Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹 I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia2 — Inspire Ethiopia 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia2
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.35K
የሰርጥ መግለጫ

Fan page of inspire ethiopia

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-10-05 19:28:33 ጀግና ያደርጉሀል!

በህይወት ፈተና ላይ ብዙ አይነት ውድቀቶችን ልታስተናግድ ትችላለህ ፤ ነው የኔ ፈተና እና ውድቀት ማብቂያው መቼ ነው እስከምንል ድረስ ድክም ብሎን ይሆናል ግን ሁሌም የሚፈተነው ብዙ ውጤትን መፍጠር የሚችለው ነውና ጀግና ሆነህ መውጣት ከፈለግህ ፈተናዎቹ ላይ የገጠሙህን ስህተቶች በደንብ ተማርባቸው በደንብ ጠንክርባቸው ብስል በልባቸውና ውጣ ያኔ ምንም አያንገዳግድህም!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
2.7K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 19:22:33 ጀምር!

አንድ ታላቅ ደራሲ "እንዴት አድርገህ ነው ይሄን የመሰለ ድንቅ መፅሀፍ የፃፍከው" ተባለ፤ ደራሲው ምንም ሳያመነታ "በአንድ ጊዜ አንድ ቃል እየፃፍኩኝ" አለ። ረጅሙ ጉዞ የሚጀመረው በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ ተራምደህ ነው።

በህይወትህ ትልቅ ምኞትና ብዙ ነገር የመቀየር ሀሳብ እንዳለህ እርግጠኛ ነኝ፤ ግን ማሰብ ብቻ  በቂ አይደለም። የምታስበውን ተነስና ማድረግ ጀምር፤ ምንም ነገር የሚሳካው ቆራጥ ሆነህ ስትጀምረው ብቻ ነው!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.8K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 13:20:25 አሁን ተነስ!

አለም የምትገዛበት አንድ የህይወት ህግ አለ፤ መስጠትና መቀበል። ማንም ሰው የሚፈልገውን ሳትሰጠው የምትፈልገውን ሁሉ አይሰጥህም። ስንዴ ዘርተህ ሩዝ አትሰበስብም፤ የተለየ ድንቅ ህይወት መኖር የሚፈልግ ድንቅ ልፋት መልፋት አለበት!

ለዛ ነው አሁን በሚገርም ሀይል ከአልጋህ መነሳት ያለብህ፤ ለዛ ነው ሳትሰለች ትምህርቱን መጨረስ ያለብህ፤ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ ካደረክ የምትፈልገው ሁሉ በጊዜው እና በሰዓቱ ያንተ ይሆናል። አሁን ተነስ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.8K views10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 19:55:04 አትቸኩል!

አንዳንዴ ፀጥ ማለት፤ አጎንብሶ ማሳለፍ መልካም ነው፤ ነገ የሚቆጭህን ነገር ከማድረግህ በፊት ትንሽ ጊዜ ውሰድና አስብ፣ ፀልይ። ፈጣሪ ስራውን የሚሰራው በግልፅ አይደለም በስውር ነው። የዘገየ ይመስልሃል ግን የሚቀድመው የለም! ስለዚህ ቸኩለህ አትወስን ብዙ ነገር ታበላሻለህ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.5K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 10:37:51 ራስህን ከማንም አታወዳድር!

ከሰዎች ጋር ራስህን አነፃፅረህ መቼም ሰላም አይኖርህም፤ ህይወት ውድድር አይደለም! ማሸነፍ ወይም መሸነፍ አይደለም! ህይወት ማለት ከዚህ አለም ከመሰናበትህ በፊት ምን ያህል ተደስተህ ታሳልፈዋለህ ነው። ወዳጄ ውድድር አቁም!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
4.6K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 14:32:32
Atomic habits በጀምስ ክሌር ተፅፎ እ.ኤ.አ በ2018  ለህትመት የበቃ መጽሐፍ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከ4 ሚሊዮን በላይ ኮፒዎች በመሸጥ የኒዮርክ ታይምስ ምርጥ ሽያጭ መፅሐፍ አንዱ ሆኗል።

ጀምስ ክሌር በህይወታችን ውስጥ  የምንፈልገውን ለውጥ ለማምጣት ትልልቅ ግቦችን ማስቀመጥ ዋነኛ እይታችን መሆን የለበትም ይላል።ይልቁኑ ወደ ምንፈልገው ግብ የሚመሩንን ልምዶች ለማዳበር በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ክስተቶች፤ ድርጊቶችና  ስርአቶች ላይ አተኩረን መስራት እንዳለብን ይገልፃል። Atomic habits ወይም ጥቃቅን ለውጦች የሚለው መጽሐፉ ስያሜውን ያገኘው ከዚህ ሃሳብ ተነስቶ ነው።

ጥቃቅን የልምድ ለውጦች በአጭር የጊዜ ሰሌዳ ላይ ሲታዩ ብዙም ለውጥ ሲያሳዩ አይታይም።ነገር ግን አንዴ ልምዶች ከዳበሩ በህይወታችሁ አስገራሚ ለውጦችን ማየት ትጀምራላችሁ።የጥቃቅን ልምዶች አቅም ከጊዜ ብዛት ተጠራቅሞ ይበዛል።ለምሳሌ በየቀኑ 1% የተሻለ ብንለብስ በአመቱ 37% እጥፍ የተሻለ አለባበስ ይኖረናል።

ከልምዶች መቀየር የሚመጣን ውጤት ለማየት ጊዜ ይፈልጋልና ትዕግስት ሊኖረን የሚገባ ሲሆን በብዛትም ትኩረታችንን ግቦችና መድረሻዎች ላይ ከማድረግ ይልቅ ሂደቶችና ለመድረስ የምንጠቀምባቸው ስርአቶች ወይም መንገዶች ላይ ልናደርግ ይገባል። ምክንያቱም ግቦችን ማስቀመጥ የምናገኘውን ውጤት ከተቀመጠለት የልኬት መጠን እንዳያልፍ ስለሚያደርግ ነው።
ክሬዲት በእምነት

ይህን መፅሃፍ Atomic habit የሚለውን መፅሀፍ በአማረኛ ትርጉም ማግኘት የምትፈልጉ በጣም በቅናሽ ዋጋ ያገኛሉ @bookstore_ethio
5.4K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 19:44:51 ስህተት ግዴታ ነው!

የሰው ልጅ ነህና መሳሳት የማይቀር ነገር ነው ነገር ግን የክፍል ፈተና ላይ x ከገባብህ እና ስህተትህን በደንብ አይተህ ትክክለኛውን መልስ ካላገኘህለት ዋናው ፈተናም ላይ ደግመህ ያን ጥያቄ ትስተዋለህ ምክንያቱም ፈተናው መጀመሪያም መጨረሻም የተለማመድከው ብቻ ነው የሚሆነው ስለዚህ በህይወትም ከምታከናውናቸው ስህተቶች በላይ ከስህተቶቹ መማር ያለብህ ላይ እና ድጋሚ እንዳይደገም ማድረጉ ላይ አተኩር!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
848 views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 15:05:03 መፅናት አለብህ!

ልጅ እያለን ለመራመድ ስንሞክር ብዙ ጊዜ ደጋግመን እንወድቅ ነበር፤ ከዛ ሰዎች ይስቁብናል በኛ ሁኔታ ይዝናኑ ነበር፤ "ደጋግሜ እየወደኩ ነው...በዛ ላይ የሰው መሳቂያ ከምሆን ባልራመድ ቢቀርብኝስ?!" ብሎ ያቆመ ህፃን ልጅ ግን የለም።

አሁንም በኑሮ ራስህን ለመቻል ወይ ለማደግ ስትሞክር የሚገጥምህ ነገር ከባድ ይሆናል፤ በብዙ አቅጣጫ ገፍቶ የሚጥልህ ነገር በዝቶ ይሆናል፤ አሁንም እንደ ልጅነትህ ተስፋ ቆርጠህ ካላቆምክ ህይወትን ማሸነፍህ አይቀርም! ወዳጄ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ፈታኝ ቢሆንም የጀመርከውን ጥግ ለማድረስ መፅናት አለብህ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.0K views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 09:58:00
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችው በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር እና የጤና ይሁንላችው !

@Inspire_ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.8K views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 17:27:31 ራስህ ላይ ስራ!

ጂም ሮን የተባለ ድንቅ መምህር "ስራህ ላይ ጠንክረህ ሰርተህ የምትዝናናው ቅንጡ ሆቴል ሊሆን ይችላል፤ ከስራህ በተጨማሪ ግን ራስህ ላይ ስትሰራ ግን ሆቴሉን ትገዛዋለህ" ይለናል።

ድርጅቶች የሚቀጥሩት ያንተን ዕውቀትና ልምድ ነው፤ አንተ በዕውቀትና በልምድ ካደክ ተፈላጊነትህ ሰማይ ይነካል። ራስህ ላይ መስራት ማለት በዕውቀት፣ በአመለካከት፣ በመንፈሳዊ ህይወት፣ በአካል፣ በስነልቦና በየቀኑ ማደግ ማለት ነው። ስራውን ወጥሮ የሚሰራ ገቢ ያገኛል፤ ከስራው በተጨማሪ ራሱ ላይ የሚሰራ ደግሞ ሀብት ይገነባል፤ ልዩነቱ ግልፅ ነው!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.9K views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ