Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 28

2022-08-20 17:43:58 በክረምት............

በክረምት በብርዱ፥ በናፍቆት ረመጥ፤
በሞኝ አበስብስ ውስጥ፥ ሞኝ ልቤ ሲሰምጥ፤
ከንፋስ ሽውታ፥ከመብረቅ ብልጭታ፤
በሀሣብ ትመጫለሽ፥ እንደ ድንገት ለአፍታ።
በአል እስኪመጣ፥ ዘመን ተቀይሮ፤
በአጥር እስክንዘል፥በጀርባ በጓሮ፤
ደግሞ እስክንጠራ፥ ት/ቤት ቢሮ ፤
እንዴት አድርጎሻል፥በክረምቱ ኑሮ፤
ትዝ አላለሽም ወይ፥የመምህሩ እሮሮ፤
እኔ.............….........
ባይኖረኝም ፍቅር፥ለትምህርቱ ከቶ፤
ቀኑን እጠብቃለሁ፥እስኪነጋ መሽቶ፤
በጋው እስኪመጣ፥ክረምቱን ረቶ፤
እንችን እስኪያሳየኝ፥አምላኬ ራርቶ።

ተፃፈ በ አቅሌስያ ፋንታሁን (@eyulka፣@akli03)
3.0K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 17:43:57 የብሄ ብርሃን ለኛም በራልን×፪
እያልክ ብሄ በሉ የደብረ ታቦርን ተአምር ስታውጅ
በድምፅክ ብለ'ይ መሆንክን የኔ ወዳጅ
ስትል ብሰማ ክፈት በለው በሩን
እንኳን አደረሳቹ ልትል እንኳን አደረሰክ ብዬ ከፈትኩልህ ልቤን
ለኔም መጥተሃልና ሆነህልኝ ብርሃን
ጅራፋን ስታጮህ ፡ እዚ ቤቶች እያልክ ሰፈር ስታካልል
ፍቅርህን ልታደርስ እኔም ቤት ደርሰሃል

እዚ ማዶ አንድ አብሽ እዛም ማዶ አንድ አብሽ
የዚህ ቤት ጌታ ወርቅ ለባሽ .......................... እያልክ
የቤቶቼን ጌታ አንተ ስታሞግስ  ..........እኔን እያማለልክ
በስርቆሽ ጨዋታ በአይን ተግባቦት
በብሄ ሙልሙል በሆያ ሆዬ ዜማ
የፍቅርህን ድርሳን ከልቤ ብታደርስ ልቤን ልታሸፍት
አባዬ እማዬ እህት ወንድሞቼ
መላው ሳይገባቸው ፍቅርን ተቋደስን
ሆያ ሆዬ ብለውን

ሆይሼ ሆይሼ
ልምጣ ወይ ተመልሼ
በአመት አንድ ቀን ብቅ ብትልልን
ተመኘሁ ሁልጊዜ ብሄ አንዲሆን
ተመላልሰክ አንድትመጣ ሆያ ሆዬ እያልክ
ከልቤ ሙዳይ ከቤቴ ደጃፍ እንዳይክ

እንድትመርቅ
አመት አውደአመትን
የብሄ ብርሃንን
የኔና ያንተን  ፍቅርን
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተጻፈ በ
            ፡ Metadel_Amel

መልካም ብሄ ;)
2.4K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 17:43:57 አንቺ ጋር ስመጣ
""""""""""""""""""""""""""""""

ዣንጥላም አልሻም.....
ዝናቡን አልፈራ፣ ከቶም አይበግረኝ
ፍቅርሽ አይደለም ወይ...
ከዝናቡ በላይ፣ የሚያረሰርሰኝ።

/ ልጅ_ወርቅነህ.. /


ጆይን/join/

@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
1.8K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 17:43:57 ቀጠሮ በክረምት
ጠዋት ተነስቼ ጀመርኩኝ ዝግጅት
አንድ ቀጠሮ አለኝ መቅረት ማልችልበት
የቀጠሮ ሰዓት ደርሶ እስካገኘው
ጠረኑን አሽትቼ ቀርቤ እስካቅፈው
የልጅነት ፍቅሬን አይኑን እስከማየው
እንዴት እንደ ጓጓው ትርታዬ ያወራል
እጅ እግሬ ታስሮ ውስጤ ግን ቸኩሏል
ንፁ አየር ፍለጋ መስኮቴን ከፍቼ
ሰማዩን አየሁት ሽቅብ በአይኖቼ
መብረቁ ያስፈራል ሰማዩም ጠቋቁሯል
ልክ እንደኔ ስሜት አንዳች ነገር አዝሏል
ሰዓቴን አይቼ ዘጋሁት መስኮቴን
ከቤቴ ልወጣ ጀመርኩ እርምጃዬን
ያጥቁሩ ሰማይ ደመናን ያዘለው
በእኔው ሰዓት ላይ ዝናቡን ለቀቀው
ያሁሉ ህልምና የሁሉ ዝግጅት
የልጅነት ፍቅሬን የማየቱ ጉጉት
በጓርፉ አለፈ አይ ቀጠሮ በክረምት
Noa
1.8K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 17:43:57 አደራ ለቡሄ

ክረምቱ ዝናቡን ያለልክ ሲያፈሰው
በቤቱ ሲታደም ጉብል አዋቂው ሰው
ናና በፉጨትህ ጥራኝ እወጣለሁ
አረማ ጉልጉሎ ወይ እንጨት ለቀማ
በወጣሁኝ ቁጥር ባንተ ከምታማ
አንተ ብቅብለህ ድምፅን አሰማ
አባባ ሳይሰማ እማማም ሳታየኝ
አንዴ ብቅ ብለህ አይንህን አሳየኝ
ይህ ሁሉ ካልሆነ አንዱም ካልተሳካ
ፎቶህን ስደደው አቅፌው ልተኛ
ይሄም ካልሆነልህ ከጠፋህ መፍትሔ
ያው ነሀሴም አይደል እንዳትቀር ለቡሄ
የምትወደውን ሙልሙሉ ስለምሰራ
እንዳትቀርብኝ አንተ ልጅ አደራ
ሆያ ሆየ እያልክ የመጣህልኝ እለት
አይኖቼ ይበራሉ አገኛለሁ ጉልበት
ሽንሽኔን ለብሼ ደር እና አምባሬን አጌጥበታለሁ
ሆያያ ሆየ እያልክ ና እጠብቅሃለሁ
ቡሄ ምክንያቴ ነው እኔ አንተን ለማየት
ሳላይህ እንዳይልፍ እንዳይልቅ ክረምት

እመጣለሁ

ወንዙን ተራራው ባህሩን አልፌ
ለፍቅራችን ስል ውዴ ተንሰፍስፌ
እኔም ናፍቀሽኛል አይንሽን አያለሁ
ሆያሆየ ብየ እመጣልሻለሁ
አባታሽ ሳያዩኝ ወንድምሽ ሳይገለኝ
ላንቺ የምነግርሽ አንድ መልክት አለኝ
ግን አሁን አይሆንም ያኔ እነግሻለሁ
የኔ አለም ጠብቂኝ ሆ ብየ እመጣለሁ
የጌቶች ጌታየን ፍቃድ ጠይቂያለሁ
ገና ሳትነግሪኝ መንገድ ጀምሪያለሁ
ሆያሆየ ብየ እመጣልሻለሁ



.... @nitsuti1419
1.7K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 16:52:22 ◈ ━━━━ ◈

የኔ........ ስልሽ

የኔ ፍቅር ስልሽ
እንባ ያረገዘዉ ይሄ አይኔ ይደርቃል፣
መኖር የደከመዉ አካሌ ይወናል፡፡

የኔ ውድ ስልሽ
እርካሹ ስሜ ባንቺ ይወደዳል፣
ፅልመት የለበሰዉ ህይወቴ ይበራል፡፡

የኔ ቆንጆ ስልሽ
.............ጨለማዬ ነግቶ፣
በቋጥሮ የቆየው ደስታዬ ፈንድቶ፣
ዘላለም የሚቆይ ብርሀንን ይረጫል፣
መቼም ላይጠወልግ ደሰታዬ ያብባል፡፡

የኔ ፍቅር ስልሽ ስሜት ይፀነሳል፣
የኔ ውድ ስልሽ ፍቅር ይወለዳል፡፡
የግሌ አድርጌሽ
የኔ ብቻ ስልሽ
መሞቴን ረስቼ
ይኼው በነፃነት መኖር ጀመርኩልሽ፡፡

ክበር ተመስገን

@yederasiyanbet
1.8K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 16:52:21 ያቀን
እንደ ሰማይ ራቀን
እንደ ሞተ ወዳጅ ናፈቀን
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ትርጉም ኖሮን ምንኖርበት
ምክንያት ይዘን ማንሞትበት
ህይወት ጣዕሟን ምናይበት
ነን ያልነውን ምንሆንበት
ያቀን....

ዛሬን ኖረን ነገን ጓግተን
አዲስ ጠዋት ተመኝተን
ከርሞችንን ሳንጠላው
እኛው እኛን ሳንጣላው
አሉ ሲሉን አለን ብለን
ባምላክ ፍቅር ተጠልለን
ለምን ብለን ሳንሞግተው
"እርሱት ሲሉን የምንረሳ"
ተውት ሲሉን የምንተው
ምንሆንበት.....

ካጀብ ማዕብል ተነጥለን
ሸክማችንን ላምላክ ጥለን
እኛን ሆነን እኛን መስለን
እንዴት ብለን ሳንጠይቀው
"ያልፋል ያሉት እያለፈ"
ሁሉን እግዜር እያወቀው
ምንኖርበት.....

ዕርስታችን ሳይታረስ
የዘሩትን ሳንለቅም
ገነት ደጇን ስንናፍቅ
ኗሪ አለምን ሳንንቅም
ላለመሞት አንዲት ምክንያት
ለመኖርም አንዲት ጥቅም
ምንይዝበት...

ያቀን
እንደ እናት ጡት ተነጠቀን
እንደበራች ፀሃይ ራቀን
እንዳ'ባት ክንድ ተናፈቀን

[ ቶማስ ትግስቱ ]
@yederasiyanbet
2.1K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:40:58 የባከነ ሌሊት!!!!
(በእውቀቱ ስዩም)
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ::
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ::
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው::
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ::
አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ::
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ::
1.1K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:40:50 ስሚኝ
እወድሽ ነበረ ፍቅሬ ባይገባሽም፣
የኔ መዉደድ ላንቺ እውነት ባይመሰልሽም
አይንሽ እንባ ሲያዝል ሆድሽ ባር ባር ሲለው፣
እኔም ከፍቶኝ ነበር እውነቱ ይሄ ነው።
@gitmv
ምህረት
26/10/2014
912 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:40:50 የፈጠርከው ፍጡር ~ከሰይጣን ሰይጥኖ
ልጆችህን ሲገለን ~ህግጋትክን ተቃርኖ
ስለምን ዝምአልከው~ ስንቴስ እንቀጣ
ውረድና ፍረድ !!
አልያ ህግክን ሻርልን ~እራሳችን እንድንቀጣ!!
@gitmv

#bluefish
921 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ