Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 21

2022-10-22 15:42:17 አመሏን አውቃለሁ ሰው አልምዳ አታውቅም
ተረተረት እጂ ሀሳብ ህልም የላትም
ስለወደፊቷ ትንሽ ብትረዳ፣
ተስፋ ቢኖራትም
አላሚዋን ጥላ ህልመኛዋን ጥላ ፣
የትም አትሄድም @gitmv
@hashuya
2.6K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 15:42:16 ሆነ ሰበር ዜና
ፈጣሪ ፈልጎት : ዛፉማ ሲፈጠር
ሰው ሊጠቀምበት : ለግልጋሎት ነበር
የሰውን ሞት ረሳን : ዛሬ ያ ቀረና
ዛፍን መትከልና መቁረጥ : ሆነ ሰበር ዜና
@gitimv
2.5K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 15:42:16 የሀገሬ እንግልት ልፋቷና አሳሯ
ምነው እንደ አንዲት ሴት
ዘጠኝ ብቻ ቢሆን የእርግዝና ወሯ
ደሟ ሳይፈስባት ምጧ ሳይበረታ
ከጥበበኛ ሰው
አዋልዳት ነበር በፍቅር በደስታ።
@gitmv
በአክሊሉ
2.5K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 15:40:30 ትናንት ዛሬ ቢሆን
ዓለም ወደ ኋላ ብትዞር

በምስራቅ ብትገባ የወትሮዋን ትታ
ቢቀየር ተመኘሁ የፀሀይ ዙረቷ

የትናንቱ ጭልምት በነበረ ንጋት
ስንቱን ባበረርኩት
አያሌውን ደሞ ከመንጎድ 
                   ባስቆምኩት          
ማርፈዴን እራሱ ምነው   
               ባስረፈድኩት።
@gitmv
2.4K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 12:50:15 መለየት ነው ቆርጦ
             መሄድ ነው እርቆ
ምንድን ነው የሙጥኝ
             ከሰው ሰው ተጣብቆ
@gitmv
           ባንተጊዜ
3.9K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 12:50:15 ጣትና ቅጣት

ብዕር ከወረቀት
ጣትም ከቀለበት
ተስማምተው እያረፉ
ምነው የሚስማሙ
ባለጣቶች ጠፉ

ልዑል
@gitmv
@gitmv
3.4K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 12:50:15 አሰኘኝ ወደ እናቴ ሆድ ዳግመኛ እንደገና  መግባት
ምትፈልገኝን አይነት ሴት ሆኜ እንደአዲስ ለመሰራት።
ፈለኩኝ ሻትኩኝ መመለስ
የልጅነት ወዜን ማደስ።
ተመኘው መቀደድ መጥፋት
ልክህ ሆኜ ለመሰፋት።
ግና....
አይቻለኝምና መሟሟት እንደ ባህር ጨው
የማልዳስስህ አካሌ ሁሌ ምትኖረው በሀሳቤ ነው።
@Nillionaire_0
3.2K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 21:13:20 #ይበልጣል
ከጉያሽ ተነጥዬ ከሳቅኩት ሳቅ፣
ይበልጣል ከእቅፍሽ ተገኝቼ የለበስኩት ማቅ።
ከአጠገብሽ ርቄ ካሳየሁት ፈገግታ፣
ይበልጣል ከጎንሽ ሆኜ የነበረው የእንባ መንታ።
እናም ነግርሻለሁ ካንቺ ስለይ ገና፣
ውበቴ ይጠፋል ጥርሴ ይቀራል መና።
ከንፈሬ ቢሸሽም አያምርብኝ ተድላ፣
አለም ምታንስብኝ ከሚዛኗ ጎድላ።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
3.1K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 21:13:20 #ውሃ_አጣጭ
ውሃ አጣጬ ምጠርግ ጉሮሮ፣
ማጣፈጫ ቅመም ለጣዕም አልባ ኑሮ።
የተራራ ስር ምንጭ ፈላቂ፣
ምጠብቅ ከደራሽ ከወሳጅ አሳሳቂ።
በጊዜ ዝቅጠት ያልደፈረሰች ወንዝ፣
እኔን የቀዳችኝ በመያዣው ጠርዝ።
ዘንበል ቢል ሸክሟ እንስራ፣
ኩልል ባለ ሕይወት ትፈካለች በፈጣሪ ስራ።
ስትል ከቸች ፈጥና ለጥሜ፣
ደ'ሞ እንዳልቀር ባክኜ ሰጥሜ።
ሽታዋ አሊያም መልኳ አይደለም ጉዳዬ፣
ስሟ መቼ ጠፋኝ የዚያች የገዳዬ።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
2.9K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 10:36:06 #ካልዳነ_ይሙት
መሃላሽ እንዳለ ካልዳነ ይሙት፣
ፍሬው ይበላል ለሰው ያሙት።
ከመደብ ቢሰሩት ቁራኛዬን አልጋ፣
የሙክቱ አጎዛው ላይ እንዴት ይንጋ።
ነጠላ ልብን ውስጥሽ እየመሰጠረ፣
የኔ አንጀት ተከቦ በስጋት ታጠረ።
የታመመ ሁሉ አፈርን ቢቀምስ፣
ማን ይይዝ ነበር የእግዜርን ቀሚስ።
እናም ተሳስተሻል እረኛዬ እርሱ፣
አያንቀላፋም ከቶ አይተኛም በስሱ።
ግና ያ የመንገዴ እንቅፋት፣
ወለል ብሎ አሳየኝ የፍቅርሽን ክፋት።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
90 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ