➪ የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ ውድድር የፊታች እሁድ ይካሄዳል
የ2015 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድር መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።
ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው “ቦታዬ ፣ መብቴ ፣ ድምፄ” በሚል መሪ ቃል ይከናወናል፡፡
• በዚህ ውድድር 15,000 ተሳታፊዎች ይገኙበታል፡፡
• ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ በሚገኙ የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች እንዲሁም በአሞሌ ሞባይል መተግበሪያ ለአንድ ተሳታፊ 450 ብር በመክፈል መመዝገብ ይቻላል፡፡
• ክፍያ ካጠናቀቅሽ በኃላ ምዝገባ የሚካሄደው በቀላሉ ካለሽበት ቦታ ሆነሽ በታላቁ ሩጫ የመመዝገቢያ telegram Bot ነው። @GREATETHIOPIANRUNBOT
• ተወዳዳሪዎች ሲመዘገቡም 20ኛ ዙር ውድድር የክብር አጋር ሆነው ከተቀላቀሉት ስንቅ ማልት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ዳሸን ባንክ እና ኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የተለያዩ ስጦታዎችን የሚያገኙ ይሆናል፡፡
• አትሌት መሰረት ደፋር ከ35 ደቂቃ በታች ለሚገቡ ተሳተፊዎች የሰርተፊኬት ማበረታቻ የምታበረክት ይሆናል፡፡
• የዘንድሮ ውድድር ከጤና ሯጮችም በተጨማሪ የሴት አትሌቶች፤ ተምሳሌት ሴቶች፤ የአምባሳደሮችና የአካል ጉዳተኞች ውድድርን ያካተተ ነው፡፡
• ዘንድሮ ከቲሸርትና ከሜዳሊያ በተጨማሪ ስጦታ በሽ፤ ቦርሳ፤ሎሽን፤ ባንዳና ከቲሸርቱ ጋር አብረው የሚሰጡ ይሆናል፡፡
• ለበለጠ መረጃ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ 0116635757 ላይ መደወል ይቻላል፡፡
ቅኝት በኳስ ሜዳ