Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹 I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia2
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.35K
የሰርጥ መግለጫ

Fan page of inspire ethiopia

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-09-01 19:08:09 ልማድ !

ህይወትህን የሚቀይረው ህልምህን ወይ አላማህን ማወቅህ ሳይሆን በየቀኑ የምታደርገው ልማድህ ነው ። ዛሬ ቀንህን እያሳለፍክ ያለኸው ካስቀመጥከው ህልም ጋር በሚገናኝ ነገር ነው ? ትናንትስ ? ነገስ ልታደርግ ነው ያሰብከው ? ምን ያህልስ ከህልምህ ጋር ይገናኛል?

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
2.7K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:30:12 ልክ ነህ!

የቆመ ሰዓት እንኳን በቀን ሁለት ጊዜ ልክ ይሆናል፤ አንተም አንዳንድ ስህተት የመሰለህ ጉዳይ ልክ እንደሆንክ የምታስበው ጊዜው ካለፈ በኋላ ነው። የሚቆጨኝ ነገር የለም ምክንያቱም ያበላሸሁትን ለማስተካከል ዕድሜና ጤና ይሰጠኛል በል! በቁጭት እና ራስን በመውቀስ የሚባክን ጊዜ የለም! አሁንን መኖር ከዛ የተሰጠህን የቤተሰብ የኑሮ ፀጋ ሁሉ ማጣጣም ጀምር፤ ጊዜው እንደሆነ መሄዱ አይቀር።

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
866 views10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:56:22 አስብበት!

ስሜትህን፣ ፍላጎትህን፣ አላማህንና ጊዜህን ራስህ ካልተቆጣጠርከው ምንም እንዳትጠራጠር ሌሎች ይቆጣጠሩታል! ይሄ እንዲሆን እንደማትፈቅድ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ፤ ያለህበት ሁኔታ በማን ቁጥጥር ስር ነው? አስብበት ወዳጄ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.9K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:08:33 ወስን!

ህይወትህን እስከመጨረሻው የሚቀይረው አንድ ውሳኔ ሊሆን ይችላል! በቃ ህይወቴን የምቀይረው እኔ ነኝ! ማንንም አልጠብቅም ከፈጣሪ ጋር ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ በል! ያኔ አይምሮህ ራሱ የምትፈልገውን እንታሳካ ክፍት ይሆናል! ወዳጄ ወስንና ወደ ተግባር ግባ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
4.1K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:07:22 ወሳኙ መምህር!

የህይወትህ ወሳኝ መምህር ፈጣሪ ነው፤ መምህር ደግሞ ማስተማር መፈተን ከዛ መሸለም ልማዱ ነው።ከበድ ያለ ችግር መጣ ማለት ወይ አድገሀል ወይ አስቸግረሀል፤ ወይ ሊያስተምርህ ነው ወይ ፈትኖ ሊሸልምህ ነው፤ እርግጠኛ መሆን ያለብህ ግን ፈጣሪ ልጁን ሊጎዳ ምንም ነገር አያመጣም! ተስፋ መቁረጥ የለም ጠንክረህ ታልፈዋለህ

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
4.1K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:06:30 ከማንነትህ ጋር መተዋወቅ!

ችግሮች ሲገጥሙህ ምን ሊያስተምሩህ እንደመጡ ማወቅ አለብህ፤ ለምን ወደ ህይወትህ እንደመጡ ሳታውቅ ከቀረህ ግን ደጋግመው መምጣታቸው አይቀርም!

ከማንነትህ ጋር የምትተዋወቀው ችግር ሲገጥምህ ነው፤ አንዳንዴ ፈጣሪ በምን መንገድ ሊያስተምርህ ወይ ታላቅ ሊያደርግህ እንዳሰበ አታውቅም። ሁኔታዎች ላያስደስቱህ ይችላሉ ግን እመነኝ ወዳጄ እንደዚህ አይቀጥሉም!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
4.0K views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:25:36 ምንም ነገር አያቆምህም!

ሁላችንም የምንኖርለትን ምክንያት እስክናውቀው ድረስ ሙሉ አቅማችንን አንጠቀምም፤ ስለዚህ ሌሎች ድክመታችንን አይተው እሱ እኮ ሰነፍ ነው ይሉናል፤ እሷ እኮ ግድየለሽ ናት ይሉናል።

ወዳጄ የምትኖርለትን ምክንያት ሳታውቀው ቀርተህ እንጂ ከማንም አንሰህ ወይ ሰነፍ ሆነህ ተፈጥረህ አይደለም! እህቴ የሚያበረታሽን ጉልበት የሚሰጥሽን ምክንያት አተሽ እንጂ የሚገርም አቅም ነው ያለሽ! አላማህን ያወከው እለት ምንም ነገር አያቆምህም!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
5.1K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 08:56:27 አሁን ሞክር!

ዕድሜህ ካለፈ በኋላ ያሳለፍከውን መለስ ብለህ ስታስብ ካደረካቸው ይበልጥ ያላደረካቸው ይቆጩሀል፣ ምናለ ሞክሬው ቢሆን አድርጌው ቢሆን ኖሮ ትላለህ፤ እንዳትል ግን አሁን የምትቸለውን ሁሉ ሞክር እና ማን እንደሆንክ ለራስ አሳየው! አለዛ ቁጭት ነው ትርፍህ።

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
5.4K views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 13:37:32 ራስን መሆን!
6.8K views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:26:24 ከባዱን ምረጥ !

ምርጫህ ሁሌም ከባዱን ስራ መሥራት ይሁን ምክንያቱም ከባዱን ስራ ከሰራህ ከባድ ሰው ትሆናለህ ቀላሉንም ከመረጥክ በምርጫህ ልክ ታገኛለህ ።

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
6.2K views05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ