Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 27

2022-08-28 19:12:05 አትሰስች እባክሽ ልብሽን ይሉኛል
ይቆራኙኛልም ጠጋኝ ይመስል


ከአንድም ሁለት ከሦስትም በላይ
ተከስክሷል ልቤ ለላን ላያይ


የፍቅር ምላሽ ከሆነ ስብራት
ከዝህም ይልቅ ልቤን ልሰስት


@Emutque
1.7K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:12:05 የንጉስ ዝምታ
ከ እልፍ ማስፈራራት ከ ሺ ድምፆች መሃል
በገዢዎች ቁጣ  ከአንበሶች መጣል
ያሰጋ ይሆናል ያርድም ይሆናል
ሃያላን  ሲያብሩ
ተማክረው ሲያሴሩ
ቁጣቸው ድምፃቸው ልብን ያሸብራል
ግና ከድምፀቱ  ከ ቁጣውም በላይ
ከ አንበሶች ግሳት ዝምታው ግን ሲታይ
ነፍስን ያስጨንቃል ከተማን ያውካል
ሃገርን ያምሳል ትጥቅ እንኳን ያስፈታል
የነገስታት ንጉስ ዝም ሲል ያስፈራል
@gitmv @mogea
1.6K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:12:04 የትኛውን ግጥም ይበልጥ ወደዳችሁት?ላይክ በማድረግ እንዲሁም ሌሎች ወዳጆቻችሁን ወደ ቻነሉ በመቀላቀል ተሳተፉ።በቅድሚያ 60 ላይክ ለሚደርስ ተወዳዳሪ ሽልማታችን እንደተጠበቀ ነው።
@gitmv
1.3K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:12:04 ክረምት እና ናፍቆት

በክረምት መግቢያ እፈልግሻለሁ
ምን ባስከፋሽ እንኳን ይቅርታን እሻለሁ
እዚህ ያለሁበት ክረምቱ ይረዝማል
ቆፈኑ ብርቱ ነው አንድ ሆኖ ይከብዳል
እዚህ ያለሁበት ውርጩ አያላውስም
ለብቻ ተሁኖ እርምጃ አይሰምርም
እዚህ ያለሁበት ዝናቡ ያይላል
ከንጋት እስከ-ሌት እዬዬን ያቀልጣል
እዚህ ያለሁበት አንቺን መሳይ የታል
እቅፍን አሙቆ ሀሴት መች ያድላል
እዚህ ያለሁበት አንቺስ የታል ያለሽ
በበጋ እኝደራቅሺኝ እንደሸሺኝ ነሽ
እዚህ ያለሁበት ትዝታሽ ብቻ ነው ውል ሲል ሚታየኝ
ከክረምት አብሮ ቆፈናም ያረገኝ
እዚህ ያለሁበት መች እንደሆን እንጃ መጥተሽ ያገኘሁሽ
ትውስታዬን ሁሉ ከክረምቱ ጋራ አጥቦት የረሳሁሽ

በክረምት...

በክረምት ፍቅራችን ጠሃይን ይሆናል
ሙቀት ተጓናፅፎ ከብርሃን ይፈካል
በክረምት ፍቅራችን ከቁር ይዛመዳል
በጠፈጠፍ መሃል ውብ ሙቀት ይወልዳል
በክረምት ፍቅራችን እርጥበት ያረግፋል
ግግር በረዶንም አቅልጦ ያከስማል
በክረምት ለዛሽ እጅግ ይጥመኛል
ከበጋ ከማውቀው እጅግ ያድግብኛል
በክረምት
ተፈጥሮሽ ውበቱ ተአምር ሲያሰኝ
ከቁሩ ገላግሎ ለፀደይ ሲያቆየኝ
ሳልጠግበው ያልፈኛል
አዲስ አመት ከቶ መምጫው እስኪደርስ እንደሁለመናሽ ሀምሌ ይናፍቀኛል።

እናም...

በክረምት አትቀሪ በውርጩ መባቻ
ከብርዱ መግቢያ ላይ ግንቦት መከተቻ
ሀምሌ ላይ አልጣሽ ክረምት ከመበርቻው
ልክ እንደ በፊቱ ልክ እንደ ካችአምናው።
Ab
1.5K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:14:56 የማያሽር...ጠባሳ
፨።።። ።።።፨

ቀኑም አይመሽልኝ ለሊቱም አይነጋ
ልቤ እየተቀጣ በሀሳብ አለንጋ
ከልብ ውስጥ የማይጠፋ ከቶ ማይረሳ
ህመሙ የማይድን የማይሽር ጠባሳ
ቁስሉ የሚቆጠቁጥ የህሊናን ዕዳ
አሸክማኝ ሄደች በሰውፊት አዋርዳ
ሀዘን ድንኳ ጥሎ ጎጆውን ቀልሶ
ልቤውስጥ ይኖራል ጎኔን ተንተርሶ
ልቤ ፍቅርን ብሎ ለፍቅር ባደረ
ሀዘን ቤቴን ወርሶት ቅስሜ ተሰበረ
.
.
.
ያላረኩት የለም ልቤን ለማሳመን
በደልሽን ችዬ ካንቺ ጋር ለመሆን
ግን አንቺ አልገባሽም ባንቺ መጎዳቴ
በብርሀን ጭለማ መሆኗን ህይወቴ።።።።።።


@yederasiyanbet
3.0K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:14:56 ።።።።።።።። ።።።።።።።።።።።።
#ፈተና_እንዱ_የህይወት_ቅመም ነው፡፡
ያለ ሃዘን ደስታ ልታቅ አትችልም፡፡
ነገሮች መጀመሪያ ክፋታቸውን ካልተረዳህ ጡሩነታቸው በፋፁም ሊገባህ አይችልም፡፡እናም ወዳጄ እይዞህ የዛሬው ፈተና የነገው ትምህርት ነው እና፡፡

#መልካም_ቀን

@yederasiyanbet
2.3K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:14:55 #የሶስት_ጠቢባን_አባባሎች

“ለሶስት ችግሮች ሶስት ሃሳቦችን ትዕዛዝ አድርገን መያዝ ይገባናል፣ እነዚህም፡-ከረጅም ጊዜ በፊት በእኔ ላይ በነበረው ያ ግብ፣ በእግዚአብሔርና በእጣ ፈንታ ተማምኛለሁ፡፡
አልወድቅም እከተላለሁ፣ ቁርጠኝነቴ ቢደክም እንኳን መጓዜን እቀጥላለሁ፡፡”
#ክሊያንተስ

“የሚያስፈልገውን ብቻ የያዘ እሱ ጠቢብ ነው፤ በአማልክቱም ተባርኳል።”
#ኢዩሪፒደስ

“አማልክቱን የሚያስደስት ከሆነ፣ ይሁን፡፡ ምናልባት ይገድሉኝ ይሆናል፣ ግን ሊጎዱኝ አይችሉም፡፡”
#ፕሌቶ

እነዚህ በኤፒክቴተስ ስራ ውስጥ የተጠናቀሩ ሶስት ጥቅሶች፣ ከታሪክ ባሻገር በጥበብ ውስጥ የመቻቻል፣ እንደ ሁኔታው የመሆንና በመጨረሻም የመቀበልን ጭብጥ የሚያሳዩ ናቸው፡፡

ክሊያንተስና ኢዩሪፒደስ መድረሻና እጣ ፈንታን መቀበልን ቀላል ለማድረግ የሚረዱ ሀሳቦች አድርገው ያቀርባሉ፡፡ አንድ ሰው በእግዚአብሔርም ይሁን በአማልክት ላይ ታላቅ ወይም ከፍተኛ የሆነ እምነት ካለው፣ ከእቅዱ በተቃራኒ የሚባል ነገር የለም፡፡

በአምላክ ባታምንም እንኳን፣ በተለያዩ የዩኒቨርስ ህግጋት ወይም በሕይወት ኡደት እንኳን ጥቂት ምቾት ልታገኝ ትችላለህ፡፡ በእኛ ላይ እንደ ግለሰብ የሚከሰተው ነገር በዘፈቀደ የሚሆን ወይም የሚያናድድ ወይም ጨካኝ ወይም ሚስጥራዊ ሊመስል ይችላል፤ እይታችን በትንሹም እንኳን በሚገለጥበት ጊዜ ግን እነዚህ ሁኔታዎች እንዲያውም ፍጹም በሆነ ሁኔታ ትርጉም ያላቸውና ስሜት የሚሰጡ ሆነው እናገኛቸዋለን። መጥፎውም የሆነው ለምክንያት ነው።

#ዛሬ_ይህንን_እይታ_እንለማመድ፡፡ የተፈለገም ይሁን ያልተጠበቀ ያ ሁኔታ እንዲሆን የታቀደ ነው። በተለይ በአንተ ላይ እንዲሆን የተፈቀደ እንደ ሆነ አስመስል፡፡ እንደዚያ ከሆነ እና የሆነው ሁሉ መሆኑ ካልቀረ እጣፈንታህን አትታገለውም፣ ትታገለዋህ?

@yederasiyanbet
2.3K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:31:09 . ዛሬ በአድናቆት አጅቦ የሚከተለኝ ሕዝብ ነገ ለመሰቀል ስሄድ ደግሞ - አጅቦ ይከተለኛል፡፡

ናፖሊዮን


@yederasiyanbet
3.2K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:31:09 አንቺ እፉዩ ገላ....
ይህ ላባሽ ገለባ..
ተከተይኝ አትበይ
ገደል እንዳልገባ..
እፍፍፍ....ሂጂ ብረሪ..
ከኔ ላያፀናሽ አትደናበሪ..
እፍፍፍ ሂጂልኝ በቃ
ራቂ ከነፍሴ..
ተስፋ ነው መናኖሬ
አንድ ሀቄን ታቅፌ...
ያዉቃል ባለነፍሴ
መኖርሺን አልሻም...
ሚዛን ላትደፊ
ሂጅ ከኔ አታመሽም...
ሂጂልኝ ከነፍሴ
ዘመናት እራቂኝ...
በነሽ እስክትጠፊ
ካቅምሽ አታቃይኝ! ሂ...ጂልኝ

ገጣሚ #ህይወት

@Yederasiyanbet
2.8K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:27:58 የትኛውን ግጥም ይበልጥ ወደዳችሁት?ላይክ በማድረግ እንዲሁም ሌሎች ወዳጆቻችሁን ወደ ቻነሉ በመቀላቀል ተሳተፉ።በቅድሚያ 60 ላይክ ለሚደርስ ተወዳዳሪ ሽልማታችን እንደተጠበቀ ነው።
@gitmv
2.5K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ