮ ካዛብላንካ መሐመድ አምስተኛ ስቴዲየም ጊኒ ኢትዮጵያን 2-0 በማሸነፍ የምድቡ መሪ መሆን ችላለች።

ለጊኒ የማሸነፊያ ጎሎች ፍራንሶዋ ካማኖና መሐመድ ባዮ አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ጊኒ የምድቡ መሪ ስትሆን ኢትዮጵያ ደግሞ ወደ 3ኛ ደረጃ ዝቅ ብላለች።



ቅኝት በኳስ ሜዳ
426 views23:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 23:46:33
➥ የሰሌክት ኮሌጅ የ500 ብር የሞባይል ካርድ ጥያቄ?

1. ሰሌክት ኮሌጅ በድግሪ ፕሮግራም ከሚሰጣቸው ስልጠና ቢያንስ ሁለቱን ጥቀሱ?


አሁኑኑ 6655 ላይ OK ብለው ተመዝግበው ይመልሱ!!

ማሳሰቢያ:- ለመሸለም መጀመሪያ 6655 ላይ OK ብለው መመዝገብ ከዚያ ጥያቄውን መመለስ ይጠበቅብዎታል!!

➤ ውድ የቅኝት በኳስ ሜዳ ቤተሰቦች ሊንኩን በመጫን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/kegnitbekuasmeda

ቅኝት በኳስ ሜዳ
566 views20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 19:27:08
አመሻሹን ከቅኝት በኳስ ሜዳ ጋር ያሳልፉ!!

ለ2023ቱ የአይቮሪኮስቱ የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ለመሆን የአህጉሪቱ አገራቶች በ12 ምድቦች ተከፍለው የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያከናወኑ ሲሆን በምድብ አራት ላይ የሚገኙት ሁለቱ ስደተኛ ብሔራዊ ቡድኖች ጊኒና ኢትዮጵያ የሞሮኮውን መሐመድ አምስተኛ ስቴዲየምን ተውሰው ዛሬ ምሽት 5:30 ላይ 3ኛ የምድብ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

አንጋፋው ኤፍኤም አዲስ 97.1 ደግሞ በቅኝት በኳስ ሜዳ አማካኝነት ይህንን አጓጊ ጨዋታ ከምሽቱ 4:00 ጀምሮ በአገር አቀፍ ስርጭት ከተለያዩ ሽልማቶች ጋር ጨዋታውን በቀጥታ ያስተላልፋል!!

➥ የጨዋታው የክብር ስፖንሰሮች

❶ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ(ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ)

❷. ሰሌክት ኮሌጅ(በምዝገባ ላይ)

➥ ስለዋልያዎቹ አጠቃላይ ዝግጅትና በጉዞ ወቅት ስላሳለፉት ውጣውረድ እንዲሁም ስለምሽቱ ጨዋታ ሞሮኮ ካዛብላንካ የሚገኘው የቅኝት በኳስ ሜዳው ተንታኝ ሚካኤል ለገሠ በቀጥታ ስርጭት ያስቃኘናል!!

➥ የጨዋታ ግምትዎንና ሀሳብ አስተያየትዎን ይጻፉን!!

ቅኝት በኳስ ሜዳ
894 views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 10:37:44
የቅኝት በኳስ ሜዳ ቀጥታ ስርጭት

በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አራት 3ኛ የምድብ መርሐግብር ዛሬ ምሽት 5:30 ላይ በመሐመድ አምስተኛ ስቴዲየም ጊኒ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ከምሽቱ 4:00 ጀምሮ በአገር አቀፍ ስርጭት ቅኝት በኳስ ሜዳ ፕሮግራም በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ ወደ እርስዎ እናደርሳለን።
1.1K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 18:45:22
ከነገው የጊኒ እና ኢትዮጵያ ጨዋታ አስቀድሞ የቅድመ ጨዋታ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በስብሰባው ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች ከቤኒን እንዲሁም ኮሚሽነር ከቡርኪና ፋሶ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በጨዋታው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቢጫ ማልያ ፥ ቀይ ቁምጣ እና ቢጫ ካሶተኒ ለብሶ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል። ተጋጣሚያችን ጊኒ ደግሞ ቀይ ማልያ ፣ ቢጫ ቁምጣ እና አረንጓዴ ካሶተኒ በመልበስ ወደ ሜዳ ይገባል።

ጨዋታው ከምሽቱ 5፡30 ላይ ካዛብላንካ በሚገኘው መሐመድ አምስተኛ ስታዲየም ይደረጋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን
1.2K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 18:26:13 አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ ሽመልስ በቀለ ቅድመ ጨዋታ መግለጫ ሰጥተዋል

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ምሽት 5:30 ላይ ከጊኒ አቻው ጋር በካዛብላንካ መሐመድ አምስተኛ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል። ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎም አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ ሽመልስ በቀለ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

" ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገን ዝግጅት ስናደርግ ቆይተናል። የአቋም መፈተሻ ጨዋታም ከሩዋንዳ ጋር አድርገናል። አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾች በስብስባችን ይዘናል። በጉዳት ያጣናቸው ተጫዋቾች ቢኖሩም የተተኩት ተጫዋቾች እያሳዩት ያለው ነገር ጥሩ ነው። በትናንቱ ልምምድ ተጫዋቾቼ ለጨዋታው ዝግጁ እንደሆኑ ተመልክቻለሁ። " በማለት መግለጫውን የጀመሩት አሰልጣኝ ውበቱ ተጋጣሚያቸው ጊኒን ለመገምገም እንደሞከሩ የገለፁት ሲሆን በምድቡ ቀላል የሚባል ጨዋታ እንደሌለ በመጠቆም ለሁሉም ቡድን ወሳኝ የሆነ ወቅት ላይ የምንገኝ በመሆኑ ከወሳኞቹ ጨዋታዎች ውጤት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ቡድኑ በወጥነት ለረጅም ጊዜያት ጥሩ ነገር እያሳየ ነው ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ " የምዕራብ እና የሰሜን አፍሪካ ቡድኖችን ስንገጥም ከዚህ ቀደም የነበረንን ሪከርድ ለማሻሻል እየሞከርን ነው። በዚህ ማጣርያ ውድድር በማላዊ 2ለ1 ስንሸነፍ የነበረን እንቅስቃሴ ግብፅን ስናሸንፍ ከነበረው ብዙ የተለየ አልነበረም። በአጠቃላይ ግን ቡድኑ ጥሩ መንፈስ ላይ ነው ያለው።" ብለዋል።

ከማጥቃት ጋር በተያያዘ ለተነሳላቸው ጥያቄ የአጥቂ ችግር በአንድ ጊዜ የሚፈታ እንዳልሆነ ገልፀው እንደ ቡድን ለመፍታት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

አምበሉ ሽመልስ በቀለ በበኩሉ ስብስቡ ከበፊቱ በተሻለ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አውስቶ እዚህ የተገኙት ነጥብ ለማሳካት እንደሆነ በመጠቆም በአሠልጣኞች ቡድኑ እና የቡድን አጋሮቹ ሙሉ እምነት እንዳለው በመጠቆም ጨዋታውን በጥሩ ሁኔታ እየተጠባበቁ እንደሚገኝ ተናግሯል። አማካዩ በተጋጣሚ ቡድን ውስጥ ስለሚገኘው ናቢ ኬታ ተጠይቆም ለማንም የተለየ ትኩረት እንደማያደርጉና አንድ ተጫዋች ብቻ ሳይሆን እንደ ቡድን ግብፅን የመሳሰሉ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድኖች ገጥመው እንደነበር በማንሳት ከጨዋታው የተሻለ ነገር ለማምጣት እየተዘጋጁ እንደሆነ አምላክቷል።

በጨዋታው ላይ በኢትዮጵያ በኩል በሁለት ቢጫ ቅጣት ምክንያት ከሚያመልጠው ምኞት ደበበ ውጪ ሁሉም ከጉዳት እና ቅጣት ነፃ እንደሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን
1.1K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 10:14:06 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ የተባረከ የረመዳን ፆም ይሁንላችሁ!
ረመዳን ከሪም!
1.0K views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 09:59:03
"ቅኝት በኳስ ሜዳ"

ጊኒ ከኢትዮጵያ

አፍሩ ፊልም ፕሮሞሽንና ኢንተርቴይመንት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፕሬሽን ጋር በመተባበር በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ የሚያደርሱት "ቅኝት በኳስ ሜዳ" የቀጥታ የእግርኳስ ስርጭት ፕሮግራም አርብ ምሽት 5:30 ላይ በመሐመድ 5ኛ ስቴዲየም በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጊኒ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ ከምሽቱ 4:00 ጀምሮ በአገር አቀፍ ስርጭት በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ ከተለያዩ ሽልማቶች ጋር ወደ እርስዎ እናደርሳለን።

➥ ጊኒ ከኢትዮጵያ
➥ መሐመድ 5ኛ
➥ ከ4:00 ጀምሮ
➥ በኤፍኤም አዲስ 97.1
➥ በቅኝት በኳስ ሜዳ
➥ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ

አርብ ምሽት ከ4:00 ጀምሮ በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ ይጠብቁን!!

ቅኝት በኳስ ሜዳ
1.0K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ