Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 24

2022-09-27 23:27:29 #መንገድ_አለ!

ለእያንዳንዱ ውድቀት ምትክ የሚሆን ድርጊት አለ፤ ያለብህ መፈለግ ብቻ ነው።

መሰናክል ሲያጋጥምህ ሌላ መንገድ ተጠቀም።

እንቅፋት ወይም መሰናክል ባጋጠመህ ጊዜ ቆም ብለህ እንዴት በዙሪያው ወይም በላዩ ላይ ወይም በውስጡ ማለፍ እንደምትችል አሰላስል።

ለእያንዳንዱ መዘጋት ያንን እንቅፋት የምታልፍበትን ሶስት የተለያዩ ስልቶችን አምጣ። ሊሰሩ የሚችሉ ብዙ ዘዴዎች አሉ፤ የምታገኛቸው ግን እነርሱን ለመፈለግ ጊዜ ከወሰድክ ብቻ ነው።

በአስተሳሰብህ ሁልጊዜ መፍትሔ ተኮር ሁን፤ የሚሰራ መንገድ እስክታገኝ ድረስ ፅና። አስቸጋሪ ሁኔታዎች የተሻሉ ነገሮችን ለማግኘት መልካም አጋጣሚዎች ናቸው፤ ወደ ታላቅ ልምምድ የሚወስዱን መረማመጃዎች ናቸው ...

#እነሆ_የወዳጅ_ምክር- ብራይን አዳምስ እንዳለው አንድ በር ሲዘጋ ሁልጊዜም ሌላኛው ክፍት ነው። የተፈጥሮ ህግ ሚዛንን ለመጠበቅ ይህ ሊሆን ግድ ነው።

የተዘጋውን በር ብቻ አትመልከት፤ ዞር ብትል የተከፈተም በር አለ፡፡

በተከፈተው በር ያውልህ፡፡


  
202 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 23:29:51 ቼም የማይረሳን-የዓለማት ጌታ
ጆቹ ነንና-ማይተወን ቀን ማታ
ለፈው እድሜ ላይ-ሌላ ዓመት ጨምሮ
ንም ብንበድለው-በይቅርታ ምሮ
.
.
ዲሱ ዓመት ላይ-ሰናይ ያድርግልን
ግሪ ላለው ማስተርስ-ትንሽ ላለው ትልቅ-አብዝቶ ይስጥልን
ጋት ችግሮችን-ከኢትዮጵያ ምድር-ፈፅሞ ያጥፋልን
.
.
ምና ያየነውን- ችግራቱን ሁሉ
ልካም ይተካቸው-ይረሱ ይጣሉ
ህትና በርክቶ-ሃዘን እንዲጠፋ-እስኪ አሜን በሉ
2015
ሮቤል
1.0K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 23:29:51 ልረሳሽ እየጣርሁ ነው
(በእውቀቱ ስዩም)
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትፀንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ መሀል፥ ያንቺን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው፥ ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርሁ ነው::
መጣ፥ መጣ ፥ መጣ ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ አለ
ስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ፥ ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እጣርሁ ነው ::
የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደ ብስል ሾላ ፍሬ ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
አዲስ ሰማይ ይነቃል፥
እንኳንስ የግርሽ ኮቴ ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው ።
(የማለዳ ድባብ)
1.0K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 10:10:51 ዛሬ አንድ በመንገድ ላይ ከእይኔ ቢጤ ጋ ያደረኩትን ንግግር ላካፍላችሁ

ትንሽ ለመዝናናት አስቤ ወደ መሃል ከተማ ወጣ ብዬ ሳለ አንድ በእድሜ ገፋ ያሉ ሰውዬ አይቼ ጠጋ ብዬ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ እንደው ቅር የማይልዎ ከሆነ ዛሬ እዚች ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ እርስዎ ጋር ሳወራ ብውል አልኳቸው ፈራ ተባ እያልኩ

ኧረ ምን ገዶኝ ልጄ እሽ ተቀመጥ እንደው እዚህ ከእኔ ጋር መዋል ጥቅም አይሰጥህም እንጂ አሉኝ እኔም ግድ የለም አባቴ ብዬ ስለ እኔ ብዙ ከጠየቁኝ እና ከነገርኳቸው በኋላ ስለ እራሳቸው እንዲያወሩኝ ፈልጌ እንደው አባቴ መልካም ፈቃድዎ ከሆነ ስለ እራስዎ ቢያጫውቱኝ አልኳቸው ሰውየውም ከብዙ ዝምታ በኋላ እንዲህ ሲሉ ማውራት ጀመሩ።

''የኔ ልጅ እዚች የምታያት ኬንዳ ቤቴ ለ21አመት ስተኛ ስቀመጥ ማንም ስለ እራሴ የጠየቀኝ ሰው የለም አንተ ለምን ጠየከኝ? አሉኝ። እኔም ለዚሁ እንዳልወጣሁ ስለማቅ ግልፁን ነገርኳቸው አባቴ እኔ የወጣሁ አየር ልቀበል ብቻዬን ልሆን ነበር እንጂ የእርስዎን ታሪክ ለመስማት አልነበረም አልኳቸው። ፈገግ ብለው እውነት አለህ የኔ ልጅ አሉና ከተቀመጡበት ወጣ ብለው ከጎኔ ተቀመጡና እንዲህ አሉኝ ''የኔ ልጅ እኔ በአንተ እድሜ እያለሁ ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ ከክፍልም ከትምህርት ቤትም ማንም አይበልጠኝ ነበር ነገር ግን ዛሬ ያለሁበትን ተመልከት'' አሉኝ።

እንደነገርኩህ እዚች የኬንዳ ቤት ውስጥ 21አመት ኑሪያለሁ አሁን እናንተ በምትማሩበት ትምህርት ደግሞ 25አመት ቆይቻለሁ አሉኝ እንዴ አባቴ አልኩኝ ደንገጥ ብዬ 25አመት ተምረዋል አልኳቸው? ልጄ የመጀመሪያ ድግሪዬን በዚህ በአዲስ አባባ ዩንቨርስቲ በማዕረግ ነው የተመረኩ አሉኝ።

ይህን ሲሉኝ አዕምሮዬ በጥያቄ ተሞላ ንግግራቸውን ቀጠሉ እናም ልጄ ለምርምር ወደ ውጭ ውጣ ተብዬ ሳለ ሃገሬን አለቅም እዚሁ መስራት እፈልጋለሁ ስል ሁሉም ፊቱን አዞረብኝ አሉኝ። ንግግራቸውን ቀበል አድርጌ እንዴት ማለት አልኳቸው ምን መሰለህ የኛ ሃገር ህዝብ የሚሰራለትን አይወድም ስታጎርሰው መንከስ ስራው አድርጎታል አሉኝ። ይብስ ግራ ገባኝ እና አባቴ ንግግርዎ አልገባኝም አልኳቸው እረጋ ብለው የኔ ልጅ አሉኝ በመንገድ ላይ ወድቆ የምታዬው ሰው ሁሉ እብድ ድሃ አይምሰልህ አሉኝ።

አንዳንዶች እውቀታቸው ከራሳቸው በላይ ሲሆን እብደትን መርጠው ከራሳቸው ጋር ያወራሉ አንዳንዶች ደግሞ ሆዳቸውን ለመሙላት ባላበዱት ላይ አበዱ እያሉ ይረማመዱባቸዋል አሉኝ። ይብስ ግራ ገባኝ እና አባቴ አንዴ አዕምሮየ ብዙ መያዝ ስለማይችል እባክዎ ንግግርዎን በፅሑፍ ልያዘው አልኳቸው ምን ገዶኝ የኔ ልጅ አሉኝ።

አባቴ ቆይ እዚህ እንዴት መጡ አልኳቸው ንግግራቸውን ማስታወሻዬ ላይ እየመዘገብኩ። የኔ ልጅ እንደ ነገርኩህ እዚህ ቆሽሸን ተጎሳቁለን ብታዬንም ውስጣችን ንፁህ የዘላለም ቤትን ናፋቂዎች ነን ለብዙወች የተራቆትን የተራብን ነን ነገር ግን ተራቁተን የለበስን ተርበን የጠገብን ሰዎች እኛ የመንገድ ነዋሪዎች ነን አሉኝ። ንግግራቸው መሬት ጠብ አይልም ከበድ ከበድ ያሉ ቃላት ይጠቀማሉ።

ዝም ብዬ መስማት ፈለኩና አይን አይናቸውን እያየሁ አንድ ባንድ ማዳመጥ ጀመርኩ። የኔ ልጅ አለም ጥሩ ስትላት መጥፎ፣መጥፎ ስትላት ጥሩ ትሆንልሃለች አቀባበልህ ግን ሁሉንም ይወስነዋል መጥፎ ነገር ሲገጥምህ እራስህን ማግለል ሳይሆን መጥፎ ነገርን መጋፈጥ መልመድ አለብህ ህይወት በብዙ ውጣ ውረዶች የተሞላች ነች አሉኝና ዝም አሉ።

ዝምታቸው በጣም ያስፈራል ግን ያለፈ ታሪካቸውን ለመስማት በጣም ጓጓሁ ግን እንዴት ብዬ ላስቀጥላቸው። ፈራ ተባ እያልኩኝ አባቴ ይቅር በሉኝ ያልሆነ ትዝታ ውስጥ ከተትኩዎ መሰለኝ አልኳቸው። አይ የኔ ልጅ እንደዛ አይደለም ትግስትህ ገርሞኝ ነው አሉኝና ንግግራቸውን ሊቀጥሉ ሲሉ አባቴ አልኳቸው ቆይ ቤተሰብ የለዎትም መጀመሪያ ስለ እራስዎ በደንብ ቢነግሩኝ እዚህ እንዴት እንደመጡ ስራወንስ ለምን እንዳቋረጡ በቃ በአጠቃላይ ስለ እራስዎ ይንገሩኝ አሁን ሳይዎ ምንም የአዕምሮ ችግር እንደሌለብዎ እየተረዳሁ ነው እና ለምንድን ነው እዚህ የሚኖሩት አልኳቸው።

እረጋ ብለዉ ንግግራቸውን ቀጠሉ ተወልጄ ያደኩት እዚሁ አዲስ አበባ ነው። ቤተሰቦቼ በሙሉ ካናዳ ነው የሚኖሩት እኔ የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ነው ጠቅልለው የሄዱ ቤቱንም ሁሉንም ነገር ለእኔ ነው ጥለውት የሄዱ። እኔ በጊዜው ከኢትዮጵያ የመዉጣት ፍላጎት ስላልነበረኝ አላስገደዱኝም ነበር አሉኝ።

እንዴት ከነሱ ተለይተው አልከበደወትም እድሜዎም ትንሽ ነው እሚሆን በዛ ሰዓት እና ምን ተገኝቶ ነው ከካናዳ ከቤተሰብዎ ተለይተው እዚህ የቀሩት አልኳቸው። ፈገግ አሉና ቤተሰቦቼ በአንድ ወቅት የሆነ ቦታ ለእረፍት ከአዲስአበባ ወጣ አድርገውን ነበር እና በዚያ ቦታ ከኢትዮጵያ የማያስወጣ ነገር ፈጣሪ አሳየኝ አሉኝ እና ፀጥ አሉ።

እንዴ ምን ቢሆን ነው? ብዬ ምንድነው አልኳቸው? መልስ የለም ትኩር ብዬ ሳያቸው ትዝታ ውስጥ እንደገቡ ተገነዘብኩና ዝም አልኩኝ። ከትዝታቸው ተመለሱና ፈገግ ብለው እንዲህ አሉኝ...
ክፍል 2...ይቀጥላል


ሼር

ተቀላቀሉን

@yederasiyanbet
@yederasiyanbet
@yederasiyanbet
@yederasiyanbet
1.7K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 10:10:05 አሰኘኝ ወደ እናቴ ሆድ ዳግመኛ እንደገና  መግባት
ምትፈልገኝን አይነት ሴት ሆኜ እንደአዲስ ለመሰራት።
ፈለኩኝ ሻትኩኝ መመለስ
የልጅነት ወዜን ማደስ።
ተመኘው መቀደድ መጥፋት
ልክህ ሆኜ ለመሰፋት።
ግና....
አይቻለኝምና መሟሟት እንደ ባህር ጨው
የማልዳስስህ አካሌ ሁሌ ምትኖረው በሀሳቤ ነው።
@Nillionaire_0
1.5K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 21:59:58 ​ . . .እኔና አንቺ ማለት እሳት እና ብረት ግለን የተዋሃድን ቀልጠን የተስማማን ዳግም ላንለያይ አንዴ የተጣመርን ሰምና ወርቅ ነን።
. . .አፈቅርሻለው. . .

◆ ─━━━━ ⊱✿⊰ ━━━━─
# ༒︎༆
┈••◉❖◉●••┈
🇯 🇴 🇮 🇳 𝐔 @yederasiyanbet
3.2K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 21:59:58 ​​​​​​​​​​ ​​.......... ሄ ዋ ን ‍..........
​​​​​​​​
ክፍል

◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ

ምንም ማስታወስ አልቻልኩም የማስታውሰውም ነገር የለም ምክንያቱም እኔ እንዳላጠፋሁት እርግጠኛ ስለሆንኩ
በዚህ ሀሳብ ላይ ሆኜ ማክ በር አንኳክቶ ገባ ማሬ ምን ሆነሽ ነው ሰላም አይደለሽ አለኝ አዙ የነገረችኝን ቴክስቱን ማን እንዳጠፋው ሳላውቅ ልነግረው አልፈለኩም እ..... ..ደና አይደለሁም ማክ ምን ብዬ እንደምነግርህ አላውቅም የደበቅኩህ ነገር ነበር አልኩ እየተንተባተብኩ ንገሪኝ ምን ደብቀሽኝ ነበር አለ በተጨነቀ አይነት ስሜት እያየኝ ማክዬ እንዳትቆጣኝ አልኩት አልቆጣም ንገሪኝ ምን ተፈጠረ ምንድነው የደበቅሽኝ
ማክ ከየት እንደምጀምርልህ አላውቅም ጥፋት ይሁን መልካም ላንተ ሳልነግርህ ከወራት በፊት የናቴ ጓደኛ ጋር ሄጄ ነገር
ብዬ ቀና ብዬ አየሁት ቀጥይ በሚል አስተያየት ሲመለከተኝ ከናቴ ጓደኛ ጋር እንዳወራንና በማግስቱ በማላውቀው ቁጥር ቴክስት እንደተላከልኝ አሁን ቴክስቱን ላገኘው እንዳልቻልኩም ጭምር ነገርኩት ምንም ባለመገረም ስሜት ነበር የሚያዳምጠኝ ስጨርስ ምን እንደሚለኝ ለመስማት በጉጉት እጠብቀው ጀመር
ሄዊዬ ቆይ ይሄ ነገር ለምን አይቀርብሽም ለምን አዲስ ህይወት "ሀ" ብለን አንጀምርም? በርግጥ የእናትሽ ጓደኛ ጋር እንደሄድሽ አላውቅም ግን ሌላ ተጨማሪ ቴክስት ካንድ አይነት ቁጥር ተልኮልሽ ነበር አንቺ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ነበርሽ በወቅቱ ከፍቼ ሳየው አባቴ አንቺን የሚያገኝበት አጋጣሚ እየፈለገ እንደሆነ ስለተረዳው አጠፋሁት ቁጥርሽን ከየት እንዳመጡ ልጠይቅሽ ነበር ግን የባስ እንዳላስጨንቅሽ ስላሰብኩ ተውኩት
አንቺም ከዛ በኋላ የረሳሽው መስሎኝ ነበር ስላልጠየቅሽ እና አሁን በምን በምን ትዝ አለሽ አለኝ በውስጤ ተመስገን ማክ ከኔ ጋር ነው ምንም አልዋሸኝም አልኩኝ ለደቂቃ ምንም ሳልናገር ቆየሁ በያ ንገሪኝ አለኝ ማክ ምንድን ነበር ሁለተኛው መልዕክት አልኩት "ይሄ የመጨረሻ እድልሽ ነው ያባትሽን ሚስጥር ማወቅ ከፈለግሽ በላክንልሽ አድራሻ ጠዋት 4 ሰዓት ነይ" ነበር የሚለው ይሄን መልዕክ ብታይ ኖሮ በርግጠኝነት ሄደሽ እራስሽን አባቴ መዳፍ ላይ ትጥይ ነበር አለኝ ማክ መሄድ ነበረብኝ ሁኔታው ከምታስበው በላይ አሳሳቢ ነው ዛሬ አዙ ጋር ደውዬ ሚስጥሩን የያዘው ፋይል ሲዲ እንደሆነ ነግራኛለች ይሄ ሲዲ ደግሞ እኔ እጅ ከገባ አባቴን እኔ ራሴ እንደሆንኩ የምበቀለው ሲያወሩ ሰምታለች፡፡ እኔ እዚህ ሲዲ ውስጥ ምን እንዳለ ሳላውቅ እንቅልፍ አይወስደኝም ምንድነው ሚስጥሩ እራሴ ሊፈነዳ ነው እባክህ አግዘኝ የኔ ፍቅር አልኩት ማክ ከተቀመጠበት ተነስቶ አቅፎ ያፅናናኝ ጀመር በቃ መፍትሄ አናጣም ትንሽ ብቻ ታገሺ እራስሽን ለማረጋጋት ሞክሪ ምን ይመስልሻል ትንሽ እንድትረጋጊ ሁኔታዎችንም ተረጋግተን ለማሰብ አንድ ሳምንት ወጣ ብለን ብንመጣ አለኝ ሀሳቡ ጥሩ መስሎ ታየኝ ወዴት እንሂድ አልኩት አሁንም ግራ እንደተጋባሁ ነኝ ዱባይ ደርሰን እንምጣ እስከዛ ነገሮችን በደንብ የምናስብበት ጊዜ ይኖረናል በዛውም ካለንበት ጭንቀት ትንሽ እናርፋለን አለኝ በሀሳቡ ተስማማሁ ከሳምንት በኃላ ዱባይ ሄደን በጣም አሪፍ የሚባል ጊዜ እያሳለፍን ነው ለጊዜውም ቢሆን ሁሉንም ነገር እረስቼዋለሁ ማክ ወደበፊቱ ማንነቴ በመመለሴ በጣም ደስተኛ ሆኗል ድንገት አየሽ አይደል ሁሉንም ነገር ጥለን ወደ አውስትራሊያ ብንሄድ ሁሉን ነገር መርሳት እንደምንችል አለኝ ማክዬ ለጊዜው መርሳት ስለፈለኩና አንተም ማስከፋት ስላልፈለኩ እንጂ እስከመጨረሻው ማንነቴንና ያባቴን የተደበቀ ማንነት እረስቼ መኖር አልችልም
በተለይ ጉዳዩ ከኔ ጋር እንደሚያያዝ ካወቅኩ በኃላ ይበልጥ የማወቅ ፍላጎቴ ጨምሯል ይህን ጉዳይ እልባት ካገኘሁለት በኃላ የፈለክበት እንሄዳለን አልኩት ማክ ይሄን ሲሰማ ሀሳቤን እንደማልቀይር ስላወቀ በቃ እሺ እኔም ይሄ ነገር ሰላም እየነሳኝ ነው ስለዚህ ወደኢትዮጵያ ስንመለስ አብረን መፍትሄ እንፈልጋለን ግን አንድ ነገር ቃል ትገቢልኛለሽ አለኝ ምንድነው ማክ የፈለግከውን አልኩት በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮኝ እንደሆነ ሲነግረኝ በመደሰት
ያባትሽ ሚስጥር ምንም ሆነ ምን ጠንካራ እንደምትሆኚና ምንም ለማድረግ እንደማትሞክሪ እንደዛ ሲለኝ ማክ የሆነ የምታውቀው ነገር እንዳለ ይሰማኛል አልኩት ሄዊዬ እንደዛ ማለቴ አይደለም ግን ያው ከሁኔታዎች አንፃር ጉዳዩ እንደሚከብድ በመጠርጠር ነው ብሎ አቅፎ ሳመኝ ነገሩ ባይዋጥልኝም ከማመን ውጪ አማራጭ አልነበረኝም
የዱባይ ቆይታችንን ጨርሰን እንደተመለስን.......ይቀጥላል


@yederasiyanbet
@yederasiyanbet
2.8K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 21:58:47 አሰኘኝ ወደ እናቴ ሆድ ዳግመኛ እንደገና  መግባት
ምትፈልገኝን አይነት ሴት ሆኜ እንደአዲስ ለመሰራት።
ፈለኩኝ ሻትኩኝ መመለስ
የልጅነት ወዜን ማደስ።
ተመኘው መቀደድ መጥፋት
ልክህ ሆኜ ለመሰፋት።
ግና....
አይቻለኝምና መሟሟት እንደ ባህር ጨው
የማልዳስስህ አካሌ ሁሌ ምትኖረው በሀሳቤ ነው።
@Nillionaire_0
2.4K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 12:20:24 እሷን!

አይኔ አይኗን እያየ ልቤ እየነዘረ
እኔ በማላቃው መንፈሴ እየናረ
በስውር ሰመመን ለቤን እያስማለ
እሷን ያስወደደኝ አንዳች ሀይል አለ ።

# ያሬድ.ብርሃነ
3.1K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 12:20:24 ስንኝ ቋጠሮ

ቅኔ ነው ስንኜ ሀገር የቋጠረ
የምጥ ጩኸት ለቅሶ ለእውነት ያደረ
ምጧ ቢበረታ ህመሟ ቢያይልም
ግድ የለም በቅርቡ መውለዱ አይቀርም።

ስንኜ ሀገር ነው ሐሴት ቋጠሮየ
ትንሳኤን የዘለ ፋሲካ ለእምየ።

liul
2.7K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ