Get Mystery Box with random crypto!

መለወጥ አለብህ! ህልምህን ከመኖር በላይ የአይምሮ ሰላም የሚሰጥህ ነገር የለም፤ ወደምትፈልገው መ | Inspire Ethiopia 🇪🇹

መለወጥ አለብህ!

ህልምህን ከመኖር በላይ የአይምሮ ሰላም የሚሰጥህ ነገር የለም፤ ወደምትፈልገው መንገድ መጓዝ የምትጀምረው መቼ ነው? ሰው እንዴት ወደ ምስራቅ መጓዝ እያለበት ወደ ምዕራብ ይሄዳል? ከማይጠቅሙህ ሰዎች ጋር መሆን የምታቆመው መቼ ነው? ጊዜህን በዋዛ ፈዛዛ የሚያባክኑ ነገሮችን ከህይወትህ ቆርጠህ የምታወጣው መቼ ነው?

ስኬትና የህይወት እርካታ ዋጋ ያስከፍላሉ፤ በነፃ አይገኙም። አንተ ደግሞ እንኳን ለሚጠቅምህ ለማይጠቅምህም ነገር ዋጋ ከፍለህ ታውቃለህ፤ አሁን ሰዓቱ ራስህን እስከ መጨረሻው ስለ መቀየር የምናወራበት ነው! ወዳጄ አሁን የሚያስደስትህን ሰው ስለመሆን በማሰብ ጀምር፤ ከዛ ወደ ተግባር ግባ! አለቀ ዋጋ መክፈል ይሄ ነው! መለወጥ አለብህ! ቆሞ መቅረት የለም!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!