Get Mystery Box with random crypto!

ሰዎች እንዳያደክሙህ! በጣም ጠንካራ እና ጎበዝ ስትሆን ሰዎች አስተያየት ያበዙብሀል እንደዚህ እኮ | Inspire Ethiopia 🇪🇹

ሰዎች እንዳያደክሙህ!

በጣም ጠንካራ እና ጎበዝ ስትሆን ሰዎች አስተያየት ያበዙብሀል እንደዚህ እኮ ብትጨምር ፣ ይሄንን እኮ ብታደርግበት ኖሮ እኮ በጣም ጥሩ ትሆን ነበር ግን አጠፋህ ይሉሀል የሰራሀቸውን ያደረግሀቸውን ትላልቅ ስራዎችህን ውርድ ያደርጉብሀል ግን የሚገርመው አንተ የለፋኸውን አንዲቷን ልፋት እንኳን አልለፉም ፣ ያደረግኸውን እንዲቷን ጥረት አልጣሩም ፣ በፍፁም ያንተን ድል አላገኙም ዝም ብለው ተቀምጠው ግን አንተን ይተቻሉ ያኔ አንተም ውስጥህ ይሸበራል አልችልም እንዴ  ፣ ምንም ነገር አልሰራውም እንዴ ? ምንም አልችልም እንዴ ያስብሉሀል ያገኘኸውን ድል ፣ ያሸነፍከውን ሁሉ ያስረሱሀል ፤ ስለዚህ አስተውል በፍፁም ላትሰማቸው ለራስህ ቃል ግባ መጨመር ያለብህን ልትጨምር ስትነሳ በፍፁም ያለህን እንዳትረሳ ፤ ብዙ እኮ ለፍተህበታል ጀግና እኮ ነህ!

@Inspire_Ethiopia2
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ