Get Mystery Box with random crypto!

መህሬ 'ተውሒድ' ነው ያለችዋ ድንቅ እንስት ≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡ ሳቢ | HAppy Mûslim

መህሬ "ተውሒድ" ነው ያለችዋ ድንቅ እንስት
≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡

ሳቢት ኢብኑ አነስ እንዲህ አሉ፡-
አቡ ጦልሓ የተባለ ሰው ኡሙ ሱለይምን የትዳር ጥያቄ ያቀርብላታል ፡

ከዚያ ኡሙ ሱለይም እንዲህ ብላ መለሰችለት ፡

☞ " አንተ አቡ ጦልሓ ሆይ ! (ወላሂ) በአላህ ስም ይሁንብኝ የአንተ አይነት ሰው ለትዳር ጠይቆ እምቢ የምትባልና የምትመለስ ሰው አልነበርክም " ነገር ግን አንተ ካፊር/ካሃዲ ነህ ፡ እኔ ደግሞ ሙስሊም ሴት ነኝ ፡ እኔ አንተን ማግባት አልተፈቀደልኝም ፡ ከሰለምክ እሱ ነው መህሬ ከዚያ ውጭ ምንም አይነትን መህር አልፈልግም ፡
ከዚያም አቡ ጦልሓ ሰለመና ተጋቡ መህሯም ይሄው ሆነ ። አላህ አክበር

በሌላም
የኡሙ ሱለይም(ረዲየላሁ ዐንሃ) መህሯ ምን ነበር?!
አነስ _ረዲየላሁ ዐንሁ _ እንዲህ ይላሉ፦
"አቡ ጠልሓ ኡሙ ሱለይም(ረዲየላሁ ዐንሃ) ለማግባት የጋብቻ ጥያቄ አቀረቡ።
ኡሙ ሱለይም፦ "አንተ የምትገዛው ጣኦት እነ እገሌ… የሚባሉ ጎሳዎች መንደር ሐበሻዊ ሰው ከእንጨት እንጠረበው አታውቅምን?"ስትል ጥያቄ አቀረበችለት።
አቡጠልሓም፦"አዎን።ጠንቅቄ አውቃለሁ።"ሲል ምላሹን ሰጣት ።
ኡሙ ሱለይም፦"ታዲያ ሐበሺያዊው ሰው ከእንጨት የጠረበውን ጣኦት ስታመልክ ትንሽ እንኳ እፍረት አይሰማህምን?!!"አለችው።
በመቀጠልም፦
"እስልምናን ከተቀበልክ ከሱ ውጭ ሌላ ሰዳቅ ፣ጥሎሽ የምጠይቅህ ነገር አይኖርም።"
አቡጠልሐ፦"እስኪ የማስተውለበትና ከራሴ ጋር የምነጋገርበት ጥቂት ቀናትን ስጪኝ።"ብሏት
ወደ ቤቱ አቀና ብዙም ሳይቆይ ወደርሷ ተመለሰና፦
"አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢለ ሏህ፣ወአሽሀዱ አነ ሙሐመደን ረሱሉላህ"በማለት እስልምናን መቀበሉን ከፊትለፊቷ አበሰራት።
ከዚያም፦

ኡሙ ሱለይም፦"አንተ አነስ ሆይ! ወልይ(ሐላፊ)ሆነህ ከአቡ ጠልሐ ኒካሁን ተቀበል።"አለችኝ።"
ሣቢት (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦
"በእስልምና ታሪክ ውስጥ እንደ ኡሙ ሱለይም የላቀ እና ውድ መህር የተሰጣት ሴት ሰምተን አናውቅም፣ምክንያቱም የርሷ መህር አቡ ጠልሐ ኢስላምን መቀበሉ ነበርና።"
【ሲፈቱ ሰፍዋ"(2/247)】


@heppymuslim29