Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹 I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia2
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.35K
የሰርጥ መግለጫ

Fan page of inspire ethiopia

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-08-26 18:25:36 አይምሮን ማሳመን!

እግርህ በተግባር እንዲራመድ አይምሮህና ልብህ ቀድሞ በሀሳብ መራመድ አለበት፤ ሁሉ ነገርህን የሚያዘው አይምሮህ ነው። ራስህን መቀየር ወይ መወሰን ስትፈልግ አስቀድመህ ለአይምሮህ ስትቀየር የሚኖርህን ደስታ ደጋግመህ አስበው ንገረው፤ ከዛ የሆነ ጊዜ አንተ ራሱ ሳታውቀው ቆራጥ ሆነሀል፣ ጠንካራ ሆነሀል ምክንያቱም አይምሮህ ካመነ የማይቀየር ነገር የለም!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
6.8K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 18:56:48 ህይወት !

በህይወትህ ውስጥ አንዳንዴ በጣም የፈለግከው ነገር ልክ መፈለግ ባቆምክበት ቅፅበት ወዳንተ ይመጣል። እስቲ ፍለጋህን አቁመህ ወዳንተ እየመጣ ከሆነ ቆም ብለህ ተመልከት !

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
7.3K views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 15:17:02 ዛሬን መጠቀም!

ትናንት ታሪክ ነው፤ ነገ ደግሞ እንቆቅልሽ ነው፤ ዛሬ ግን የፈጣሪ ስጦታ ነው! ስጦታህን መጠቀምም ማባከንም ያንተ ምርጫ ነው።

ፈጣሪን አመስግነህ፤ ስለሚያስደስትህ ነገር እያሰብክ ስሜትህን ቀይረህ የሚጠበቅብህን ሁሉ ካደረክ መቼም አይቆጭህም ምክንያቱም ታላቅነት የሚገነባው ዛሬን በመጠቀም ነው።

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
8.4K views12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 15:16:28 ይቅርታ !

ይቅርታ ለሰው ስታደርግ ለሰውየው ጥቅም ወይ እንዳይደብረው የምታሰገው ውለታ ሳይሆን ለራስህ የምትሰጠው ውድ ስጦታ ነው ፤ በልብህ ውስጥ ያሰርካትን ትንሽዬ የነፃነት ወፍ ነፃ የምታወጣበት ቁልፍ ነው ።

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
7.7K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 18:49:24 ተዓምር!

ተኝተህ ማደርህ እኮ ተዓምር ነው ምክንያቱም  ዛሬን ማየት ያልቻሉ ብዙ ናቸው፤ መተንፈስ እኮ ተዓምር ነው ምክንያቱም ከማሽን ውጪ የማይተነፍሱ ሞልተዋል። የሚያስጨንቅህ ነገሮች በሞት ፊት ተራ ናቸው!

ከጎደለህ ይልቅ የተሰጠህን ተመልከት፤ ከስንቱ ችግር አልፈሀል፤ አበቃልኝ ብለህ ተስፋ የቆረጥክባቸው ጊዜያት እንደ ቀልድ አልፈዋል እኮ፤ ወዳጄ አላስተዋልከውም እንጂ ህይወትህ የተሞላው በተዓምር ነው።

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
8.3K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 19:52:25 @Inspire_Ethiopia2
15.1K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 19:39:07 ምስጋና!

አንተ ደስተኛ እንድትሆን የግድ የምትፈልገው ሁሉ መሳካት የለበትም። ቀንህን ማሳመር ከፈለክ እጅህ ላይ ስላለው ነገር በጎ ነገር አስብ፤ አቅም አለህ፣ ወጣት ነህ፣ ብዙ ነገር መቀየር ትችላለህ ከሁሉ በላይ ደግሞ እየተነፈስክ ነው!

በዚህ አለም አንዳንድ ነገሮች የጎደሉህ ቀን ነው እንደነበሩህ ራሱ የምታውቀው፤ ለምሳሌ ስትታመም ነው ለካ ጤነኛ መሆን ወሳኝ ነገር እንደሆነ የሚገባህ። ወዳጄ የተሰጠህን ተመልከትና ህይወትህን አሳምረው!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
13.1K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 11:33:46 አመለካከት !

በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብትሆን አመለካከትህን በመቀየር ማሸነፍ ትችላለህ ። እስቲ ራስህን ጠይቅ ችግሩ ከባድ ሆኖ ነው ወይስ አንተ በምን አይን አይተኸው ነው ? አንተ የገባህበት ሁኔታ ውስጥ የገቡ ያሸነፉ አሉ እነሱ እንዴት አለፉ ? አንተም ማለፍ የምትችል መሆንህን ማረጋገጫ ነው ።

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
12.6K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 09:36:13 ከባዱን አሁን ስራ!

ታሪክ በአንድ ጀምበር አይሰራም! ሁሌም የማይቆም ጥረት ማድረግ አለብህ፤ የምትፈልጋቸው ነገሮች በነፃ አይገኙም ዋጋ ያስከፍላሉ ዋጋ ለመክፈል ራስህን አዘጋጅ! ወዳጄ አሁን ከባዱን ካደረክ ህይወት ቀላል ትሆናለች፤ ቀላሉን ካደረክ ግን ህይወት ትከብድሀለች!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
11.8K views06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 09:35:03 ነገ ያንተ ነው!

የምትሰምጠው ውሀ ውስጥ ስትገባ አይደለም፤ ውሀ ውስጥ ገብተህ ከቀረህ ነው። ህይወትህ የሚበላሸው ስትሳሳት አይደለም ለማስተካከል ምንም ካላደረክ ነው፤ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ተስፋ ቆርጠህ ዛሬን ካላቆምክ ነገ ያንተ ነው!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
10.5K views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ