Get Mystery Box with random crypto!

#በብርሃን_ፀዳል በብርሃን ፀዳል ተከባ እመቤቴ በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ የጽጌውን ዜማ ስንዘም | ማህበረ ሊባኖስ 👨‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👧👨‍👨‍👧‍👦 ₃

#በብርሃን_ፀዳል

በብርሃን ፀዳል ተከባ እመቤቴ
በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ
የጽጌውን ዜማ ስንዘምር በደስታ
በምስጋናሽ መጠጥ/ሲሰማኝ እርካታ/(፪)

እንባዬ ሲቀዳ ናፍቆትሽ መስጦኝ
ከደስታ በላይ አንቺን ስላየሁኝ
ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼው
የሌሊቱ ህልሜ /የቀን ምኞቴ ነው/(፪)
#አዝ
ሩኅሩኅ ነሽና ይህ ህልሜ ተሳክቶ
አመስግኜሽ ድንግል ህልናዬ ረክቶ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን/ህሊናዬ ይትጋ/(፪)
#አዝ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ህሊናዬ ይርካ
የምስጋናሽ ብዕር ብራናሽ ልሁን
ስምሽ ይፃፍብኝ /በልዩ ህብር/(፪)

@Abalibanos333
@Abalibanos333
@Abalibanos333

@DA121922

tik tok

https://www.tiktok.com/@da121922