Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​ ​​.......... ሄ ዋ ን ‍.......... ​​​​​​​​ ክ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

​​​​​​​​​​ ​​.......... ሄ ዋ ን ‍..........
​​​​​​​​
ክፍል

◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ

ምንም ማስታወስ አልቻልኩም የማስታውሰውም ነገር የለም ምክንያቱም እኔ እንዳላጠፋሁት እርግጠኛ ስለሆንኩ
በዚህ ሀሳብ ላይ ሆኜ ማክ በር አንኳክቶ ገባ ማሬ ምን ሆነሽ ነው ሰላም አይደለሽ አለኝ አዙ የነገረችኝን ቴክስቱን ማን እንዳጠፋው ሳላውቅ ልነግረው አልፈለኩም እ..... ..ደና አይደለሁም ማክ ምን ብዬ እንደምነግርህ አላውቅም የደበቅኩህ ነገር ነበር አልኩ እየተንተባተብኩ ንገሪኝ ምን ደብቀሽኝ ነበር አለ በተጨነቀ አይነት ስሜት እያየኝ ማክዬ እንዳትቆጣኝ አልኩት አልቆጣም ንገሪኝ ምን ተፈጠረ ምንድነው የደበቅሽኝ
ማክ ከየት እንደምጀምርልህ አላውቅም ጥፋት ይሁን መልካም ላንተ ሳልነግርህ ከወራት በፊት የናቴ ጓደኛ ጋር ሄጄ ነገር
ብዬ ቀና ብዬ አየሁት ቀጥይ በሚል አስተያየት ሲመለከተኝ ከናቴ ጓደኛ ጋር እንዳወራንና በማግስቱ በማላውቀው ቁጥር ቴክስት እንደተላከልኝ አሁን ቴክስቱን ላገኘው እንዳልቻልኩም ጭምር ነገርኩት ምንም ባለመገረም ስሜት ነበር የሚያዳምጠኝ ስጨርስ ምን እንደሚለኝ ለመስማት በጉጉት እጠብቀው ጀመር
ሄዊዬ ቆይ ይሄ ነገር ለምን አይቀርብሽም ለምን አዲስ ህይወት "ሀ" ብለን አንጀምርም? በርግጥ የእናትሽ ጓደኛ ጋር እንደሄድሽ አላውቅም ግን ሌላ ተጨማሪ ቴክስት ካንድ አይነት ቁጥር ተልኮልሽ ነበር አንቺ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ነበርሽ በወቅቱ ከፍቼ ሳየው አባቴ አንቺን የሚያገኝበት አጋጣሚ እየፈለገ እንደሆነ ስለተረዳው አጠፋሁት ቁጥርሽን ከየት እንዳመጡ ልጠይቅሽ ነበር ግን የባስ እንዳላስጨንቅሽ ስላሰብኩ ተውኩት
አንቺም ከዛ በኋላ የረሳሽው መስሎኝ ነበር ስላልጠየቅሽ እና አሁን በምን በምን ትዝ አለሽ አለኝ በውስጤ ተመስገን ማክ ከኔ ጋር ነው ምንም አልዋሸኝም አልኩኝ ለደቂቃ ምንም ሳልናገር ቆየሁ በያ ንገሪኝ አለኝ ማክ ምንድን ነበር ሁለተኛው መልዕክት አልኩት "ይሄ የመጨረሻ እድልሽ ነው ያባትሽን ሚስጥር ማወቅ ከፈለግሽ በላክንልሽ አድራሻ ጠዋት 4 ሰዓት ነይ" ነበር የሚለው ይሄን መልዕክ ብታይ ኖሮ በርግጠኝነት ሄደሽ እራስሽን አባቴ መዳፍ ላይ ትጥይ ነበር አለኝ ማክ መሄድ ነበረብኝ ሁኔታው ከምታስበው በላይ አሳሳቢ ነው ዛሬ አዙ ጋር ደውዬ ሚስጥሩን የያዘው ፋይል ሲዲ እንደሆነ ነግራኛለች ይሄ ሲዲ ደግሞ እኔ እጅ ከገባ አባቴን እኔ ራሴ እንደሆንኩ የምበቀለው ሲያወሩ ሰምታለች፡፡ እኔ እዚህ ሲዲ ውስጥ ምን እንዳለ ሳላውቅ እንቅልፍ አይወስደኝም ምንድነው ሚስጥሩ እራሴ ሊፈነዳ ነው እባክህ አግዘኝ የኔ ፍቅር አልኩት ማክ ከተቀመጠበት ተነስቶ አቅፎ ያፅናናኝ ጀመር በቃ መፍትሄ አናጣም ትንሽ ብቻ ታገሺ እራስሽን ለማረጋጋት ሞክሪ ምን ይመስልሻል ትንሽ እንድትረጋጊ ሁኔታዎችንም ተረጋግተን ለማሰብ አንድ ሳምንት ወጣ ብለን ብንመጣ አለኝ ሀሳቡ ጥሩ መስሎ ታየኝ ወዴት እንሂድ አልኩት አሁንም ግራ እንደተጋባሁ ነኝ ዱባይ ደርሰን እንምጣ እስከዛ ነገሮችን በደንብ የምናስብበት ጊዜ ይኖረናል በዛውም ካለንበት ጭንቀት ትንሽ እናርፋለን አለኝ በሀሳቡ ተስማማሁ ከሳምንት በኃላ ዱባይ ሄደን በጣም አሪፍ የሚባል ጊዜ እያሳለፍን ነው ለጊዜውም ቢሆን ሁሉንም ነገር እረስቼዋለሁ ማክ ወደበፊቱ ማንነቴ በመመለሴ በጣም ደስተኛ ሆኗል ድንገት አየሽ አይደል ሁሉንም ነገር ጥለን ወደ አውስትራሊያ ብንሄድ ሁሉን ነገር መርሳት እንደምንችል አለኝ ማክዬ ለጊዜው መርሳት ስለፈለኩና አንተም ማስከፋት ስላልፈለኩ እንጂ እስከመጨረሻው ማንነቴንና ያባቴን የተደበቀ ማንነት እረስቼ መኖር አልችልም
በተለይ ጉዳዩ ከኔ ጋር እንደሚያያዝ ካወቅኩ በኃላ ይበልጥ የማወቅ ፍላጎቴ ጨምሯል ይህን ጉዳይ እልባት ካገኘሁለት በኃላ የፈለክበት እንሄዳለን አልኩት ማክ ይሄን ሲሰማ ሀሳቤን እንደማልቀይር ስላወቀ በቃ እሺ እኔም ይሄ ነገር ሰላም እየነሳኝ ነው ስለዚህ ወደኢትዮጵያ ስንመለስ አብረን መፍትሄ እንፈልጋለን ግን አንድ ነገር ቃል ትገቢልኛለሽ አለኝ ምንድነው ማክ የፈለግከውን አልኩት በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮኝ እንደሆነ ሲነግረኝ በመደሰት
ያባትሽ ሚስጥር ምንም ሆነ ምን ጠንካራ እንደምትሆኚና ምንም ለማድረግ እንደማትሞክሪ እንደዛ ሲለኝ ማክ የሆነ የምታውቀው ነገር እንዳለ ይሰማኛል አልኩት ሄዊዬ እንደዛ ማለቴ አይደለም ግን ያው ከሁኔታዎች አንፃር ጉዳዩ እንደሚከብድ በመጠርጠር ነው ብሎ አቅፎ ሳመኝ ነገሩ ባይዋጥልኝም ከማመን ውጪ አማራጭ አልነበረኝም
የዱባይ ቆይታችንን ጨርሰን እንደተመለስን.......ይቀጥላል


@yederasiyanbet
@yederasiyanbet