Get Mystery Box with random crypto!

#ካልዳነ_ይሙት መሃላሽ እንዳለ ካልዳነ ይሙት፣ ፍሬው ይበላል ለሰው ያሙት። ከመደብ ቢሰሩት ቁራኛዬ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#ካልዳነ_ይሙት
መሃላሽ እንዳለ ካልዳነ ይሙት፣
ፍሬው ይበላል ለሰው ያሙት።
ከመደብ ቢሰሩት ቁራኛዬን አልጋ፣
የሙክቱ አጎዛው ላይ እንዴት ይንጋ።
ነጠላ ልብን ውስጥሽ እየመሰጠረ፣
የኔ አንጀት ተከቦ በስጋት ታጠረ።
የታመመ ሁሉ አፈርን ቢቀምስ፣
ማን ይይዝ ነበር የእግዜርን ቀሚስ።
እናም ተሳስተሻል እረኛዬ እርሱ፣
አያንቀላፋም ከቶ አይተኛም በስሱ።
ግና ያ የመንገዴ እንቅፋት፣
ወለል ብሎ አሳየኝ የፍቅርሽን ክፋት።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)