Get Mystery Box with random crypto!

HAppy Mûslim

የቴሌግራም ቻናል አርማ heppymuslim29 — HAppy Mûslim H
የቴሌግራም ቻናል አርማ heppymuslim29 — HAppy Mûslim
የሰርጥ አድራሻ: @heppymuslim29
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.25K
የሰርጥ መግለጫ

ONLY SHORT ISLAMIC STORY‼️
Fôr Any Cømments👉 @HappyMuslim29bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-14 15:31:40 ልጅቷን ለምን ሳምካት..?

በእድሜ የገፉ አባት ናቸዉ ከሁለት ወጣት ልጆቻቸዉ ጋር ሲኖሩችግር ይገጥማቸዋል :: ወንዱን ልጅ ስራ እንዲሰራ ይልኩታል ከመሔዱ በፊት ሊመክሩት ፈለጉና ''ልጄ ሆይ ስለ እህትህ ስትል አሏህን ፍራ አሉት:: አልገባዉም እህቱ አብራዉ አትሔድ ..ምን ለማለት ፈልገዉ እንደሆነ ሳይገባዉ ሳይጠይቅ ተሰናብቷቸዉ ሄደ:: ስራዉን ጨርሶ ሲመለስ አባት ልጄ ሆይ! ለምን ያቺን ልጅ ሳምካት አሉት ።

አባቴ አረ ማንንም አልሳምኩም አላቸዉ። ''በጭራሽ ስመሃታል!'' ብለዉ ሲያፋጥጡት አባቴ ማንም አላየንም ጨለማ ዉስጥ ነበርን ከአሏህ ዉጪ ማንም አልተመለከተንም ማን ነገረህ? ዋህይ(ራዕይ) ወረደልህ? እንዴት አወክ ብሎ ሲጠይቃቸዉ..

በሩን ከፍቼ ቤት ዉስጥ ቁጭ ብዬ ነበር ዉሀ ቅጂዉ ዉሀ ይዞ መጣ እህትህ ከፈተችለት ዉሃዉን ከገለበጠ በኃላ ሊወጣ ሲል እህትህን ግጥም አድርጎ ሳማት ያኔ አንተም የሰዉ እህት እንደሳምክ አወኩ ወደ ሌላ እንቅስቃሴ ብትገባ ዉሀ ቅጂዉም ወደሌላ እንቅስቃሴ ይገባ ነበር፡፡


*ሁሉም ሰው የዘራውን ያጭዳል በራስህ ላይ (በቤተሰብህ) ላይ ሊደረግ የማትፈልገውን ነገር በሌሎች ላይ አታድርግ። በሌላ ሴት ላይ የምሰራዉ ስራ አንተ ሳታቅ በእህትህ ላይ እንደሚሰራ እወቅ የሌሎችን ሴቶች መብት ስትጠብቅ የአንተም እህት መብት ይጠበቃል፡፡

@heppymuslim29
2.5K viewsعرفات ابن صادق, edited  12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 21:46:04 ይሰምራል ሃሳቡ ይሽራል ህመሙ
ያያቸው እንደሆን ነቢዩን በህልሙ
ሲባል የሰማው ሰው ነቢዩን የማየት ጉጉቱ ቢወርሰው ሼኽየው ጋር መጣ ምክርን ፈልጎ

ሃዘኔ ሚጠፋው ውጥኔም ሚሰምር
በሁለቱም ሃገር ተሽቆጥቁጬ ማምር
የሚፈካው ልቤ የሚሽር ህመሜ
ሳያቸው ነውና ነቢዩን በህልሜ
ይኼው በጠዋቱ መጣሁ አሰግስጌ
የልቤ እንዲሞላ ምክሮትን ፈልጌ

ሸኽየው ጠቢቡ ጥቂት አሰላስለው
ለርሱ ብቻ ሳይሆን ለትውልድ ደግሰው
ማለፊያ ምክርን ነገሩት ለዚህ ሰው

ከሼኹ አንደበት

ሦስት ቀን በሙሉ ውሃ ሳትጠጣ
ከቆየህ በኃላ ወደኔ እንድትመጣ
የሚል ትእዛዝ ወጣ

ነቢዩን ለማየት የከጀለው ያ ሰው
ከባዱን ጥም ፀንቶ እየታገሰው
ሁለተኛውን ቀን በጥማት ደረሰው
የመጨረሻይቱ ሶስተኛ ቀን ማታ የተኛው ይኸ ሰው እየተሰቃየ አንድ ህልምን አየ

ሲዋኝ ባህር ሰምጦ ሲራጭም ሲጠጣ
በውሃ ተከቦ ተውሃ እየገባ ተውሃ ሲወጣ
ታዲያ ሌት ነጋና ሼኽየው ጋር መጣ

ይኸው ሶስት ቀን ሙሉ ጥሙን ተቋቁሜ ከውሃ ሸሸሁም
ስቃዩን ታግሼ ጥማቴን ሸኘሁም
ታዲያ ግን ነቢየን በህልሜ አላየሁም
ሲል ቃሉን ሰበቀ

ታዲያ ምንድን አየህ ተብሎም ተጠየቀ
በውኃ ታጅቤ ስራጨው ስጠጣው ስገባው ስወጣው
ጥማቴን ስወጣው ሌቱን አደርኩና ወዳንቱ ጋር መጣው

ሼኹም ከተል አርገው አየህ አንተ ልጄ
ሶስት ቀኑን ሙሉ እጅግ የናፈቅከው
ስታስበው ውለህ ስታስብ ያደርከው
ውኃን ነበርና ልብህ ያሳረፍከው
ያው እንደናፈቅከው በህልምህ ጠጣኻው ጠገብከው
ታዲያ አንተ ልጄ ነቢም እንደ ውኃው ቢጠሙህ ቢናፍቁህ ብታስታውሳቸው
ቀን ሌቱን ተጠምተህ ጠንተህ ብትናፍቃቸው
እሳቸውን ሊያስብ ተከፍቶ ያንተ በር
ዘይንዬን ተጠምቶ ውስጥህ ቢንበረበር
እንደ ውኃው ሁላ ነቢዩንም በህልም ባየሃቸው ነበር
አየህ አንተ ልጄ ከሻትክ ልታያቸው የእውነት አፍቅራቸው
ናፍቅ አስታውሳቸው ተራብ ተጠማቸው
በማለት ተቋጨ ሸኽየው ምክራቸው

صلوات ربي وسلامه عليه
@heppymuslim29
5.8K viewsɯɐɥlǝ, edited  18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 17:21:38 ኢማሙ አህመድ "ቁርአን የአላህ ቃል ሳይሆን የፍጡር ነው" የሚለውን ቃል በመቃወማቸው ነበር ለእስር የተዳረጉት በዚህም ምክንያት ተይዘው ታሰሩ ብዙ እንግልትም ደረሰባቸው ከእስር ተፈተው ቤታቸው ቁጭ ብለው ሳለ "አላህ ሆይ! አቡ አብደላህን ይቅር በለው "ብለው ዱአ ያደርጉ ነበር፡፡
ማነው ይህ ዱዐ የሚያደርጉለት አቡ አብደላህ ተብለው ተጠየቁ፡፡ አብደላህማ አብረውኝ ታስረው ከነበሩት ሰዎች ውሰጥ አንዱ ነው፡፡ሰርቆ ነበር የታሰረው እኔ እስር ቤት እንደገባሁ... አሳሪዎቼ ሊገርፉኝ ተዘጋጁ ወደ መግረፊያው ስፍራ ወሰዱኝ ከዚያም መገረፍ ስጀመር ከሊፋው ገራፊውን በደንብ እንዲገርፈኝ ይነግረው ጀመር፡፡ አስር ገራፊዎች ነበሩ በስፍራው የነበሩት ተራ በተራ ይገርፉኝ ጀመር፡፡አንደኛው ገራፊ እስከ አስር ይገርፍና ያቆማል ፡፡እናም እንደገና አቅሙን አሰባስቦ ይመጣል
....ከዚያም ይህ ሌባ ወደ ኢማሙ አህመድ ጠጋ በማለት የሚያጠነክራቸውን እና የሚያበረታቸውን ቃል ተናገረ፡፡የሚደርስባቸውን በደል ሊያቆምላቸው ባይችል እንኳን የሚያረጋጋቸውን ቃል ተናገረ፡፡እንዲህም አላቸው "ኢማም ሆይ በከሊፋው ወቅት ሰርቄ አንድ ሺ ጅራፍ ተፈርዶብኝ ተገርፌ አውቃለሁ በተደጋጋሚም ሰርቄ ተገርፌያለሁ ግርፋቱ ግን ፈፅሞ ከአቋሜ እንዳፈገፍግ አላደረገኝም አሁንም እሰርቃለሁ እርስዎ ደግሞ ሀቅ ላይ ነዎት ኢማም ሆይ!ምናልባት አንድ ሁለት ዱላዎች ሲያርፍቦት ህመም ሊሰመዎት ይችላል ሲደጋገም ግን ህመሙ ይጠፋል አለኝ
.... "የዚህ ሌባ ሰው ንግግሮች በውስጤ ትዕግስት እና መረጋገት እንዲሰፍን አደረገልኝ፡፡"ይላሉ፡፡
እናም ይህ ሰው ከአንደበቱ በወጡት መልካም ቃላት እንዴት አንድን የተጎዳ ሰው እንደረዳ ተመልከቱ። አንድን የተቸገረ ሰው ምንም ልናደርግለት ባንችል በመልካም ንግግር ልንረደው እንደምንችል ሁነኛ ማሳያ ነው፡፡

@heppymuslim29
5.1K views*¨*ɯɐɥlǝ*¨*, 14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 06:47:50 መህሬ "ተውሒድ" ነው ያለችዋ ድንቅ እንስት
≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡

ሳቢት ኢብኑ አነስ እንዲህ አሉ፡-
አቡ ጦልሓ የተባለ ሰው ኡሙ ሱለይምን የትዳር ጥያቄ ያቀርብላታል ፡

ከዚያ ኡሙ ሱለይም እንዲህ ብላ መለሰችለት ፡

☞ " አንተ አቡ ጦልሓ ሆይ ! (ወላሂ) በአላህ ስም ይሁንብኝ የአንተ አይነት ሰው ለትዳር ጠይቆ እምቢ የምትባልና የምትመለስ ሰው አልነበርክም " ነገር ግን አንተ ካፊር/ካሃዲ ነህ ፡ እኔ ደግሞ ሙስሊም ሴት ነኝ ፡ እኔ አንተን ማግባት አልተፈቀደልኝም ፡ ከሰለምክ እሱ ነው መህሬ ከዚያ ውጭ ምንም አይነትን መህር አልፈልግም ፡
ከዚያም አቡ ጦልሓ ሰለመና ተጋቡ መህሯም ይሄው ሆነ ። አላህ አክበር

በሌላም
የኡሙ ሱለይም(ረዲየላሁ ዐንሃ) መህሯ ምን ነበር?!
አነስ _ረዲየላሁ ዐንሁ _ እንዲህ ይላሉ፦
"አቡ ጠልሓ ኡሙ ሱለይም(ረዲየላሁ ዐንሃ) ለማግባት የጋብቻ ጥያቄ አቀረቡ።
ኡሙ ሱለይም፦ "አንተ የምትገዛው ጣኦት እነ እገሌ… የሚባሉ ጎሳዎች መንደር ሐበሻዊ ሰው ከእንጨት እንጠረበው አታውቅምን?"ስትል ጥያቄ አቀረበችለት።
አቡጠልሓም፦"አዎን።ጠንቅቄ አውቃለሁ።"ሲል ምላሹን ሰጣት ።
ኡሙ ሱለይም፦"ታዲያ ሐበሺያዊው ሰው ከእንጨት የጠረበውን ጣኦት ስታመልክ ትንሽ እንኳ እፍረት አይሰማህምን?!!"አለችው።
በመቀጠልም፦
"እስልምናን ከተቀበልክ ከሱ ውጭ ሌላ ሰዳቅ ፣ጥሎሽ የምጠይቅህ ነገር አይኖርም።"
አቡጠልሐ፦"እስኪ የማስተውለበትና ከራሴ ጋር የምነጋገርበት ጥቂት ቀናትን ስጪኝ።"ብሏት
ወደ ቤቱ አቀና ብዙም ሳይቆይ ወደርሷ ተመለሰና፦
"አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢለ ሏህ፣ወአሽሀዱ አነ ሙሐመደን ረሱሉላህ"በማለት እስልምናን መቀበሉን ከፊትለፊቷ አበሰራት።
ከዚያም፦

ኡሙ ሱለይም፦"አንተ አነስ ሆይ! ወልይ(ሐላፊ)ሆነህ ከአቡ ጠልሐ ኒካሁን ተቀበል።"አለችኝ።"
ሣቢት (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦
"በእስልምና ታሪክ ውስጥ እንደ ኡሙ ሱለይም የላቀ እና ውድ መህር የተሰጣት ሴት ሰምተን አናውቅም፣ምክንያቱም የርሷ መህር አቡ ጠልሐ ኢስላምን መቀበሉ ነበርና።"
【ሲፈቱ ሰፍዋ"(2/247)】


@heppymuslim29
2.2K viewsعرفات ابن صادق, 03:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 22:57:22 ዘጠነኛውንና አስረኛውን ቀን ትፆሙ ዘንድ እናስታውሳለን:-

#ሙሐረም_እሁድ_9
መልዕክተኛው (ﷺ) "አላህ ብሎ መጪው ዓመት
ከደረስን ዘጠነኛውን ቀን እንፆማለን።"
(ሶሒሕ ሙስሊም 1134)

#ሙሐረም_10_ሰኞ
መልዕክተኛው (ﷺ) "የዓሹራን ቀንን መፆም የመጪውን ዓመት ኃጢአት ያስምራል ብዬ ከአላህ እከጅላለሁ።" ብለዋል
(ሶሒሕ ሙስሊም 1162)

አላህ ከሚጠቀሙት ያድርገን!
@heppymuslim29
5.3K views*¨*ɯɐɥlǝ*¨*, 19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 23:55:04 #አኩራፊ_ሰው_ብዙ_ነገር_ያመልጠዋል!

ባል እና ሚስቱ በመሀላቸው ግጭት ተፈጥሮ አይነጋገሩም፡፡ ሁለቱም በረጅም ትዝታ ተውጠዋል፡፡ መጀመሪያ ማውራት ሽንፈት መስሎ ስለታያቸው ሳይነጋገሩ መተኛ ሰዓታቸው ደረሰ፡፡ ድንገት ግን ባል የሆነ ነገር ትዝ አለው፡፡ ነገ በጠዋት የስራ ስብሰባ ስላለው ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ በረራ አለው፡፡ ሁሌ ደግሞ ወደ ስራ ሲሄድ እንቅልፋም በመሆኑ የምትቀሰቅሰው ሚስቱ ናት፡፡ እናም የነገው ስበሰባ እንዳያመልጠው ለሚስቱ "11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በአፉ መናገር ሞት መስሎ ታየው፡፡ እና ወረቀት ላይ "ነገ የስራ ስብሰባ ስላለበኝ ወደ ሌላ ሀገር እበራለው፡፡ አደራ 11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በወረቀት ፅፎ እሷ የምታየው ቦታ አስቀምጦላት ምንም ቃል ሳይተነፍስ ተኛ፡፡ ጠዋት ሰውየው ከእንቅልፉ ሲነቃ ከጠዋቱ 3ሰዓት ሆኖ በረራውም ስብሰባውም አምልጦታል፡፡ "እንዴት እንደዛ አስጠንቅቄ ነግሪያት አትቀሰቅሰኝም?" ብሎ በጣም ተበሳጨ፡፡ ከአልጋው ለመነሳት ሲሞክር አንድ ወረቀት ኮመዲኖ ላይ ተቀምጦ አየ፡፡ "11 ሰዓት ሆኗል ተነስ ስብሰባ እንዳያመልጥህ" የሚል ፅሁፍ ተፅፎበታል፡፡ ማነው ስህተት የሰራው? ማነው ልክ? ወዳጄ ሴትን ልጅ በተንኮልም ሆነ በፍቅር ልትበልጣት አትችልም፡፡
ዝምታ ደሞ መቼም መፍትሔ ሁኖ አያውቅም፡፡

"ለአላህ ስትል ክብርህን አሳልፈህ ስጥ።
የሰደበህን አሊያም የመታህን ለአላህ ስትል
ተውለት። ያጠፋህ እንደሆነም ከአላህ ምህረትን
ለምን።" (አቡ አድደርዳእ ረ.ዐ)

@heppymuslim29
3.1K views*¨*ɯɐɥlǝ*¨*, edited  20:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 10:35:07 * የቲም ሆነው ተወለዱ፣ ትንሽ ሆነው እናታቸዉን በሞት አጡ።
* በቅብብሎሽ በቅርብ ዘመዶቻቸው ቤት አደጉ።
* ኑሮን ለማሸነፍ ከእረኝነት እስከ ንግድ ሥራ አገልጋይነት ላይ ተሰማሩ።
* በ40 ዓመታቸው ነቢይነትን ተቀበሉ።
* በ53 ዓመታቸው ከመካ ወደ መዲና ተሰደዱ።
* በ61 ዓመታቸው በድል መካ ገቡ።
* በ63 ዓመታቸው ዓለምን ከመሠናበታቸው በፊት ዓለምን በኢስላም ብርሃን አበሩ።
* ይህ ሁሉ የሆነው በ23 ዓመታት ዉስጥ ብቻ ነበር።

እነሆ ዛሬ 1444 የስደት ዓመታቸው ላይ ነው።
የአላህ እዝነት እና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈን።

የኢማን፣ የአማን፣ የበረካ ወርና ዓመት ይሁንልን።
@heppymuslim29
3.0K views*¨*ɯɐɥlǝ*¨*, 07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 23:01:18 <<ድህነት ከተጫነህ፣ ችግር ከከበበህ፣ ማጣት ከወረረህ ሰለዋት አብዛ! ስስታምነት ከተጠናወተህ፣ እያለህ ማካፈል ከተሳነህ፣ ራስ ወዳድና ለመስጠት እጅህ የተሳሰረ ከሆነብህ ሰለዋትን አብዛት። ሰለዋት ድህነትን ያስወግዳል፡ ከስስታምነት ያጠራልና!!>>

اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا ومولانا محمد

@heppymuslim29
3.1K views*¨*ɯɐɥlǝ*¨*, 20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 15:17:13 በሱሓቦች ግዜ #ሳቢቱል_ቡንያን የተባሉ አሏህን ፈሪ የሆነለ ሰዉ ነበሩ ።

#ሳቢቱል_ቡንያን ነብዩ ሙሐመድን ﷺ አልተገናኙም ነበር ።ነገር ግን ነብዩ ሙሐመድን ﷺ በመዲና ለ10 አመት ያክል ከኸደማቸው ከአነስ_ኢብኑዐማሊክ ጋር ተገናኘተዋል።

#ሳቢቱል_ቡንያን" አሏህን ተገዢ፣ አሏህ ፈሪ ፣ የእውቀት ባለቤት፣ እንደዚሁም ከሐዲስ ዑለማወች አንዱ ናቸው።


"ሳቢቱል ቡንያን" የማይቀረው ሞት ደረሰና ወደ ቀብር በገቡ ግዜ እሳቸው ወደ ለህዱ ያስገባቸው ሰው እንዲህ_አለ ፦ « በአሏህ ይሁንብኝ #እኔ ሳቢቱል ቡንያንን ወደ #ለህዱ ካሰገባኃቸው ቡኃላ ከለህዱ መክደኛ መካከል አንዷ #ዲንጋ ወደ ለህዱ ገባች


ከዛም ይቺን ዲንጋይ ለማወጣት ወደ ለህዱ ገባ ስል #ሳቢቱል_ቡንያን ሶላት እየሰገዱ ተመለከትኩ።አብሮኝ ለነበረው ሰው እያየህ ነው ይሄን ነገር አለኩት ??? ሰውየውም በመገረም እረ አሁን ዝምበል አለኝ።

ከዛም ለህዱን ካስተካከልን እና ቀብሩን በአፈር ከሞላን ቡኃላ ወደ "ሳቢቱል ቡንያን" #ልጅ ሄድን ለልጅቷም አባትሽ ምንድነው ስራው? በዚች ዱንያ ምንድን ነበር የሚሰራው? ብለን ጠየቅናት
#ልጅቷም ምን አይታችሁ ነው? ብላ ጥየቀችን
#እኛም የተከሰተውን ነገር ባጠቃላይ ነገርናት ።

#ልጅቷም አባቴ ለ50 አመት ያክል የለይል ሶላት ይሰግድ ነበር እንደዚሁም በዚያ ለይልይ << #አሏህ_ሆይ! ለአንድ ሰው በቀብር ሶላት መስገድን ሰጠኽ እንደሆነ ለኔም ስጠኝ>> እያለ ዱዓእ ያደርግ ነበር ። ብላ መለሰችላቸው።

@heppymuslim29
7.0K views*¨*ɯɐɥlǝ*¨*, 12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 22:33:43 በቃልህ ሰውን አትግደል !

በአንድ ብርዳማ የክረምት ለሊት ንጉሱ ከጉዞው ወደ ቤቱ ይመለሳል ፣ በደጃፉም ላይ ከጠባቂዎቹ አንዱ ሽማግሌ ብርዱን ሊቋቋም ማይችል ልብስ ለብሰው ቆመዋል ፣ ንጉሱም ወደሳቸው ተጠጋና ....

"ለመሆኑ በዚህ ብርድ ይሄን ለብሰህ ትቋቋማለህ? " ሲል ጠየቃቸው ።

" እውነት ነው በጣም ይበርዳል ግን ደግሞ የክረምቱን ብርድ ማሳልፍበት ልብስ ስለሌለኝ ችለዋለሁ ! " ብሎ መለሰለት ።

ንጉሱም ....
" አሁን ውስጥ እንደገባሁ አንዱን አገልጋይ ብርዱን ምትከላከልበት ልብስ ይዞልህ እንዲመጣ ልክልሀለው " ሲለው በጣም ተደሰተ ።

ይሁንና ንጉሱ ወደ ውስጥ ሲገባ ሽማግሌውን ረሳው ፣ ወደራሱ ጉዳዮች ገባ ።

ንጉሱ ጠዋት ሲወጣ ሽማግሌው መሬት ላይ ተደፍቶ አጠገቡ አንዲት ወረቀት ላይ ...

" ንጉስ ሆይ የገደለኝ ቃልህ እንጂ ብርዱ አደለም ፣ ብርዱንማ ሁሌም እቋቋመው ነበር ዛሬ ግን ሚመጣውን ልብስ እየጠበኩ ነው ያቃተኝ ! " ሚል መልዕክት አስቀምጦለት አገኘው ።


ላንተ ተራ ለሌሎች የህይወት ጉዳይ በሆኑ ነገሮች ላይ ችልተኛ አትሁን

@heppymuslim29
2.7K views*¨*ɯɐɥlǝ*¨*, edited  19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ