Get Mystery Box with random crypto!

ሀገረ_ገዢው 'በአንድ ወቅት አንድ ንጉስ ብርዳማ በሆነ ምሽት ወደ ቤተ መንግስት ሲገባ ድንገት | ማህበረ ሊባኖስ 👨‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👧👨‍👨‍👧‍👦 ₃

ሀገረ_ገዢው

"በአንድ ወቅት አንድ ንጉስ ብርዳማ በሆነ ምሽት ወደ ቤተ መንግስት ሲገባ ድንገት አንድ ቀልቡን የሚስብ ነገር ይመለከታል። አንድ ሰው ለራሱ በብርድ ተቆራፍዶ ነገር ግን ከጎኑ ላለው ውሻ ልብስ አልብሶት ይመለከታል በዚህ ጊዜ በጣም በመገረም ወደ ሰውየው ተጠግቶ እንዲህ ሲል ጠየቀው።

በዚ ቀዝቃዛ በሆነ ምሽት ከሰው በተሻለ ብርድን የመቋቋም ተፈጥሯዊ ችሎታ ላለው ለዚ ውሻ ልብስህን አልብሰህ አንተ ግን በብርድ ተቆራፍደሀል??? እና ይህን ለምን አደረክ ሲል ጠየቀው???
ሰውየውም፦ ጌታዬ እኔ እንደርሶ ያሉ ሰዎች መጥተው ሲጠይቁኝ ከውሻው በተሻለ ስለህመሜ፡ችግሬ፡ቁስሌ ባጠቃላይ ስሜቴ የመናገር ተፈጥሯዊ ችሎታ አለኝ ነገር ግን ይህ ውሻ ሲያመውም ሆነ ሲበርደው አፍ አውጥቶ ስሜቱን እንኳን መግለፅ አይችልም ለዚህ ነው ያለችኝን ልብስ ያለበስኩት አላው።

ንጉሱም፦የሰብአዊነትን ጥግ በተግባር በማየቱ በጣም እየተደነቀ ከጠባቂዎቹ አንዱን ወታደር ጠርቶ ለሰውየው ብርድ ሊቋቋም የሚችል ወፍራም ልብስ እንዲያመጣለት ትዛዝ አስተላልፎ እየተደነቀ ወደ ቤተ መንግስቱ ገባ።

ሰውየውም፦በንጉሱ ንግግር በጣም ተደሰቱ የሚመጣላቸውንም ብርድ የሚከላከል ልብስ በጉጉት መጠበቅ ጀመሩ። ነገር ግን ትዛዙ የተሰጠው ወታደር የንጉሱን ትዛዝ ረስቶት ልብሱን ሳያመጣላቸው ቀረ።
በንጋታው ንጉሱ ያሀን ሩህሩህ ሰው ለማየት ወደ ደጃፍ ሲወጡ ያሀ ቅን ሰው ትናንት ትተውት ከሄዱበት ቦታ ክልትው ብሎ ሞቶ አገኙት። ንጉሱም ካጠገቡ አንድ ብጣሽ ወረቀትላይ የተፃፈ መልእክት አገኙ ፁሁፉም እንዲህ ይል ነበር፦ንጉስ ሆይ እኔ ለብዙ አመታት ብርዳማ ለሊቶችን መቋቋም እችል ነበር።

ነገር ግን እርሶ ለማያሳኩት(ለማይፈፅሙት) ለኔ ብርድ የሚከላከል ልብስ ቃል መግባትዎ የኔን ብርድ የመቋቋም ሀይሌን ነጠቀኝ ስለዚህ ንጉስ ሆይ እኔስ አንድ ግለሰብ ነኝ ነገር ግን እርሶ የሚመሩት ህዝብ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የገቡለትን ቃል የማትፈፅሙለት ከሆነ በእርሶ ላይ ያለውን እምነት ሊሸረሽለው ይችላልና በተቻሎት መጠን ቃሎትን አይጠፉ ይላልፁሁፉ።

እስኪ ስንቶቻችን ነን፦ ለማንፈፅመው ነገር ለጓደኞቻችን ፍቅረኛችን ለሚስታችን ፡ለልጆቻችን ለቤተሰባችን ባጠቃላይ ለወዳጆቻችን ቃል ገብተን በባዶ ተስፋ ልባቸውን የሰበርነው???

ምን ለማለት ፈልጌ ነው፦ ቃል የምትገባላቸው ሰዎች ቃልህን አንተ ከምታስበው በላይ ቦታ ሊሰጡት ይችላሉና ለማታሳካው ወይም ለማትፈፅመው ነገር ቃል አትግባ።

ምክር ነክ ፁሑፍ

https://t.me/Abalibanos333