Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹 I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia2
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.35K
የሰርጥ መግለጫ

Fan page of inspire ethiopia

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-11-12 11:41:45 እውነተኛ ለውጥ!

ያንተ ለውጥ በአጭር ጊዜ ሰዎችን ሁሉ እንዲያስገርም አጠብቅ፤ እውነተኛ ለውጥ ጊዜ ይጠይቃል፣ የማይቆም ጥረት ይጠይቃል፣ ያንተን ትዕግስት ይጠይቃል፤ ፍራንክ ኦሽን "ድምፅህን አጥፍተህ ጠንክረህ ስትሰራ ስኬትህ በራሱ ጊዜ ጮሆ ይናገራል" ይለናል። ወዳጄ በትዕግሥት ተሞልተህ ለውጥህን ቀጥል!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
3.1K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 18:50:40 መገፋትህን አትጥላው!

"ሰዎች አይፈልጉኝም፣ ተገፍቻለው፣ ስራ አልሳካ አለኝ፣ መለወጥ ከበደኝ" አላቸው። "የኔ ልጅ እንደውም ጥሩ ገፊ አላገኘህም እንጂ በደምብ ትለወጥ ነበር" አሉት።

ውስጥህ ጥንካሬ ካለ የምታጎነብሰው ለጊዜው ነው፤ ፀጥ ብለህ አንገትህን ደፍተህ ትለወጣለህ ስኬትህ ጮሆ ይናገራል። የናቁህ ሰዎች እሳቱ ማንነትህን ቆስቁሰው እያወጡት ነው! መገፋትህን አትጥላው ወዳጄ!

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.2K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 10:32:04 ምን ያህል አትችልም የሚሉ ቃላትን ተሸክመሀል ?

ይቅርብህ ፣ አይሆንም ፣ አትችለውም ፣ አይሳካልህም ፣ አትመጥኚም፣  አይገባሸም ፣ ላንቺ አይሆንም የሚሉ ቃላቶች ምን ያህል ከመንገድሽ መድረስ ከተመኘሽበት አሽሽተውሻል? ዛሬ አለም ያደነቃቸው ጀግንነታቸው ያስደነገጠን ምን አይነት ጥበብ ነው ብለን የተደመምንባቸው ሰዎች ልክ ሲጀምሩ ሁሉም ተቃውሟቸው እንደነበርስ ምን ያህል ሰምተናል?

ስኬት ማደግ አዲስ መንገድ መሞከር ለብዙዎች እብደት ነው ስለዚህ የማይሆን ነገር እንደሆነ ይነግሩናል ሆነው ስላላዩት ማሳካት ስላልቻሉ ሌላው እንዲያሳካው አይፈቅዱም ! ምክንያቱም ማንም ሰው መበለጥ አይፈልግም ስለዚህ እንዳትበልጣቸው እንደተሸነፍክ ይነግሩሀል ፣ እንዳታሸንፋቸው የተሸነፍክ እንደሆንክ አድርገው ከመንገድህ ያቆሙሃል ።

ወገኔ ብልጥ ሁን እንጂ ንቃ ራስህን እየው ካንተ በላይ አንተን የሚያውቅህ ማነው? ካንተ በላይ ችሎታህን ሊነግርህ የሚችለው ማነው? ለምን ራስህን ማንነትህን አቅምህን አሳልፈህ ትሰጣለህ? ትችላለህ ትችያለሽ!

ደስ የሚል ቀን ተመኘን
@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምረጥ ጓደኛ
1.7K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 10:12:07 የinspire ethiopia 2ኛው የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
1.6K views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 13:10:24 አሁን ወስን!

እንዲህ ቢሆን ኖሮ እያልክ ስለትላንት ማሰቡን አቁም! አሁን ወስን! አንድ ውሳኔ ህይወትህን እስከመጨረሻው ሊቀይረው ይችላል! ከዚህ ቅፅበት ጀምሮ የምችለውን ሁሉ አደርጋለው በልና ወስን!

ቆራጥ ካልሆንክ ማንም አይፈልግህም! ለራስህ አቶን ለምትወዳቸው አቶን! የሚያመነታ ሰው ሲባክን ይኖራል! ቆራጥ መሆን አለብህ የምትፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ ከፍርሀትህ ጀርባ ቁጭ ብለዋል!

ወደኋላ ተመልሰህ ምንም ነገር መቀየር አትችልም፤ ከአሁን ብትጀምር ግን አጨራረስህን ማሳመር ትችላለህ፤ ከዚህ የተሻለ ሰው መሆን ይገባሀል! ወስን ወዳጄ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
3.6K views10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 07:19:19 ይበቃል!

በቃኝ ማለት መጀመር አለብን ! ከዛሬ ጀምሮ መቸገር ፣ መፍራት ፣ ማጣት ፣ መጨነቅ በህይወቴ ውስጥ አይኖሩም የሚገባኝን ጥሩ ህይወት መኖር እጀምራለው ! ከዚህ በኋላ መቆም የሚባል ነገር የለም ፣ ወደፊት እራመዳለው መሰናክሎቼን በሙሉ አውጥቼ እጥላቸዋለው እጅ አልሰጥም ማለት መጀመር አለብን እስከመቼ የማትፈልጊውን ህይወት ትመሪያለሽ? ስለዚህ መንገድሽን አስተካክዪ ራስሽን ፈትሺ እናም በቃኝ በይ እና አዲስ ህይወት ጀምሪ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
760 views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 20:17:19 መለወጥ አለብህ!

ህልምህን ከመኖር በላይ የአይምሮ ሰላም የሚሰጥህ ነገር የለም፤ ወደምትፈልገው መንገድ መጓዝ የምትጀምረው መቼ ነው? ሰው እንዴት ወደ ምስራቅ መጓዝ እያለበት ወደ ምዕራብ ይሄዳል? ከማይጠቅሙህ ሰዎች ጋር መሆን የምታቆመው መቼ ነው? ጊዜህን በዋዛ ፈዛዛ የሚያባክኑ ነገሮችን ከህይወትህ ቆርጠህ የምታወጣው መቼ ነው?

ስኬትና የህይወት እርካታ ዋጋ ያስከፍላሉ፤ በነፃ አይገኙም። አንተ ደግሞ እንኳን ለሚጠቅምህ ለማይጠቅምህም ነገር ዋጋ ከፍለህ ታውቃለህ፤ አሁን ሰዓቱ ራስህን እስከ መጨረሻው ስለ መቀየር የምናወራበት ነው! ወዳጄ አሁን የሚያስደስትህን ሰው ስለመሆን በማሰብ ጀምር፤ ከዛ ወደ ተግባር ግባ! አለቀ ዋጋ መክፈል ይሄ ነው! መለወጥ አለብህ! ቆሞ መቅረት የለም!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.6K views17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 20:15:54 የመፍትሄ ሰው ሁን !

ማደግ ከፈለግህ የመፍትሄ ሰው ሁን "መፍትሄ ወዳለበት ገንዘብ ይፈሳል " ስለዚህ ምንም የምሰራው አጣው ካልክ ውጣ እና ዞር ዞር ብለህ አካባቢህን ቃኝ ምን ምን የጎደለ ነገር አለው? ሰዎች ምን አስፈልጎቸዎል? በዚህ ምድር ላይ ያለ ስራ ሁሉ የተፈጠረው መፍትሄ ለመስጠት ነው ህክምናው፣ ትምህርቱ ፣ ምግብ ቤቱ ፣ ልብስ ሰፊው ፣ ሊስትሮው ሁሉም የሰዎችን ችግር በመቅረፋቸው ሰው ወደ እነርሱ እየሄደ ገንዘቡን ያፈሳል ! እድለኛነታችን የእኛ ሀገር ብዙ መፍትሄ የሚፈልጉ ጥያቄዎች መኖራቸው ነው ስለዚህ የመፍትሄ ሰው እንሁን! ያኔ ከእኛም ተርፈን ለብዙው እንሆናለን!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
2.6K views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 15:57:41 መፍራት የለም!

በህይወት አስጨናቂ ወቅቶች የሚመጡት ለአጭር ጊዜ ነው ግን የዘላለም ያህል ይረዝማሉ፤ ያንተ ማንነት ነጥሮ የሚወጣው በዚህ ከባድ ወቅት ነው፤ ጀግና ታላቅነቱ የሚታየው ከብርቱ ጠላት ጋር ሲፋለም ነው!

የገጠመህ ከባድ ችግር ከኋላው የፈጣሪን ስጦታ የያዘ ሊሆን ይችላል፤ አንተ አላየኸውም ማለት ደግሞ የለም ማለት አይደለም! ፈርተህ የትም አትደርስም የምትችለውን እያረክ መጋፈጥ አለብህ ወዳጄ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.6K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 13:13:02 በሌሎች መደሰት

"ብዙ ሺ ሻማዎች ከአንድ ሻማ ብቻ እሳት አግኝተው ሊበሩ ይችላሉ፤ እነሱን ስላበራ የሻማው እድሜ አያጥርም። ደስታህን ለሌሎች ስላካፈልክ በፍፁም አያልቅብህም" ይለናል ታላቁ የሀይማኖት መስራች ቡድሀ

ወዳጄ በሌሎች ስኬት ወይ በሌሎች ደስታ መደሰትን ልመድ፤ የግድ ሻማውን እኔ ብቻ ላብራው አትበል! ተራው ያንተ ሲሆን ደግሞ ደስታህን ታካፍላቸዋለህ ያኔ በተራህ ያንተ ስኬት ለነሱ ተስፋና ብርሀን ይሆናቸዋል።

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
3.1K views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ