Get Mystery Box with random crypto!

ትጾማለህን? @Abalibanos333 በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትጾማለህን? እንግዲያውስ በሥራህ | ማህበረ ሊባኖስ 👨‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👧👨‍👨‍👧‍👦 ₃

ትጾማለህን?
@Abalibanos333
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ትጾማለህን? እንግዲያውስ በሥራህ አረጋግጥልኝ!
በምን ዓይነት ሥራ ካልከኝ?

*ደሃውን ካየህ እዘንለት (ቸርነትን አድርግለት)!
*የተጣላኸውን ካየህ ታረቀው!
*ጓደኛህ ክብርን ሲያገኝ ካየህ አትቅናበት!
*መልከኛ ሴት ካየህ እለፋት!
*አፍህ ብቻ ከምግብ አይከልከል፤ አይንህም፣ ጆሮህም፣ እግርህም፣ እጆችህም፣ ሁሉም  የሰውነትህ ክፍሎች ይጹሙ።
እጆችህ ከንጥቂያና ስግብግብነት (ንፉግነት) ይጹሙ።

እግሮችህ የማይገቡ ትእይንቶችን ለመመልከት ከመንደርደር ይጹሙ።

አይኖችህ ውብ መልኮች ላይ ያልተገቡ እይታዎችን መቼም መች ከማሳረፍ መከልከልን ይማሩ እና ቁንጅና ላይ ከመጠመድ ይጹሙ።

ማየት ለዐይን ምግብ ስለሆነ ያልተገባ እና የተከለከለን እይታ ካደረግህ ጾምህን ያፈርሰዋል፣ የነፍስህንም ሙሉ ደህንነት ያነዋውጣል፤ ነገር ግን የተገባና ጥንቁቅ ከሆነ ጾምህን ያስጌጣታል።

የተከለከለውን በዓይን እየነካህ ነገር ግን በጾም ምክንያት ከማያረክስ ምግብ መጾሙ ከንቱ ከሆኑ ነገሮች መካከል ይቆጠራል።

ሥጋን አትበላም አይደል? ስለዚህ በዐይኖችህ አማካኝነት ፍትወትን አትመገብ። ጆሮም ይጹም።

የጆሮ ጾም ክፉ ወሬን እና ሐሜትን አለመቀበልን ያካትታል።

“ሐሰተኛ ወሬ አትቀበል” እንዲል። (ዘጸ. 23፥1)   አፍም እንዲሁ ከመጥፎ እና ከጥላቻ ንግግሮች ይጹም። 

ከአዕዋፋትና አሳዎች ብንከለከል ነገር ግን ወንድማችንን ብንበላው ምን ይጠቅመናል? ክፉ ተናጋሪ የወንድሙን ሥጋ ይበላል የባልንጀራውንም ሰውነት ይነክሳልና።

ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ