Get Mystery Box with random crypto!

◈ ━━━━ ◈ የኔ........ ስልሽ የኔ ፍቅር ስልሽ እንባ ያረገዘዉ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

◈ ━━━━ ◈

የኔ........ ስልሽ

የኔ ፍቅር ስልሽ
እንባ ያረገዘዉ ይሄ አይኔ ይደርቃል፣
መኖር የደከመዉ አካሌ ይወናል፡፡

የኔ ውድ ስልሽ
እርካሹ ስሜ ባንቺ ይወደዳል፣
ፅልመት የለበሰዉ ህይወቴ ይበራል፡፡

የኔ ቆንጆ ስልሽ
.............ጨለማዬ ነግቶ፣
በቋጥሮ የቆየው ደስታዬ ፈንድቶ፣
ዘላለም የሚቆይ ብርሀንን ይረጫል፣
መቼም ላይጠወልግ ደሰታዬ ያብባል፡፡

የኔ ፍቅር ስልሽ ስሜት ይፀነሳል፣
የኔ ውድ ስልሽ ፍቅር ይወለዳል፡፡
የግሌ አድርጌሽ
የኔ ብቻ ስልሽ
መሞቴን ረስቼ
ይኼው በነፃነት መኖር ጀመርኩልሽ፡፡

ክበር ተመስገን

@yederasiyanbet