አንዲት በስጋ ፋብሪካ ውስጥ የምትሰራ ሴት የዘወትር ተግባሯን ስትከውን ዋለች። በመጨረሻም ስጋ የሚቀመጥበትን ማቀዝቀዣ ክፍል ለማየት ወደማቀዝቀዣው ክፍል ገብታ ስጋዎችን በማስተካከል ላይ ሳለች የማቀዝቀዠው ክፍል በድንገት ተዘጋባት። የሚከፍትላት ሰው በመፈለግም በሩን ደጋግማ ደበደበች። ሰራተኞቹ ወተው ነበርና የድረሱልኝ ጩኸቷን የሚሰማት አላገኘችም። ቅዝቃዜው ሰውነቷን እያኮማተራት ነው። ሞት አፍጥጦ ከጣገቧ ደፍጦ ደቂቃ እየቆጠረ ነው። በዚህ ህኔታ ለአምስት ሰአት በፊሪጁ ውስጥ ቆየች። እስትንፋሷ ግን አልተቋረጠም። በድንገት ግን ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ። የፋብሪካው የጥበቃ ሰራተኛ በሩን ከፍቶ ገባ። እሷ ግን ለመናገር ትንፋሽም አጥሯት ነበር። ዘበኛው ግን የማቀዝቀዣውን በር ከፈተው። በሞት አፋፍ ላይ ያለችውንም ወይዘሮ ህይወት ታደጋት። ድርጊቱ ከሆነ በኃላ የዘበኛው በድንገት እዛ ክፍል መገኘት ያስገረማቸው ሁሉ ይሄን ጥያቄ ሰነዘሩለት።