Get Mystery Box with random crypto!

ማህበረ ሊባኖስ 👨‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👧👨‍👨‍👧‍👦 ₃

የቴሌግራም ቻናል አርማ abalibanos333 — ማህበረ ሊባኖስ 👨‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👧👨‍👨‍👧‍👦 ₃
የቴሌግራም ቻናል አርማ abalibanos333 — ማህበረ ሊባኖስ 👨‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👧👨‍👨‍👧‍👦 ₃
የሰርጥ አድራሻ: @abalibanos333
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.25K
የሰርጥ መግለጫ

ገና እንዘምራለን እንደመላእክቱ ብርሃንን ለብሰን
የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምሮ ና ስርዓት የጠበቁ
👉 መንፈሳዊ መዝሙሮች
👉 መንፈሳዊ ትምህርቶች
👉 መንፈሳዊ ግጥሞች
👉 መንፈሳዊ ታሪኮች
👉 ምንፈሳዊ ምክር ነክ ፁፎች
👉 ንግሶች ስኖሩ እናሳዊቃለን
👉ለመናፍቃለ የተለያዩ መልሶችን እንሰጣለን
ቻናሉን ለመቀላቀል @Abalibanos333

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-03-08 20:03:09 በአንድ መንደር ውስጥ በሰዳቢነታቸው የታወቁ እድሜያቸው ገፋ ያለ ሴትዮ ነበሩ። አንዴ መሳደብ ከጀመሩ ማቆሚያም የላቸው።

የአብይ ጾም ገብቶ ነበርና ከአሁን በኋላ አልሳደብም ብለው ምለው ተገዘቱ።

ከእለታት በአንዱ ቀን አንዲት ጎረቤታቸው አንቺን ብሎ ጿሚ አፍሽ አይጾም እያለች በነገር እና በስድብ ስትጠዘጥዛቸው "አይ ጾም ሆነ እንጂ ለዚህስ መልስ ነበረው ፣ ሲፈታ ያገናኘን" አሉ ይባላል

ስድብ በቀጠሮ ይሏል ይሄ ነው።

@Abalibanos333

እስቲ ብዙዎቻችን ራሳችንን ዞር ብለን እንፈትሽ። ለጾም ለጾም ከኃጢአት ራቁ፣ ከጾም መልስ ወደ ኃጢአታችሁ ተመለሱ የሚል የትኛው የቤ/ክን ሕግ ነው? ጾምን በኃጢአት ይዘን በኃጢአትስ መፍታት ተገቢ ነውን? ጾም እንዴት ድል ባለ ጭፈራና የመጠጥ ጋጋታ ይይዛል? በጾም መያዣ ወቅት የከተማችን መኝታ ቤቶች ስለምን ይጨናነቃሉ? በእውነት ስለምን እንደምንጾም እናውቀዋለን ግን?

እግዚአብሔር ልብንና ማስተዋልን ያድለን።
501 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 06:45:38
#መንፈሳዊ_ጉዞ ወደ ምድረ ከብድ አቦ ገዳም

በመጀመሪያ ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን እያልን የአያት ጣፎ መካነ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ተክለ ቴዎፍሎስ ሰንበት ት/ቤት በደማቅ ሁኔታ የሚከበረውን የምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ በዓለ ንግሥ ምክንያት በማድረግ መጋቢት 4-5/2015 ዓ.ም ወደ ምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መንፈሳዊ ጉዞ አዘጋጅተናል።ስለዚህ እርስዎም የበረከቱ ተሣታፊ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር እና በጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም ተጠርተዋል።

መነሻ ቀን : 04|07|2015
መነሻ  : 12:00 ሰዓት
መመለሻ  05|07|2015 ከንግሥ በኋላ
የጉዞ ዋጋ : 500 ብር መስተግዶን ሳይጨምር
መነሻ ቦታ : አያት ጣፎ ቅዱስ ገብርኤል ቅጥር ጊቢ ዉስጥ    
                    

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር :

0953125078 ዳኜ
                   
0919289762 ደሳለኝ                   
0941137351 ፀጋ

0922592670 ተካልኝ

የጉዞ ቦታ ሳይሞላ አሁኑኑ ይመዝገቡ
በረከቱ እንዳያልፈን በቶሎ እንመዝገብ

       ለመመዝገብ  ከላይ ባሉት ስልኮች ይደውሉ

አዘጋጅ : ተክለ ቴዎፍሎስ ሰንበት ትምህርት ቤት

በቴሌግራም @DA121922
552 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 06:40:49 @Abalibanos333
471 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 06:40:48 የምትወዱት ሰዎች አልቅሱለት

ብክይዎ ወላሕውዎ
እለ ታፈቅርዎ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ኤልማስ
ዘበ እደ አይሁድ ተአስረ
አመ ጸምአ ማይ ይሰቲ
ሀሞተ ወከርቤ መሪረ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ

ጌታዬ አምላኬ በደል ሳይኖርበት ተገፋ
የአዳምን መርገም ሊያጠፋ
በአይሁድ እጅ ታሰረ
እንደ ወንጀለኛ ተቆጠረ
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ስለኔ
አልቅሱለት ስለ መከራው የምትወዱት

አዕንቃዕደ ወሰማየ
ኀበ አቡሁ ነጸረ
ሶበመንፈሱ ትወጽዕ
በላዕለ መስቀሉ ገአረ
ወይቤ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ

ውሃን የፈጠረ ተጠማ
ሀሞትን አጠጡት እየደማ
የሾህ አክሊል ደፍቶ ቀና አለ
መራራውን ጽዋ ተቀበለ 
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ስለኔ
አልቅሱለት ስለ መከራው የምትወዱት

በእናቱ ፊት ሰቀሉት
በጥፊ እየመቱ ዘበቱበት
ሐዘኑንስ እንዴት ትቻለው
መተኪያ የሌለው ልጇ እኮ ነው

እውነት ወደ ምድር ቢመጣ
በሀሰት ዳኝነት ተመታ
በጀርባው ላይ ጅራፍ አረፈ
ደሙ እንደ ውሃ ጎረፈ 
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ሰለኔ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ
ወይቤ ኤሎሄ ተፈጸመ ኲሉ

https://t.me/Abalibanos333
466 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 06:39:01 ✞ከካራን ስወጣ✞

ከካራን ስወጣ ወደ አዲሱ መንገድ
አላውቅም ነበረ ወዴት እንደምሄድ
ያንተን ቃል ነውና በማመን ወጣሁኝ
በረከት አግኝቼ ዘሬን አበዛሁኝ

ሲሰማኝ ምሬቱ የቀድሞው ኑሮዬ
ከቅርቡ ታሪኬ ጨለመ ኋላዬ
ካራን ያስተማረኝ ተስፋ ቢስ ሕይወት ነው
ስጠራኝ ያየሁት የነገን ክብሬን ነው
አዝ= = = = =
ከቶ ማን ሆኜ ነው እንዲህ ያከበርከኝ
ከአህዛብ ለይተህ ከፍ ከፍ ያረከኝ
አብርሐም ሆይ አልከኝ የወደድከኝ አምላክ
ልገዛ ላምልክህ ለክብርህ ልንበርከክ
አዝ= = = = =
ሕዝብህን ታደገው በረከት አይጥፋ
መሆንክን ይወቀው የዘለዓለም ተስፋ
አለማመን ይራቅ ጥርጥር ይወገድ
ልጆችህ ይጓዙ በአንዲቱ መንገድ

መዝሙር
ቀሲስ ዳዊት ፈንታዬ

"ግዚአብሔርም አብራምን አለው። ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።"

@Abalibanos333
@Abalibanos333
@Abalibanos333
532 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 11:52:35
#ታላቅ_መንፈሳዊ_ጉዞ ወደ ምድረ ከብድ አቦ ገዳም

በመጀመሪያ ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን እያልን የአያት ጣፎ መካነ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ተክለ ቴዎፍሎስ ሰንበት ት/ቤት በደማቅ ሁኔታ የሚከበረውን የታላቁን ገዳም ምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ በዓለ ንግሥ ምክንያት በማድረግ መጋቢት 4-5/2015 ዓ.ም ወደ ምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መንፈሳዊ ጉዞ አዘጋጅተናል።ስለዚህ እርስዎም የበረከቱ ተሣታፊ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር እና በጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም ተጠርተዋል።

መነሻ ቀን : 04|07|2015
መነሻ  : 12:00 ሰዓት
መመለሻ  05|07|2015 ከንግሥ በኋላ
የጉዞ ዋጋ : 600 ብር ምሳን ጨምሮ
መነሻ ቦታ : አያት ጣፎ ቅዱስ ገብርኤል ቅጥር ጊቢ ዉስጥ    
                    

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር :

0953125078 ዳኜ
                   
0919289762 ደሳለኝ                   
0941137351 ፀጋ

0922592670 ተካልኝ

የጉዞ ቦታ ሳይሞላ አሁኑኑ ይመዝገቡ
በረከቱ እንዳያልፈን በቶሎ እንመዝገብ

       ለመመዝገብ  ከላይ ባሉት ስልኮች ይደውሉ

አዘጋጅ : ተክለ ቴዎፍሎስ ሰንበት ትምህርት ቤት

በቴሌግራም @DA121922
807 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 11:29:53 3. #ምኩራብ
   ምኩራብ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ናት፡፡ በብሉይ ኪዳን የአይሁድ አምልኮ በኢየሩሳሌም በሚገኘው ቤተ መቅደስ ላይ ብቻ የሚፈጸም ነበር፡፡ በኋላ ንጉሥ ናቡከደነፆር ቤተ መቅደሳቸውን አፍርሶ ሕዝቡንም ማርኮ ወደ ባቢሎን አፈለሳቸው፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎትና ለማኅበርተኝነት ልዩ ቤት በመሥራት ስሙን ምኩራብ አሉት፤ (ሕዝ 11፥16)፡፡ በዚህ ምኩራብ ይጸልያሉ፣ ይማራሉ፣ ያስተምራሉም፤ በአጠቃላይ ከመሥዋዕተ ኦሪት ውጭ የቀረውን ሥርዓተ አምልኮ ሁሉ ይፈጽሙበት ነበር፤ መሥዋዕት ለማቅረብ ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ይሄዱ ነበር፡፡
  ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያ ምኩራብ ለማስተማር በገባ ጊዜ ከግብሯ በተቃራኒ መሸጫና መለወጫ ሆና ርግብና በሬ ሲነግዱባት አገኛት፡፡ ጌታም ይህን በተመለከተ ጊዜ ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት›› (ማቴ 21፥13 ፣ ኢሳ 56፥7 ፣ ኤር 7፥11) በማለት ለጸሎት ሳይሆን ለንግድ የገቡትን ከምኩራብ እንዲወጡ በጅራፍ እየገረፈ አባሯቸዋል፡፡ ጌታ ይህን ያደረገበት ሳምንት መታሰቢያ በመሆኑ ሳምንቱ ምኩራብ ይባላል፡፡
   በዚህ ሳምንት የሚሰበከው ምስባክ ‹‹የቤትህ ቅናት በልታኛለችና የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቋልና፤ ነፍሴን በጾም አስመረርኳት ለስድብም ሆነብኝ›› (መዝ 68፥9) የሚለው ሲሆን የዕለቱ ወንጌል ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ መቅደስ ርግቦችን፣ በሬዎችን፣ በጎችን ወዘተ ይሸጡና ይለውጡ የነበሩትን ከቤተ መቅደሱ ማባረሩንና ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ‹‹የቤትህ ቅናት ይበላኛል›› የሚለው ትንቢት መፈጸሙን እንዳስታወሱ ይነገራል፤ (ዮሐ 2፥12-25)፡፡ ጌታ በዕለቱ በሬ፣ በግ፣ ርግብ ወዘተ ይሸጡ የነበሩትን ከምኩራብ አስወጥቶ በእነዚህ እንስሳት ይፈጸም የነበረውን መሥዋዕተ ኦሪት አልፎ የክርስቶስ ሥጋና ደም ብቻ የሚሠዋበት ጊዜ መድረሱን አስተምሯል፡፡
   ቤት የተባለው በምሥጢሩ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነው የሰው ሰውነት ነው፡፡ ስለሆነም ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሳምንት ሸቀጥ ከተባለው ኃጢአት በንስሐ ታጥበን ለመቅደሱ ሥርዓት የምንመች ሆነን እንድንኖር ትሰብካለች፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ›› (ሮሜ 12፥2) ብሎ እንዳስተማረን በንሥሐ እየታደስን ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያነት ሰውነታችንን ማዘጋጀት ይገባናል፡፡

@Abalibanos333
              ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣  ሰባቱ አጽዋማት
    
738 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 16:29:14 ድንግል የዛን ጊዜ
ድንግል የዛን ጊዜ (፪) ሀዘንሽ በረታ (፪)
በመስቀል ላይ ሆኖ ልጅሽ ሲንገላታ(2)
የግፍ ግፍ ደርሶበት የዛን ጊዜ ተጠማሁ ሲልሽ
ለውሻ ያጠጣሽ በወርቅ ጫማሽ(2)
ሴቶች ሲያባርሩት የዛን ጊዜ ራርቶ ሆድሽ
ለፍጡር በማዘን ውኃ ያጠጣሽ(2)
ተጠማሁ እያለ የዛን ጊዜ ሲናገር ልጅሽ
ታዲያ እንደምን ቻለ የእናት አንጀትሽ (2)
እንደዚያ ስታለቅሽ የዛን ጊዜ ሐዘን ሲከብሽ
እነማን ነበሩ ያስተዛዘኑሽ(2)
ስታለቅሽ በማየት የዛን ጊዜ ራርቶ ልጅሽ
ዮሐንስን አፅናኝ እንደ ልጅ ሰጠሽ(2)

@Abalibanos333

Tik tok

https://www.tiktok.com/@da121922
805 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 16:29:12 እመቤቴ ማርያም
እመቤቴ ማርያም ወየው እያለች (፪)
አምርራ አለቀሰች እየተደፋች
ወየው አንዱ ልጄ
አንዱ ልጄ እኮ ነው የሌለው እኅት
አንዱ ልጄ እኮ ነው የሌለው ወንድም
ኧረ እንዴት ልቻለው መድኃኔዓለም
ወየው አንዱ ልጄ
እናቴ ኤልሳቤጥ ወዴት ነው ያለሽው
እኅቴ ሶሎሜ ወዴት ነው ያለሽው
እንድታላቅሽኝ ወየው እያልሽ ወየው
ወየው አንዱ ልጄ
ምንም ባላጠፋ ምንም ባልበደለ (፪)
በቀራንዮ ላይ በእንጨት ተሰቀለ
ወየው አንዱ ልጄ


@Abalibanos333
721 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 16:26:24ተሃልና ስለኔ
     ሞተሃልና ስለኔ ምንም ስይኖርብህ ጥፋት
      በሐሰት ተከሰህ በጲላጦስ ፊት
      ኢየሱስ አምላከ ምሕረት ስብሐት ለከ
ያንተ መንገላታት ሁል ጊዜ ያሳዝነኛል ሲወራ
በመስቀል ላይ ስለ እኛ ያየኸው መከራ
ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ስብሐት ለከ
      ከልዑል ቦታ ዝቅ ብለህ ፈጣሬ ፍጡራን አምላክ  
      በመስቀል ተሰቅለህ ስለ ሰው የሞትክ
       በመስቀል ላይ ተጠማሁ እያልክ ስብሐት ለከ
ክፉ አድራጊዎች ተነሥተው በምቀኝነት መንፈስ
ብዙ ሲጣጣሩ ለደምህ መፍሰስ
ሞትክላቸው ደስ እዲላቸው ስብሐት ለከ
       መሐሪ ጌታ አሁንም እንደቸርነትህ ብዛት
       የእኛን በደል ሁሉ ሳትመለከት
       አድነን ከዳግም ሞት ስብሐት ለከ


@Abalibanos333

Tik tok

https://www.tiktok.com/@da121922
621 viewsĎ`Ą የእናቱ ልጅ , 13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ