Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 26

2022-09-11 01:16:29

ያ የተረገመ የክፉ ቀን ክስተት
የሰይጣን ምርኮኛ የሰላም እንቅፋት
የጠንቋዮች ፍሬ የባእዳውያን ብስራት
የፈጣሪ ቁጣ ያ ነው የኛ ቅጣት
ያ ያ ነዋ ያ
የፈረንጆች ባርያ
እኔ አላልኩም
2.9K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 22:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 22:22:13 "እኮ ለምን?????"
ሴት እኮ እናት ናት፣
ሴት እኮ ሀገር ናት፣
ሰሴት እህት ናት፣
ወልዳ ተሸክማ ጡቶቿን አጥብታ ፣
ልጇ እንዲኖር ብላ እሷ ተሰቃይታ፣
እኮ ለምን....
በሁለት ሶስት ወንድ ተገዳ መደፈር፣
ለምንድነው ካለፍላጎቷ አፏ የሚታሰር፣
ህይወትን በሰጠች ነፍገው ምስጋናን፣
ሀገር አያድግም ካላገዝን ሴትን፣
የወላድ መካን እሷን ሊያደርጉ፣
እምነት አርክሰው ለስሜት ሊዋጉ፣
ምናለ ፈጣሪ ቢሰማኝ ጸሎቴን፣
ክብር ለማያውቁ ፈጽመው ክህደትን፣
ሊመራ ኢትዬጵያን አብዝቶ ስቃይን፣
እንዲእያደረገ ሳይወቅሰው ህሊናው፣
የተናቀ እንጂ አይደለም ይሄ ሠው።
ገጣሚ" ጽዮን ግርማ (ቃል)"
@gitmv
415 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 22:22:12 የገሀነም መዝገብ

አንድ ጦማር አንድ መዝገብ፣ አምልጦ ወድቆ ከሰማይ፣
ወደ ገሀነም የሚገቡ፣ ሰዎችን ዝርዝር የሚያሳይ፣
አነሳሁትና ስበር፣
ከራሴ ስም አስቀድሜ የፈለኩት ያንቺን ነበር።
Firmaye Addisu
423 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 22:22:12 ቅጠረኝ 'መጣለው
ቅጠረኝ 'መጣለው በተመቸህ ጊዜ
ወዴት እሄዳለሁ ሁንልኝ አዛዤ
ዝናቡ ቢዘንብም ቢሆንም በጭቃ
ሆነሃልኮ የልቤ አለቃ
ያለህበት ስፍራ ቢሆንም ዳገት አልቀርም እመጣለሁ በጠራኸኝ ሰአት
yoyo
394 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 19:47:12
ስውር ማንነቴ
በሚያበራው ፊቴ በጥርሴ ፈግጌ
በኮምታራ 'ኔነት በውስጤ ጨፍግጌ
ገነት ፖስታለው እውነታው በረሃ
ስፈፈልግ ኖራለው ጥሜን ሚቆርጥ ውሃ
ሲያውቀኝ አያውቀኝም ማንነቴን ዘልቆ
ፈገግታዬን ሲያየው ፊቴ አሸብርቆ
ማስመሰሌ እንኳን እንዲሁ ያታልላል
እንደ ጥርስ ልማም እያደር ይሸታል!!
Moge @gitmv
954 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 19:47:07 እንቆጳዝዮን

አንችነትሽን ሸሽተው ከፍቅርሽ ቢርቁ ፣
እንደሌዊ ልጆች በክብር ሳይበቁ ፣
ውድ እንቁ ሃገሬን
ለጥል የነኩሽ 'ለት ከዙፋንሽ በታች በሞታቸው ይንቁ ።

ሙሌ @gitmv
902 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 19:47:07 ብዕር አለቀሰ
ፍልስፍና ቢሉ መላቅጡን ያጣ
ዝቃጭ አስተሳሰብ ሀገር ካገረጣ
የፈሰሰው እምባ ከአይን ካልደረቀ
ፍትህ ተገማድሎ ከሀገር ከራቀ
በሟች ቤተሰብ ፊት ገዳይ መሳለቁ
ያንገበግበናል ፍትህ ማዘቅዘቁ።
ገድለው ሲያበቁ ተፈቱ ሳይቀጡ
ፍትህ ድምፁን ሲያጣ ተበዳይ ተቆጡ
የ እንባችን ወዙ በፊታችን ደርቋል
የመንግሥትም ጆሮ ከድምፃችን ርቋል
እኛ ዝም ስንል ብእራችን አልቅሷል

@gitmv .
881 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:04:58 ለሠላም ዘምሩ


የሀገሬ ፈተና - አትስገዱ ዛቻ
በምእመኑ ጥሪ - አትሮጡም ዛቻ
የመንግስቱ አቋም - እኔ ያልኩት ብቻ

ኑሮ ተወደደ - ዘይትም ጣራ ነካ
ታድያ ምን ያደርጋል - ሙዝ በዳቦ እንካ

ደሞ ሌላ ጊዜ...

በአባቶች ችልታ ምናገባኝ ስሜት
ፖሊሶች ሲሰርቁ
አባቶች ቁጭ ብለው
ልጆች ሲያስታርቁ

ባዋቂው ዝምታ - ባላዋቂው ወሬ
ሃገር የሚያክል ነገር
እምነት የሚያክል ነገር
ሆነ አንድ ፍሬ

የሃገሬ ሠዎች - ለነብሳችሁ ኑሩ
መልካም ፍሬን ዝሩ
በብሄር ከፋፍሎ - ለፀብ ክመሯሯጥ
ለሠላም ዘምሩ::

-ዳዊት(የለትዬ ልጅ)
@DevZHab
1.1K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:04:49 የመታመምሸ ልክ

የታረዘ አንጀትሺን ቲብቲቦ ያሰረሺዉ
መታረዝ መራብን እንደምን የቻልሺዉ


ከደረቀዉ ጡትሺ ቁረንጮ እየጠባ
ምራቁን በገላሺ አርሷ ለጠባ
የመታረዙን ልክ የመራብን ጠኔ አይተሺ እንዳላዬ
ምታልፊዉ ጨንቆሽ ነዉ ገብቶኛል እማዬ
ለተራበዉ ሆደሸ ለሚፈሰዉ እንባሸ
ለጨነቀዉ ልብሸ
አንቺ ምኑን አዉቆሸ ምክኒያቱሱ መቺ ገብቶሸ
ገሎሸ መኖር ሚመኝ የወሬ አለቃዉ
ያ እሩቅ ያለዉ የማያዉቅሸ ልጂሸ ደልቶት የሚኖርዉ
ብላቴና ልጂሸን እንዲያለቅስ ላረገዉ
ማይተዉሸ አምላክሺ ቀድሞ ይግደልና እንባሺን ያብሰዉ

በራማዉም ይሰማሸ መልሱንም ያፍጥነዉ።።።።ተፃፈ Fanta
1.0K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:04:34 ለኢትዮጵያ እንቁም
ለሰላም እንዘምር ፍቅር እናስፋፋ
የጦርነት መአት ከሀገራችን ይጥፋ
መዝፈን ብቻ ሳይሆን በጋራ እንታገል
ካለ ቆራጥ ትግል ሰላም አይታደል
ዝም ማለትማ ለበግም አልበጄ
ሺዉን የበግ መንጋ አንድ ነብር ፈጄ
በጋራ ተነስተን በአንድነት ተሳስረን
ኢትዮጵያን እናድን እንደ አባቶቻችን
ታሪክ እንደሰማን ታሪክ እንሰራለን
ፍሥሃ
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
939 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ