Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 22

2022-10-08 10:36:06 #ግት
አይኖችሽ ውብ ናቸው ፍቅር አግተዋል፣
ለኔ እንባን አውርደው ዘርተዋል።
ክንዶችሽ ብሩኮች መውደድን ያጠነጠኑ፣
ሞልቶ መፍሰስ ነው የክብረትሽ መጠኑ።
ሰላምን ያዘንባል የልብሽ ንፅህና፣
የሙገሳን ሕይወት አትፈልጊ ዝና።
እዩኝ እዩኝ አትዪ አያምርሽ ደጁ፣
እንኳን የሰው የአራዊት ወዳጁ።
አመል የሌለብሽ ከሴት የማትቅበጠበጪ፣
መልስሽ አዎንታ ለሂያጅ ለመጪ።
አንቺን አደለም ወይ አምላክ እጁን ታጥቦ፣
የሰራሽ በኪነጥበቡ ለአይነት አስቦ።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
92 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 10:36:06 #ልስለምልሽ
አይቆጡም ከቶ የጀነት ጠባቂዎች፣
ደጃቸው ቢመጡ የአብርሃም ልጆች።
አያዩትም ጭራሽ እንደ ሃራም፣
ክፋት በቅን ልብ አይዘራም።
በቃ ከመስጂድሽ ልዋል ዘልቄ፣
እውን ስለሆነ በፍቅርሽ መውደቄ።
ሂጃብሽን ጠምጥሚ እኔ ልስለምልሽ፣
ምክንያቱም ይሄ ሁሉ ስለምወድሽ።
መሃመድ ያሉትን አስተምሪኝ ከቁርዓኑ፣
ልቤ አድልቷል በማፍቀር ሚዛኑ።
ሳውዲን አስጎብኚኝ ልዳሳት መዲና፣
ነፍሴ አንቺን በማምለክ ደንድና።
ልጠራ በእምነትሽ ልማል ወላሂ፣
ስለተሰጠሽኝ ላመስግነው እንደገና አላምዱሊላሂ።
ላስብሽ በእግሬ እጥፋት በዱኣዬ፣
ለሶላቱ ክዋኔ በምንጣፉ መስገጃዬ።
ልፁመው ይታጠፍ አንጀቴ በረመዳን፣
ለአላህ በመገዛት በኒካሽ ልዳን።
ከጌታ የተላክሽ ፋንታዬ ሃዋ፣
አደምሽ ቤት ሊሰራ አስገልብጧል አሸዋ።
#መኮንን_ዮሴፍ
እባክዎ ሼር ያድርጉ!!!
89 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 10:35:35 Watch "Fellynova xREMIX of popular music" on YouTube


82 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 13:57:10 ቄስ ይጥራው
ትዝ ይልሻል ውዴ አስታወሽ፣
የሞተው አካሌን ሬሳዬን የለወሽ።
ስምሽን ስጠራው ስምህን ቄስ ይጥራው ያልሽኝ፣
አፍ አውጥተሽ እንዲያ የረገምሽኝ።
ይኸው ዛሬ እርግማንሽ ደርሶ፣
በድኔን ሆኛለሁ ሰውነቴ ፈርሶ።
ሆዴ የተናገርሽው ጠብ አላለም፣
ከምላስሽም ፀጉር ከቶ አልተነቀለም።
ይሰማኛል ቄሱ ክርስትና ስሜን ሲጠይቁ፣
ዲያቆኖቹም ሁላ በፀሎት ሲደምቁ።
አንቺ ታውቂው የለ ንገሪያቸው፣
ክንፈ ገብርኤል ነው በያቸው።
ከንፈር ቀዳዳ አለው ነውና ወንፊት፣
የማይደርስ መስሎሻል ሲቀርብ ከሰው ፊት።
210 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 13:57:10 #ታሰግድ
እንደ
ታቦት ጽላት እንደ ቅዱሳኑ ምስል፣
ሰው ቢሳለማት ያመልካት ይመስል።
እንደ ሰሌን እንደ ስጋጃ፣
ወንድ ቢነጠፍላት ያለ መጋረጃ።
ታሰግድ ጀመረ ስድሳ አርባ ጊዜ፣
እኔም የማፈቅራት ገባሁ ከትካዜ።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
209 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 13:57:09 #ዘብትደር
ቅናት እላዩዋ ላይ ቤቱን ከገነባ፣
ዘብትደር እንግዲህ አይደለሁም ሌባ።
ከሰየመችው መቀላወጤን በአጉል ስርቆት፣
የጋራ ብሌን ይኑረን ያስመልክተን አፈራርቆት።
እንዲህ ከነበረ ቁመናው የውስለታ፣
ማወጇ ነውና ትንሹን ዱለታ።
በሏት ተመከሪ አሊያም ትቁም ጥበቃ፣
እኔ የለኝም ለራሴ ጠበቃ።
የመንጣሪ ተረት የሚለው ጠርጥር፣
እንዲያው ከምረው ፍፁም አታበጥር።
ትታው የእምነትን ሰላም መኝታ፣
እንቅልፍ እምቢ ካላት ጉያዬ ተገኝታ።
አዳሬ ከንክኗት ካልመሰላት ውሎዬ፣
ዘብትደር በቃ አላብድም ቀልዬ።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
203 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 13:57:09 #ካልዳነ_ይሙት
መሃላሽ እንዳለ ካልዳነ ይሙት፣
ፍሬው ይበላል ለሰው ያሙት።
ከመደብ ቢሰሩት ቁራኛዬን አልጋ፣
የሙክቱ አጎዛው ላይ እንዴት ይንጋ።
ነጠላ ልብን ውስጥሽ እየመሰጠረ፣
የኔ አንጀት ተከቦ በስጋት ታጠረ።
የታመመ ሁሉ አፈርን ቢቀምስ፣
ማን ይይዝ ነበር የእግዜርን ቀሚስ።
እናም ተሳስተሻል እረኛዬ እርሱ፣
አያንቀላፋም ከቶ አይተኛም በስሱ።
ግና ያ የመንገዴ እንቅፋት፣
ወለል ብሎ አሳየኝ የፍቅርሽን ክፋት።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
195 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 16:05:24 #ልስለምልሽ
አይቆጡም ከቶ የጀነት ጠባቂዎች፣
ደጃቸው ቢመጡ የአብርሃም ልጆች።
አያዩትም ጭራሽ እንደ ሃራም፣
ክፋት በቅን ልብ አይዘራም።
በቃ ከመስጂድሽ ልዋል ዘልቄ፣
እውን ስለሆነ በፍቅርሽ መውደቄ።
ሂጃብሽን ጠምጥሚ እኔ ልስለምልሽ፣
ምክንያቱም ይሄ ሁሉ ስለምወድሽ።
መሃመድ ያሉትን አስተምሪኝ ከቁርዓኑ፣
ልቤ አድልቷል በማፍቀር ሚዛኑ።
ሳውዲን አስጎብኚኝ ልዳሳት መዲና፣
ነፍሴ አንቺን በማምለክ ደንድና።
ልጠራ በእምነትሽ ልማል ወላሂ፣
ስለተሰጠሽኝ ላመስግነው እንደገና አላምዱሊላሂ።
ላስብሽ በእግሬ እጥፋት በዱኣዬ፣
ለሶላቱ ክዋኔ በምንጣፉ መስገጃዬ።
ልፁመው ይታጠፍ አንጀቴ በረመዳን፣
ለአላህ በመገዛት በኒካሽ ልዳን።
ከጌታ የተላክሽ ፋንታዬ ሃዋ፣
አደምሽ ቤት ሊሰራ አስገልብጧል አሸዋ።
#መኮንን_ዮሴፍ
እባክዎ ሼር ያድርጉ!!!
1.2K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 16:05:24 #ከኑግ_ጋር
ግዴለም ዓለሜ አብሬሽ ልወቀጥ ፣
በዘነዘናው ሽመል ከፊትሽ ልቀጥቀጥ።
ስህተት ከሆነ ካንቺ መገኘቴ፣
ክልክል ከተባለ ፍቅርሽን መመኘቴ።
ከኑግ ጋር እንደተደባለቀ ሰሊጥ፣
ምንም አይደል ብጨፈጨፍ ከሊጥ።
የጥፋትሽን ቅጣት ኃጥያትሽን ልካፈል፣
መውደድ ከታደሰ መከራሽ ሲፈለፈል።
ማን ያውቃል ሲጠፋ ዘይት፣
ይወለወልበት ይማሳል መደገኛ ጥይት።
ላይገርመው ላይደንቀው ትኩስ ቀልሃ፣
አፈር ላይ ያደገ ለጥ ያለ በረሃ።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
1.1K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 16:05:24 #ወንድምሽ_ያዕቆብ
ግዴለም ከቶ እህቴ የሺ፣
ብትመጪም ብትቀሪ ደርሰሽ ባትመለሺ።
ግና ከምሩ ያፈቅርሻል ወንድምሽ ያዕቆብ፣
ጥሎ የክህነቱን ውበት የጭንቅላቱን ቆብ።
ምንም እንኳ በሌላ ብትቆርቢ፣
ክረምቱን ታግሶ እስከሌላኛው ጥቢ።
ይጠበቅሻል በተስፋ መውደድን ደግሶ፣
አንቺን ልዕልቱን በልቡ አንግሶ።
ነሽና በሕይወቱ እንቅልፍ የመጀመሪያዋ ቀስቃሽ፣
የፍቅሩን ደውል ደውለሽ ያነቃሽ።
ሊታዘዝሽ ፈቅዷል በማሸለቢያው ዘመን ሁሉ፣
ሊታመንልሽ ተነስቷል በእምነት በቃሉ።
በስል ጥርሶቹ በታጠፈው አንጀቱ፣
ባልቆረሰው ቁርስ በስብር አንገቱ፣
መሃላውን ይሰጥሻል ከነስህተት ምኞቱ።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
1.0K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ