Get Mystery Box with random crypto!

ኢማሙ አህመድ 'ቁርአን የአላህ ቃል ሳይሆን የፍጡር ነው' የሚለውን ቃል በመቃወማቸው ነበር ለእስር | HAppy Mûslim

ኢማሙ አህመድ "ቁርአን የአላህ ቃል ሳይሆን የፍጡር ነው" የሚለውን ቃል በመቃወማቸው ነበር ለእስር የተዳረጉት በዚህም ምክንያት ተይዘው ታሰሩ ብዙ እንግልትም ደረሰባቸው ከእስር ተፈተው ቤታቸው ቁጭ ብለው ሳለ "አላህ ሆይ! አቡ አብደላህን ይቅር በለው "ብለው ዱአ ያደርጉ ነበር፡፡
ማነው ይህ ዱዐ የሚያደርጉለት አቡ አብደላህ ተብለው ተጠየቁ፡፡ አብደላህማ አብረውኝ ታስረው ከነበሩት ሰዎች ውሰጥ አንዱ ነው፡፡ሰርቆ ነበር የታሰረው እኔ እስር ቤት እንደገባሁ... አሳሪዎቼ ሊገርፉኝ ተዘጋጁ ወደ መግረፊያው ስፍራ ወሰዱኝ ከዚያም መገረፍ ስጀመር ከሊፋው ገራፊውን በደንብ እንዲገርፈኝ ይነግረው ጀመር፡፡ አስር ገራፊዎች ነበሩ በስፍራው የነበሩት ተራ በተራ ይገርፉኝ ጀመር፡፡አንደኛው ገራፊ እስከ አስር ይገርፍና ያቆማል ፡፡እናም እንደገና አቅሙን አሰባስቦ ይመጣል
....ከዚያም ይህ ሌባ ወደ ኢማሙ አህመድ ጠጋ በማለት የሚያጠነክራቸውን እና የሚያበረታቸውን ቃል ተናገረ፡፡የሚደርስባቸውን በደል ሊያቆምላቸው ባይችል እንኳን የሚያረጋጋቸውን ቃል ተናገረ፡፡እንዲህም አላቸው "ኢማም ሆይ በከሊፋው ወቅት ሰርቄ አንድ ሺ ጅራፍ ተፈርዶብኝ ተገርፌ አውቃለሁ በተደጋጋሚም ሰርቄ ተገርፌያለሁ ግርፋቱ ግን ፈፅሞ ከአቋሜ እንዳፈገፍግ አላደረገኝም አሁንም እሰርቃለሁ እርስዎ ደግሞ ሀቅ ላይ ነዎት ኢማም ሆይ!ምናልባት አንድ ሁለት ዱላዎች ሲያርፍቦት ህመም ሊሰመዎት ይችላል ሲደጋገም ግን ህመሙ ይጠፋል አለኝ
.... "የዚህ ሌባ ሰው ንግግሮች በውስጤ ትዕግስት እና መረጋገት እንዲሰፍን አደረገልኝ፡፡"ይላሉ፡፡
እናም ይህ ሰው ከአንደበቱ በወጡት መልካም ቃላት እንዴት አንድን የተጎዳ ሰው እንደረዳ ተመልከቱ። አንድን የተቸገረ ሰው ምንም ልናደርግለት ባንችል በመልካም ንግግር ልንረደው እንደምንችል ሁነኛ ማሳያ ነው፡፡

@heppymuslim29