Get Mystery Box with random crypto!

#አኩራፊ_ሰው_ብዙ_ነገር_ያመልጠዋል! ባል እና ሚስቱ በመሀላቸው ግጭት ተፈጥሮ አይነጋገሩም፡ | HAppy Mûslim

#አኩራፊ_ሰው_ብዙ_ነገር_ያመልጠዋል!

ባል እና ሚስቱ በመሀላቸው ግጭት ተፈጥሮ አይነጋገሩም፡፡ ሁለቱም በረጅም ትዝታ ተውጠዋል፡፡ መጀመሪያ ማውራት ሽንፈት መስሎ ስለታያቸው ሳይነጋገሩ መተኛ ሰዓታቸው ደረሰ፡፡ ድንገት ግን ባል የሆነ ነገር ትዝ አለው፡፡ ነገ በጠዋት የስራ ስብሰባ ስላለው ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ በረራ አለው፡፡ ሁሌ ደግሞ ወደ ስራ ሲሄድ እንቅልፋም በመሆኑ የምትቀሰቅሰው ሚስቱ ናት፡፡ እናም የነገው ስበሰባ እንዳያመልጠው ለሚስቱ "11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በአፉ መናገር ሞት መስሎ ታየው፡፡ እና ወረቀት ላይ "ነገ የስራ ስብሰባ ስላለበኝ ወደ ሌላ ሀገር እበራለው፡፡ አደራ 11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በወረቀት ፅፎ እሷ የምታየው ቦታ አስቀምጦላት ምንም ቃል ሳይተነፍስ ተኛ፡፡ ጠዋት ሰውየው ከእንቅልፉ ሲነቃ ከጠዋቱ 3ሰዓት ሆኖ በረራውም ስብሰባውም አምልጦታል፡፡ "እንዴት እንደዛ አስጠንቅቄ ነግሪያት አትቀሰቅሰኝም?" ብሎ በጣም ተበሳጨ፡፡ ከአልጋው ለመነሳት ሲሞክር አንድ ወረቀት ኮመዲኖ ላይ ተቀምጦ አየ፡፡ "11 ሰዓት ሆኗል ተነስ ስብሰባ እንዳያመልጥህ" የሚል ፅሁፍ ተፅፎበታል፡፡ ማነው ስህተት የሰራው? ማነው ልክ? ወዳጄ ሴትን ልጅ በተንኮልም ሆነ በፍቅር ልትበልጣት አትችልም፡፡
ዝምታ ደሞ መቼም መፍትሔ ሁኖ አያውቅም፡፡

"ለአላህ ስትል ክብርህን አሳልፈህ ስጥ።
የሰደበህን አሊያም የመታህን ለአላህ ስትል
ተውለት። ያጠፋህ እንደሆነም ከአላህ ምህረትን
ለምን።" (አቡ አድደርዳእ ረ.ዐ)

@heppymuslim29