Get Mystery Box with random crypto!

#የብርሃን_እናት_ነሽና የብርሃን እናት ነሽና የብርሃን እናት(፪) ለምኚልን ድንግል ለምኚልን(፪) | ማህበረ ሊባኖስ 👨‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👧👨‍👨‍👧‍👦 ₃

#የብርሃን_እናት_ነሽና

የብርሃን እናት ነሽና የብርሃን እናት(፪)
ለምኚልን ድንግል ለምኚልን(፪)

ጸጋንና ክብርን የተመላሽ
ከሴቶች መካከል የተመረጥሽ
ለቃሉ ማደሪያ ዙፋን ሆነሽ
በደመና መንበር የተመሰልሽ
አዝ= = = = =
የሽቶ ማኖሪያ የተቀደስሽ
መዓዛሽ ያማረ ሽቶ ያለሽ
ውዳሴሽ ብዙ ነው እናታችን
ስምሽን እያሰብን ነው መጽናኛችን
አዝ= = = = =
በሀሳብ በግብር ፍጹም ሆነሽ
ምንኛ ብሩህ ነው ድንግል ልብሽ
አንቺን የሚመስል የለምና
ይሰማል ምልጃሽ ያንቺ ልመና
አዝ= = = = =
የብርሃን መውጫ ምሥራቁ ነሽ
ሰውን ለለወጠ ድልድይ ነሽ
ምሥጋናሽ አያልቅም ለዘላለም
ማህሌት ነሽና በአርያም
አዝ= = = = =
መላዕክት ፍጥረትሽን ያደንቃሉ
ጌታን በመውለድሽ ይመካሉ
ሰማይና ምድር ሳይወስኑት
ባንቺ ተወሰነ እፁብ በእውነት

@Abalibanos333
@Abalibanos333
@Abalibanos333

@DA121922

TIK TOK

https://www.tiktok.com/@da121922