Get Mystery Box with random crypto!

#ግት አይኖችሽ ውብ ናቸው ፍቅር አግተዋል፣ ለኔ እንባን አውርደው ዘርተዋል። ክንዶችሽ ብሩኮች መው | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#ግት
አይኖችሽ ውብ ናቸው ፍቅር አግተዋል፣
ለኔ እንባን አውርደው ዘርተዋል።
ክንዶችሽ ብሩኮች መውደድን ያጠነጠኑ፣
ሞልቶ መፍሰስ ነው የክብረትሽ መጠኑ።
ሰላምን ያዘንባል የልብሽ ንፅህና፣
የሙገሳን ሕይወት አትፈልጊ ዝና።
እዩኝ እዩኝ አትዪ አያምርሽ ደጁ፣
እንኳን የሰው የአራዊት ወዳጁ።
አመል የሌለብሽ ከሴት የማትቅበጠበጪ፣
መልስሽ አዎንታ ለሂያጅ ለመጪ።
አንቺን አደለም ወይ አምላክ እጁን ታጥቦ፣
የሰራሽ በኪነጥበቡ ለአይነት አስቦ።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)