Get Mystery Box with random crypto!

በቃልህ ሰውን አትግደል ! በአንድ ብርዳማ የክረምት ለሊት ንጉሱ ከጉዞው ወደ ቤቱ ይመለሳ | HAppy Mûslim

በቃልህ ሰውን አትግደል !

በአንድ ብርዳማ የክረምት ለሊት ንጉሱ ከጉዞው ወደ ቤቱ ይመለሳል ፣ በደጃፉም ላይ ከጠባቂዎቹ አንዱ ሽማግሌ ብርዱን ሊቋቋም ማይችል ልብስ ለብሰው ቆመዋል ፣ ንጉሱም ወደሳቸው ተጠጋና ....

"ለመሆኑ በዚህ ብርድ ይሄን ለብሰህ ትቋቋማለህ? " ሲል ጠየቃቸው ።

" እውነት ነው በጣም ይበርዳል ግን ደግሞ የክረምቱን ብርድ ማሳልፍበት ልብስ ስለሌለኝ ችለዋለሁ ! " ብሎ መለሰለት ።

ንጉሱም ....
" አሁን ውስጥ እንደገባሁ አንዱን አገልጋይ ብርዱን ምትከላከልበት ልብስ ይዞልህ እንዲመጣ ልክልሀለው " ሲለው በጣም ተደሰተ ።

ይሁንና ንጉሱ ወደ ውስጥ ሲገባ ሽማግሌውን ረሳው ፣ ወደራሱ ጉዳዮች ገባ ።

ንጉሱ ጠዋት ሲወጣ ሽማግሌው መሬት ላይ ተደፍቶ አጠገቡ አንዲት ወረቀት ላይ ...

" ንጉስ ሆይ የገደለኝ ቃልህ እንጂ ብርዱ አደለም ፣ ብርዱንማ ሁሌም እቋቋመው ነበር ዛሬ ግን ሚመጣውን ልብስ እየጠበኩ ነው ያቃተኝ ! " ሚል መልዕክት አስቀምጦለት አገኘው ።


ላንተ ተራ ለሌሎች የህይወት ጉዳይ በሆኑ ነገሮች ላይ ችልተኛ አትሁን

@heppymuslim29