Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹 I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia2
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.35K
የሰርጥ መግለጫ

Fan page of inspire ethiopia

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-10-27 19:00:30 ከሁሉ ፍቅር ይቀድማል!

ደስተኛ መሆን ትፈልጋለህ? ፍቅርን ፍጠር አካባቢህን በሙሉ በፍቅር ሙላው ለምታገኘው ሰው ሁሉ ሰላምን ስጥ ከልብህ መውደድን ተማር ! ከልብህ መስጠትን ጀምር ! ምንም ሳትጠብቅ ሁኔታዎችን ሳታይ ካንተ የሚጠበቀውን ብቻ ፈፅም ያኔ ህይወት መልካም ነገሯን በሙሉ ወደ አንተ ትገለብጣለች ደስታህ ወደር አይኖረውም ፤ ፍርሀት ጥርግ ብሎ ከውስጥህ ይጠፋል ፤  እመነኝ በፍቅር ከሆነ ሁሉን ነገር ታሸንፋለህ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
4.6K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 17:54:09 ሰዎች እንዳያደክሙህ!

በጣም ጠንካራ እና ጎበዝ ስትሆን ሰዎች አስተያየት ያበዙብሀል እንደዚህ እኮ ብትጨምር ፣ ይሄንን እኮ ብታደርግበት ኖሮ እኮ በጣም ጥሩ ትሆን ነበር ግን አጠፋህ ይሉሀል የሰራሀቸውን ያደረግሀቸውን ትላልቅ ስራዎችህን ውርድ ያደርጉብሀል ግን የሚገርመው አንተ የለፋኸውን አንዲቷን ልፋት እንኳን አልለፉም ፣ ያደረግኸውን እንዲቷን ጥረት አልጣሩም ፣ በፍፁም ያንተን ድል አላገኙም ዝም ብለው ተቀምጠው ግን አንተን ይተቻሉ ያኔ አንተም ውስጥህ ይሸበራል አልችልም እንዴ  ፣ ምንም ነገር አልሰራውም እንዴ ? ምንም አልችልም እንዴ ያስብሉሀል ያገኘኸውን ድል ፣ ያሸነፍከውን ሁሉ ያስረሱሀል ፤ ስለዚህ አስተውል በፍፁም ላትሰማቸው ለራስህ ቃል ግባ መጨመር ያለብህን ልትጨምር ስትነሳ በፍፁም ያለህን እንዳትረሳ ፤ ብዙ እኮ ለፍተህበታል ጀግና እኮ ነህ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
5.4K views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 08:41:23 መጠየቅ አትፍራ!

ህልመኛ መሆን አለብህ ያለበለዚያ ህልም ያለው አገልጋይ ነው የምትሆነው። ፈጣሪህ ውዱን ስጦታ በነፃ ሰጥቶሀል፤ ጤናህን ቤተሰቦችህን የምትወዳቸውን ሰዎች ሁሉ በነፃ ነው የሰጠህ፤ ሀብት ስኬት ደስታ ብትጠይቀው ለሱ ርካሽ ነው። ወዳጄ መጠየቅ መመኘት አትፍራ፤ ምንም የማይሳነው አምላክ ከጎንህ ነው!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
7.6K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 18:38:07 ለምንወደው ሁሉ!

አንድ ሰው "በጣም መብላት የምወዳት ብስኩት አለች ፤ እና ደግሞ ብዙ ግዜ አሳ ለማጥመድ መውጣት ያስደስተኛል ነገር ግን አሳ ለማጥመድ በምሄድበት ግዜ ለአሳዎቹ ይዤ የምሄደው እነሱ መመገብ የሚወዱትን ነው እንጂ እኔ የምወደውን ብስኩት አይደለም" ይላል ከአንድ ሰው የምንፈልገውን ጥሩ የፍቅር ግንኙነትም ሆነ ጥሩ ጓደኝነት ለማግኘት እኛ የምንወደውን ወይ ያስፈልገናል ብለን የምናስበውን ሳይሆን እነሱ የሚወዱትን እና የሚያስፈልጋቸውን ነው ልንሰጣቸው የሚገባው ፤ ያኔ የተሳካ ህይወት እንደምንመሰርት ምንም ጥርጥር የለውም !

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
8.0K views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 08:41:55 ያንተ ጥንካሬ!

አይንህ ወደ ብርሀኑ አቅጣጫ ከሆነ ሊጋርድህ የሚፈልግ ጥላ ከኋላህ ያርፋል፤ ሀሳብህ መልካም ነገር ላይ ብቻ ካረፈ መጥፎ ነገሮች አንተ ጋር ሳይደርሱ ከጀርባህ ይወድቃሉ።

ጨለማው ላይ ማፍጠጥ ብርሀን አይሰጥም፤  ድክመትህን ብቻ አጉልተህ አትይ!  አንተ ባትሆን የማታልፋቸው ብዙ ችግሮች ነበሩ፤ አንተ ግን ለዛሬ ደርሰሀል፤ ወዳጄ አሁን ያለህ ጥንካሬ የምታስበውን ሁሉ ለማሳካት ከበቂ በላይ ነው!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
7.9K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 19:50:38 ምንም አልጎደለህም!

እጅግ ውድ የሆነ መኪና ቢኖርህና ከፊቱ ሁለት ፈረሶች በገመድ አስረህ ብታስጎትተው መኪናው ሊንቀሳቀስ ይችላል፤ ግን የፈለክበት አያደርስህም! ቁልፉን አስገብተህ ብታስነሳው ግን የምትፈልገው ቦታ በፈለከው ፍጥነት ያደርስሀል።

መኪናው አይምሮህ ነው፤ ቁልፉ ደግሞ አመለካከትህ ነው። ወዳጄ ምንም የጎደለህ ነገር የለም የፈለክበት መድረስ ትችላለህ! ፈጣሪ የሰጠህን ካልተጠቀምክበት ግን ውዱ መኪናህን በፈረስ እየጎተትከው ነው።

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.9K views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 17:51:42 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ! መልካም በዓል
1.9K views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 12:24:16 ራስን መቀየር!

የማትቆጣጠራቸው ነገሮች ላይ ጊዜህን ልታጥፋ ስትል ንፋስ ልትጨብጥ እየሞከርክ እንደሆነ አስብ፤ የሰዎችን ፀባይ፣ የሀገርህን ሁኔታ፣ የኑሮ ውድነቱን፣ የአለቃህን ወይ የአሰሪዎችህን ፀባይ መቀየር አትችልም!

ግን እንደምትችለው እርግጠኛ የምትሆንበት አንድ ነገር አለ...ራስህን መቀየር ግን ትችላለህ! እመነኝ ወዳጄ አንተ ከተቀየርክ ነገሮች ሁሉ ይቀየራሉ፤ ካንተ የሚጠበቀው ለራሴ ያለሁት ራሴ ነኝ ብሎ ማመን እና የተግባር ሰው መሆን ነው።

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.9K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 10:40:53 ሁሉም ለበጎ ነው!

ፈጣሪ በነገሮች በሁኔታዎች ነው የሚናገርህ፤ በጆሮህ መጥቶ እንዲህ አድርግ አይልህም፤ በህይወት እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ለምክንያት ነው።

ንቁ ሆነህ በህይወትህ የሚሆነውን ሁሉ ማስተዋል አለብህ! ደግሞ አትርሳ ተማሪ ካለ አስተማሪ የትም ቦታ አለ።

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
3.1K views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 21:04:21 አሸናፊ ነህ!

የጀመርከውን ለማቆም ብዙ ምክንያቶችና ብዙ ፈተናዎች እየገጠሙህ ይሆናል ግን ወዳጄ እልኸኛ መሆን አለብህ! የምፈልገውን ሳላሳካ፣ ለምወዳቸው ሳልደርስ ጥረቴን አላቆምም ማለት አለብህ! አሸናፊ ማለት የማይወድቅ አይደለም ግን ተስፋ ቆርጦ የማያቆም ነው። አንተ ደግሞ አሸናፊ ነህ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.7K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ