Get Mystery Box with random crypto!

ያቀን እንደ ሰማይ ራቀን እንደ ሞተ ወዳጅ ናፈቀን ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ያቀን
እንደ ሰማይ ራቀን
እንደ ሞተ ወዳጅ ናፈቀን
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ትርጉም ኖሮን ምንኖርበት
ምክንያት ይዘን ማንሞትበት
ህይወት ጣዕሟን ምናይበት
ነን ያልነውን ምንሆንበት
ያቀን....

ዛሬን ኖረን ነገን ጓግተን
አዲስ ጠዋት ተመኝተን
ከርሞችንን ሳንጠላው
እኛው እኛን ሳንጣላው
አሉ ሲሉን አለን ብለን
ባምላክ ፍቅር ተጠልለን
ለምን ብለን ሳንሞግተው
"እርሱት ሲሉን የምንረሳ"
ተውት ሲሉን የምንተው
ምንሆንበት.....

ካጀብ ማዕብል ተነጥለን
ሸክማችንን ላምላክ ጥለን
እኛን ሆነን እኛን መስለን
እንዴት ብለን ሳንጠይቀው
"ያልፋል ያሉት እያለፈ"
ሁሉን እግዜር እያወቀው
ምንኖርበት.....

ዕርስታችን ሳይታረስ
የዘሩትን ሳንለቅም
ገነት ደጇን ስንናፍቅ
ኗሪ አለምን ሳንንቅም
ላለመሞት አንዲት ምክንያት
ለመኖርም አንዲት ጥቅም
ምንይዝበት...

ያቀን
እንደ እናት ጡት ተነጠቀን
እንደበራች ፀሃይ ራቀን
እንዳ'ባት ክንድ ተናፈቀን

[ ቶማስ ትግስቱ ]
@yederasiyanbet