Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹 I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia2
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.35K
የሰርጥ መግለጫ

Fan page of inspire ethiopia

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-08-13 09:34:20 አንድ ቀን ተጨምሮልሀል!

የጀመርከውን እንድትጨርስ፤ ያበላሸኸውን እንድታስተካክል፣ የልብህን መሻት እንድታሳካ አንድ ቀን ተጨምሮልሀል። ይሄን ቀን ለማግኘት ያልታደሉ ብዙ አሉና አመስግነህ ተጠቀምበት!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
9.7K views06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 20:27:02 ከአንተ የሚጠበቀው!

በተግባር የምትገልጠው ማንነት ያስፈልግሀል፤ ከ 5 ዓመት ወይ ከ 10 ዓመት በኋላ መሆን የምትፈልገውን ሰው አሁን መሆን መጀመር አለብህ!

በቃ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ አድርግ! በየቀኑ በጥረትህ የሚገነባ እንጂ ከሰማይ የሚወርድ ማንነት የለም!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
10.1K views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 17:18:24 ሁሉንም ታልፋለህ!

በሰዎች መካከል ልዩነት የሚፈጥረው አንዱ ለማድረግ የሚከብደውን ወይ የሚፈራውን ነገር ሌላኛው እየደበረውም ቢሆን ጨክኖ ማድረጉ ነው። ህይወት ቀላል እንዲሆን አትመኝ፤ ከባድ ቢሆን እንኳን አንተ ከሱ በላይ ከባድ ሆነህ ማሸነፍን አስብ!

መጀመሪያ ተመኝ እንድታገኝ! ከዛ የሚጠበቅብህን ሁሉ አድርግ ያኔ በህይወት ሚዛን አንተ የማታልፈው ፈተና የለም፤ ወዳጄ ብርሀን ማየት የሚፈልግ ሁሉ ጨለማውን ታግሶ ማሳለፍ አለበት!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.4K views14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 09:36:00 የመጀመሪያው ደረጃ

ራስህን ለመለወጥ ሁሌም ዕድል አለህ፤ አንተ ማለት ከራስህ አልፈህ የቤተሰቦችህን ህይወት እስከመጨረሻው የምትቀይር ተዓምረኛ ነህ! ማማረር እና ሰበብ ማብዛት ባንተ አያምርም።

ለሁሉም ነገር ሀላፊነቱን እኔ እወስዳለው ስትል የራስህን ዕጣ ፋንታ ራስህ መወሰን ትጀምራለህ፤ የስኬት የመጀመሪያው ደረጃ ከማንም ምንም ነገር ሳትጠብቅ በራስህ ተማምነህ ህይወትህን ለመቀየር መነሳት ነው!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.4K views06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 19:21:09 ራስህን እመነው!

ለችግርህ ጊዜ የራቁህ ለስኬትህ ዙሪያህን ቢከቡህ አትደነቅ፤ በከባዱ ጊዜህ ትዝም ያላልከቸው በምርጡ ጊዜ ፍቅር በፍቅር ቢሆኑ እንዳይገርምህ። የዛሬም ሺ አመት ሰዎች እንደዚህ ነበሩ፤ ዛሬም ነገም እንዲህ ናቸው።

ስለዚህ ከሰው ምንም አጠብቅ! ከፈጣሪህ ቀጥሎ ራስህን እመነው! ራስን እንደመጠራጠር ህልም ገዳይ ነገር የለም!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተ ምርጥ ጓደኛ!
3.1K views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 15:44:14 ስለራስህ አስብ !

ሰዎች ስለ አንተ ምን እንደሚያስቡ በማሰብ ብዙ አትጨነቅ፣ እውነታው ሰዎች ስለ አንተ ከማሰብ በላይ ብዙ ሀሳብ አለባቸው፣ አንዱ ሀሳባቸው እንደ አንተ "ሰዎች ስለ እኔ ምን ያስባሉ" የሚለው ነው።

እና ሰዎች ምን ይላሉ የሚለውን ማሰብ ጎታች እና ራስን ከመሆን የሚያስቆም መሰናክል ነውና እንዳትሸወድ !

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
3.3K views12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 11:58:51 እችላለሁ በል!

ለትልቅ አላማ ነው ወደዚህ ምድር የመጣኸው ግን የምትፈልገውን ሁሉ ማሳካት እንደማትችል እያመንክ ስለሆነ ከአብዛኛው ሰው ጋር ለመመሳሰል እየጣርክ ነው። እንደ ንስር ከፍ ብለህ መብረር እየቻልክ ለምን እንደ ዶሮ መሬት ትጭራለህ?

ትልቅ ነገር የምታሳካው መጀመሪያ በነፃነት ትልቅ ማሰብ ከቻልክ ነው፤ አየህ መጀመሪያ ሀሳብ ትዘራለህ ከዛ ወደ ተግባር ትገባለህ። ወዳጄ አልችልም የሚለውን ትብታብ በጥሰህ የፈለከውን ሁሉ ለማሳካት ፈጣሪ እንደፈቀደልህ ራስህን አሳምነው! አሁን ለራስህ እችላለሁ ከማለት ጀምር!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
3.7K views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:24:19 ጉዞ ወደ ለውጥ!

ድግስ ላይ ከቡፌው የምትፈልገውን የምግብ ዓይነት ሁሉ አንስተህ ስትጨርስ ምግቡን ፊት ለፊትህ አስቀምጠው አይንህ እንዲያየውና አፍንጫህ እንዲያሸተው ብቻ ቢደረግ አያበሳጭም?

በህይወትም ብዙ የሚጠቅሙ ነገሮች አንብበህ፣ ሰምተህ፣ በአይምሮህ ሰብስበህ ግን ተግባር ላይ ካላዋልከው አሪፍ ምግብ ሳይበሉ ከማሽተት በምንም አይለይም። ብዙ ነገር ማወቅህ ጥሩ ነው፤ ወደ ተግባር ሲለወጥ እውቀት ኃይል ይሆናል። ዳይ ወደ ተግባር!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
4.3K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:07:58 ሀሳብና ስሜት

ማንኛውም ሀሳብ ወዳንተ ሲመጣ ስሜት ሰጥተህ ከተቀበልከው አንተ ውስጥ ይቀራል ህይወትህንም ይቆጣጠረዋል ለምሳሌ የሰው ጉዳት አይተህ ልብህ እስኪሰበር ካዘንክ አንተ ጋር ተመዘገበ ማለት ነው ፤ ስለዚህ የምትፈልገውን ህልምህንም ልብህ እስኪደነግጥ በስሜት አንተ ውስጥ አስቀረው ።

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
4.2K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 11:46:05 ይሄ ቀን ያንተ ነው!

እንዴ ያንተ ባይሆንማ በተኛህበት ትቀር ነበር፤ ስንቶች በተኙበት ቀሩ? ስንቶች በዚህ ለሊት ከመሬት በታች በመቃብር አደሩ? ለምን መሰለህ? ቀናቸው እንዲሆን ፈጣሪ አልፈቀደማ! እኛ ግን ተፈቅዶልናል ዛሬ የኛ ነው!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
4.2K views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ