Get Mystery Box with random crypto!

ማህበረ ሊባኖስ 👨‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👧👨‍👨‍👧‍👦 ₃

የቴሌግራም ቻናል አርማ abalibanos333 — ማህበረ ሊባኖስ 👨‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👧👨‍👨‍👧‍👦 ₃
የቴሌግራም ቻናል አርማ abalibanos333 — ማህበረ ሊባኖስ 👨‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👧👨‍👨‍👧‍👦 ₃
የሰርጥ አድራሻ: @abalibanos333
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.25K
የሰርጥ መግለጫ

ገና እንዘምራለን እንደመላእክቱ ብርሃንን ለብሰን
የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምሮ ና ስርዓት የጠበቁ
👉 መንፈሳዊ መዝሙሮች
👉 መንፈሳዊ ትምህርቶች
👉 መንፈሳዊ ግጥሞች
👉 መንፈሳዊ ታሪኮች
👉 ምንፈሳዊ ምክር ነክ ፁፎች
👉 ንግሶች ስኖሩ እናሳዊቃለን
👉ለመናፍቃለ የተለያዩ መልሶችን እንሰጣለን
ቻናሉን ለመቀላቀል @Abalibanos333

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-12 06:39:49 #በብርሃን_ፀዳል

በብርሃን ፀዳል ተከባ እመቤቴ
በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ
የጽጌውን ዜማ ስንዘምር በደስታ
በምስጋናሽ መጠጥ/ሲሰማኝ እርካታ/(፪)

እንባዬ ሲቀዳ ናፍቆትሽ መስጦኝ
ከደስታ በላይ አንቺን ስላየሁኝ
ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼው
የሌሊቱ ህልሜ /የቀን ምኞቴ ነው/(፪)
#አዝ
ሩኅሩኅ ነሽና ይህ ህልሜ ተሳክቶ
አመስግኜሽ ድንግል ህልናዬ ረክቶ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን/ህሊናዬ ይትጋ/(፪)
#አዝ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ህሊናዬ ይርካ
የምስጋናሽ ብዕር ብራናሽ ልሁን
ስምሽ ይፃፍብኝ /በልዩ ህብር/(፪)

@Abalibanos333
@Abalibanos333
@Abalibanos333

@DA121922

tik tok

https://www.tiktok.com/@da121922
326 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 06:35:10 #የብርሃን_እናት_ነሽና

የብርሃን እናት ነሽና የብርሃን እናት(፪)
ለምኚልን ድንግል ለምኚልን(፪)

ጸጋንና ክብርን የተመላሽ
ከሴቶች መካከል የተመረጥሽ
ለቃሉ ማደሪያ ዙፋን ሆነሽ
በደመና መንበር የተመሰልሽ
አዝ= = = = =
የሽቶ ማኖሪያ የተቀደስሽ
መዓዛሽ ያማረ ሽቶ ያለሽ
ውዳሴሽ ብዙ ነው እናታችን
ስምሽን እያሰብን ነው መጽናኛችን
አዝ= = = = =
በሀሳብ በግብር ፍጹም ሆነሽ
ምንኛ ብሩህ ነው ድንግል ልብሽ
አንቺን የሚመስል የለምና
ይሰማል ምልጃሽ ያንቺ ልመና
አዝ= = = = =
የብርሃን መውጫ ምሥራቁ ነሽ
ሰውን ለለወጠ ድልድይ ነሽ
ምሥጋናሽ አያልቅም ለዘላለም
ማህሌት ነሽና በአርያም
አዝ= = = = =
መላዕክት ፍጥረትሽን ያደንቃሉ
ጌታን በመውለድሽ ይመካሉ
ሰማይና ምድር ሳይወስኑት
ባንቺ ተወሰነ እፁብ በእውነት

@Abalibanos333
@Abalibanos333
@Abalibanos333

@DA121922

TIK TOK

https://www.tiktok.com/@da121922
259 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 06:28:45 #ድንግል_ሆይ_ስላንቺ

ድንግል ሆይ ስላንቺ ነውና መሓሪ
አማልጅኝ ካንዱ ልጅሽ ከፈጣሪ

ስሙን እዳልጠራ አንደበትም የለኝ
ፊቱንም እንዳላይ ስራዬ አሳፈረኝ

በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ
እለምነዋለሁ ከአሁኑ ይቅርታ

አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሳሪ
አማልደኝ ከአምላኬ ከፈጣሪ

ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ
ትእዛዙን እንደጣስኩ ህጉን እንደሻርኩኝ

ፃድቃን ሰማዕታት እናንተ ሁላችሁ
አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ

@Abalibanos333
@Abalibanos333
@Abalibanos333

Tik tok

https://www.tiktok.com/@da121922
214 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 03:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 21:18:04 ዛሬ በወጣው መረጃ ሕገወጦቹን ከአንዳንድ አህጉረ ስብከት ለማስወጣት ሙከራ ተደርጓል። የሚያስወጣቸው ደግሞ ያስገባቸው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ነው። ታዲያ ለምን ማስወጣት ጀመረ ብለን ስንጠይቅ መልሱ የድራማው አካል ስለሆነ ነው።
ኦርቶዶክሳውያኑን ለማሞኘት እያስወጣን ነው ብለው በሚዲያ ያስነግራሉ። ከዚያ በተለያዩ ከተሞች ለሕገወጦቹ የድጋፍ ሰልፍ ያካሂዳሉ። ከዚያም ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጉዳዩ የኦሮሚያ ሕዝብ ጥያቄ ነው ብለው ድጋፍ ያገኙበታል። ከነገ ጀምሮም አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሕገወጦቹን የሚደግፍ ሰልፍ ይደረጋል።
እንንቃ። በሴራ አንታለል።
391 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 18:28:48
ህገ ወጦቹ ጳጳስ ነን ባይ አካላት ከጊንቢ ወለጋ እና ነቀምት ከተሞች በፌዴራል ፓሊስ እና ኦሮሚያ ልዩ ኃይል ዛሬ መጋቢት 2 ተለቅመው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑ እየተሰማ ነው
***

የጊዜ ጉዳይ እንጅ ህገወጥነት አንድ ቀን እንደሚቆም እናምናለን።

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ግን ነገረ ሥራው አንቺው ታመጪ አንቺው ታሮጭው ሆኗል።

የግድህን ታወጣለህ!

የፍትህ ቀን ሲመጣ ደግሞ ቃታ ስበው በአውደምህረቱ ላይ የገ*ሉንን ወታደሮች እና ወንበዴዎችን በህግ አትሮንስ ውስጥ እናቆማለን።

@Abalibanos333
448 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 07:33:07 የሕገ ወጦቹ ተሿሚዎች ጠበቃዎች ያቀረቡት አስቂኝ የክስ መቃወሚያ

፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ሕጋዊ ሰውነት የላትም የመክሰስ ሥልጣን የላትም፤ ልትከስሰን አትችልም።

፦ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ስለሆነ ፍርድ ቤት እጁን ሊያስገባ አይገባም። በፍርድ ቤት ሊታይ አይገባም።

፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን "ተዋሕዶ" የሚለውን ስም መጠቀም አትችልም።

፦ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን ወክላ መክሰስ አትችልም

በማለት የክስ መቃወሚያ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል።

https://t.me/Abalibanos333
533 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 22:41:10 ፍርድ ቤቱ የሕገወጥ ቡድኑን መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ከጠየቀችው ዘጠና ቀናት ውስጥ የ፵፭ ቀናት የእግድ ትዕዛዝ ወሰነ።

( ኢኦተቤ ቴቪ የካቲት ፴/፳፻፲፭ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጸመው ሕገወጥና ኢቀኖናዊ ድርጊት ምክንያት በሕግ አግባብ የሚፈቱ ችግሮችን ለመቅረፍ፣ የቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ መብት እና የአማኞችን ሁለንተናዊ መብት እንደከበር ያስችል ዘንድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ ባለሙያዎች የጠበቆች ኮሚቴ በማቋቋም ጉዳዮችን በሕግ አግባብ እንዲፈቱ እየጠየቀችና እየተከታተለች እንደሆነ ይታወቃል።

በዚህ መሠረት የጠበቆች ቡድኑ ዛሬ የካቲት ፴/፳፻፲፭ ዓ/ም በዋለ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ችሎት የሰጠውን የተለያዩ ውሳኔዎችን በጥልቅ ማብራሪ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ፍርድቤቱ የቤተ ክርስቲያኗን ሕጋዊ ጥያቄ በሕግ አግባብ መልካም ውሳኔ የሰጠበት መሆኑን ግልጽና ጥልቅ በሆነው ገለጻው ተጠቁሟል።

የጠበቆች ቡድኑ በመግጫው ሕገወጦቹ ያቀረቦቻው የመቃወሚያ ጉዳዮች እንደነበሩ አብራርቶ ፍርድቤቱ በውሳኔ ውድ አድርጓቸዋል ብሏል።
ፍርድቤቱ ውድቅ ካደረጋቸው መቃወሚያ መከራከሪያ ነጥቦች መካከል

፩. ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ ሰውነት ያላት በመሆኑ የመክሰስና የመከሰስ መብት የለት መሆኑንና በጉዳዩ ላይ ክስ መመስረት እንደምትችል።

፪. ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን የመብት ጥሰት የንብረት ባለቤትነት ያለው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ማየት የሚችል መሆኑ በመጥቀስ የሕገወጡ ቡን መከራከሪያ ነጥቦችን ውድ አድርጓል።
በአጠቃላይ በሕገወጡ ቡድን የቀረቡ መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረግ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጡ ሹመት ላይ በተሳተፉ ፳፮ቱ ግለሰቦች ላይ ክስ እንድትመሠርት ውሳኔ ሰጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ቤተክርስቲያኗ በጠየቀችው የሦስት ወር እግድ ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤቱ ፵፭ ቀናት ከሦስቱ "አባቶች" በስተቀር ፳፮ (26)ቱም ግለሰቦች
ከዚህ ቀደም የገቡበትን መንበረ ጵጵስና እና አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ "የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሏትን ይዞታዎች፣ አህጉረ ስብከት፣ገዳማት እና አድባራት፤ አብያተ ክርስቲያናት ንብረቶቿን፤ ታሪካዊ ቅርሶች፣ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ መገልገያ እንዳይጠቀሙ፣ ወደ ቅጥሯ እንዳይገቡ፤ ንብረቶቿን እንዳይወስዱ፣ እንዳይገለገሉ፣ ዓርማዋንና ስሟን እንዳይጠቀሙ ይህ ጊዜያዊ የዕግድ ትዕዛዝ ለአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀናት ብቻ (ከየካቲት ፫/፳፻፲፭ ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ድረስ ብቻ ተሰጥቷል"።
መባሉን የጠበቆች ቡድን በመግጫው አሳውቋል።

ከዚሁ ጋር የኦርዶክሳውያን የእስር ሁኔታ የተነሳ ሲሆን በአብዛኛው እየተፈቱ መሆናቸውን ጠቅሶ በሻሸመኔና በአርሲ ነገሌ አካባቢ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን እስረኞ ለመጋቢት ፯፳፻፲፭ ዓ/ም ፍርድ ቤት እንደተቀጠሩም ተጠቅሷል።

በዚህ ረገድ የሕግ ተርጓሚ አካላት ላይ የሚታየው ፍትሕን የማስፈን ተጠቃሽ ሥራዎችን በመመዘርዘር በፍርድ ቤቶች የሚስተዋለው ፍትሕን የማስፈን መንገድ የሚበረታታና የሚያስመሰግን መሆኑን የጠቀሰው የጠበቆች ቡድኑ በአስፈጻሚ አካላት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የታየው የፍረድ ቤቶችን ውሳኔ ያለማስፈጸም ሁኔታዎች በእጅጉ ሊታረሙ እንደሚገባም ገልጿል።

በሌላ በኩል "በፓስተር ዮናታን" እና "በፓስተር ኢዩ ጩፋ" የቀረበው ክስ ምን ላይ ደረስ? ለሚለውም በምላሹ ከዚሁ ጋር ጎን ለጎን እያስኬደው እንደሆነ ተጠቁሟል።

በመጨረሻም የጠበቆች ቡድኑ የሕጉን መንገድ ተከትሎ የቤተ ክርስቲያን መብትና ማስጠበቅ ሁነኛ ግቡ መሆኑን የጠቀሰ ሲሆን ይሁን እንጂ የትኛውም መንገድ ይሁን ድርጊት ከቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ከአባቶች ቃል የማይቀድምና የማይበጥል በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የምትከተላቸውን የይቅርታና የስምምነት አቅጣጫዎችን በማክበረ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ኃይሉ በላይ
541 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 20:04:36 ሀገረ_ገዢው

"በአንድ ወቅት አንድ ንጉስ ብርዳማ በሆነ ምሽት ወደ ቤተ መንግስት ሲገባ ድንገት አንድ ቀልቡን የሚስብ ነገር ይመለከታል። አንድ ሰው ለራሱ በብርድ ተቆራፍዶ ነገር ግን ከጎኑ ላለው ውሻ ልብስ አልብሶት ይመለከታል በዚህ ጊዜ በጣም በመገረም ወደ ሰውየው ተጠግቶ እንዲህ ሲል ጠየቀው።

በዚ ቀዝቃዛ በሆነ ምሽት ከሰው በተሻለ ብርድን የመቋቋም ተፈጥሯዊ ችሎታ ላለው ለዚ ውሻ ልብስህን አልብሰህ አንተ ግን በብርድ ተቆራፍደሀል??? እና ይህን ለምን አደረክ ሲል ጠየቀው???
ሰውየውም፦ ጌታዬ እኔ እንደርሶ ያሉ ሰዎች መጥተው ሲጠይቁኝ ከውሻው በተሻለ ስለህመሜ፡ችግሬ፡ቁስሌ ባጠቃላይ ስሜቴ የመናገር ተፈጥሯዊ ችሎታ አለኝ ነገር ግን ይህ ውሻ ሲያመውም ሆነ ሲበርደው አፍ አውጥቶ ስሜቱን እንኳን መግለፅ አይችልም ለዚህ ነው ያለችኝን ልብስ ያለበስኩት አላው።

ንጉሱም፦የሰብአዊነትን ጥግ በተግባር በማየቱ በጣም እየተደነቀ ከጠባቂዎቹ አንዱን ወታደር ጠርቶ ለሰውየው ብርድ ሊቋቋም የሚችል ወፍራም ልብስ እንዲያመጣለት ትዛዝ አስተላልፎ እየተደነቀ ወደ ቤተ መንግስቱ ገባ።

ሰውየውም፦በንጉሱ ንግግር በጣም ተደሰቱ የሚመጣላቸውንም ብርድ የሚከላከል ልብስ በጉጉት መጠበቅ ጀመሩ። ነገር ግን ትዛዙ የተሰጠው ወታደር የንጉሱን ትዛዝ ረስቶት ልብሱን ሳያመጣላቸው ቀረ።
በንጋታው ንጉሱ ያሀን ሩህሩህ ሰው ለማየት ወደ ደጃፍ ሲወጡ ያሀ ቅን ሰው ትናንት ትተውት ከሄዱበት ቦታ ክልትው ብሎ ሞቶ አገኙት። ንጉሱም ካጠገቡ አንድ ብጣሽ ወረቀትላይ የተፃፈ መልእክት አገኙ ፁሁፉም እንዲህ ይል ነበር፦ንጉስ ሆይ እኔ ለብዙ አመታት ብርዳማ ለሊቶችን መቋቋም እችል ነበር።

ነገር ግን እርሶ ለማያሳኩት(ለማይፈፅሙት) ለኔ ብርድ የሚከላከል ልብስ ቃል መግባትዎ የኔን ብርድ የመቋቋም ሀይሌን ነጠቀኝ ስለዚህ ንጉስ ሆይ እኔስ አንድ ግለሰብ ነኝ ነገር ግን እርሶ የሚመሩት ህዝብ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የገቡለትን ቃል የማትፈፅሙለት ከሆነ በእርሶ ላይ ያለውን እምነት ሊሸረሽለው ይችላልና በተቻሎት መጠን ቃሎትን አይጠፉ ይላልፁሁፉ።

እስኪ ስንቶቻችን ነን፦ ለማንፈፅመው ነገር ለጓደኞቻችን ፍቅረኛችን ለሚስታችን ፡ለልጆቻችን ለቤተሰባችን ባጠቃላይ ለወዳጆቻችን ቃል ገብተን በባዶ ተስፋ ልባቸውን የሰበርነው???

ምን ለማለት ፈልጌ ነው፦ ቃል የምትገባላቸው ሰዎች ቃልህን አንተ ከምታስበው በላይ ቦታ ሊሰጡት ይችላሉና ለማታሳካው ወይም ለማትፈፅመው ነገር ቃል አትግባ።

ምክር ነክ ፁሑፍ

https://t.me/Abalibanos333
635 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 20:04:30 ትጾማለህን?
@Abalibanos333
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ትጾማለህን? እንግዲያውስ በሥራህ አረጋግጥልኝ!
በምን ዓይነት ሥራ ካልከኝ?

*ደሃውን ካየህ እዘንለት (ቸርነትን አድርግለት)!
*የተጣላኸውን ካየህ ታረቀው!
*ጓደኛህ ክብርን ሲያገኝ ካየህ አትቅናበት!
*መልከኛ ሴት ካየህ እለፋት!
*አፍህ ብቻ ከምግብ አይከልከል፤ አይንህም፣ ጆሮህም፣ እግርህም፣ እጆችህም፣ ሁሉም  የሰውነትህ ክፍሎች ይጹሙ።
እጆችህ ከንጥቂያና ስግብግብነት (ንፉግነት) ይጹሙ።

እግሮችህ የማይገቡ ትእይንቶችን ለመመልከት ከመንደርደር ይጹሙ።

አይኖችህ ውብ መልኮች ላይ ያልተገቡ እይታዎችን መቼም መች ከማሳረፍ መከልከልን ይማሩ እና ቁንጅና ላይ ከመጠመድ ይጹሙ።

ማየት ለዐይን ምግብ ስለሆነ ያልተገባ እና የተከለከለን እይታ ካደረግህ ጾምህን ያፈርሰዋል፣ የነፍስህንም ሙሉ ደህንነት ያነዋውጣል፤ ነገር ግን የተገባና ጥንቁቅ ከሆነ ጾምህን ያስጌጣታል።

የተከለከለውን በዓይን እየነካህ ነገር ግን በጾም ምክንያት ከማያረክስ ምግብ መጾሙ ከንቱ ከሆኑ ነገሮች መካከል ይቆጠራል።

ሥጋን አትበላም አይደል? ስለዚህ በዐይኖችህ አማካኝነት ፍትወትን አትመገብ። ጆሮም ይጹም።

የጆሮ ጾም ክፉ ወሬን እና ሐሜትን አለመቀበልን ያካትታል።

“ሐሰተኛ ወሬ አትቀበል” እንዲል። (ዘጸ. 23፥1)   አፍም እንዲሁ ከመጥፎ እና ከጥላቻ ንግግሮች ይጹም። 

ከአዕዋፋትና አሳዎች ብንከለከል ነገር ግን ወንድማችንን ብንበላው ምን ይጠቅመናል? ክፉ ተናጋሪ የወንድሙን ሥጋ ይበላል የባልንጀራውንም ሰውነት ይነክሳልና።

ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
542 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 20:03:59 ኃጢአት ስትሠራ አታፍር፣ ንስሐ ስትገባ አታፍርም [ንስሐ መግባት ማለት የልብና የአስተሳሰብ ለውጥ ማድረግ ማለት ነው። በቀላሉ የሀዘን ስሜት ሳይሆን ከክፉ/ከሞት የራቀ የስነ-ልቦና/መንፈሳዊ እድገት እና ወደ እግዚአብሔር/ህይወት መዞር ነው። ኃጢአት ቁስሉ ነው ንስሐ መድኃኒቱ ነው። ኃጢአትን ተከትሎ ነውር; ንስሐ በድፍረት ይከተላል [ድፍረት ማለት የማይገባን ምሕረትን መለመን ማለት ነው]። ሰይጣን ይህን ሥርዓት ሽሮ ለኃጢአት ድፍረትን ለንስሐም ነውርን ሰጥቷል
588 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ