Get Mystery Box with random crypto!

Fuad Muna (Fuya)

የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya) F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya)
የሰርጥ አድራሻ: @fuadmu
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.67K
የሰርጥ መግለጫ

የኛ እዉነታ የሌሎችን ስጋ ለብሶ ሲቀርብ!
በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት!
ለአስተያየትዎ
@fuadmubot
ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14
ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-06 17:58:55
ፕሮጀክት 2 እየተገባደደ ነው!
.
ከሀረማያ የደረሱን ምስሎች የፕሮጀክት 2 የኮንክሪት ግንባታ መጠናቀቁን ያሳያሉ።

ለፕሮጀክት 3 የቀረውን ገንዘብ @Fuadmuna ላይ አካውንት በመውሰድ ለጎደለባቸው ሙላትን ለጎደሉባችሁ ሰደቀተል ጃሪያን አስገቡ።

መልካም ኢፍጣር!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
762 views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 11:54:14 ሀምራ አልአሰድ ላይ ...
(ፉአድ ሙና)
.
ቀኑ ለሙስሊሞች ከባድ ነበር። አይደለም ምዕመኑ ውዱ ነብያቸው እንኳን ከጥቃት አልተረፉም። አብላጫው ሶሀባ ሰውነቱ ክፉኛ ቆስሏል።

ጦርነቱ የዕሁድ ጦርነት ነበር። ሙስሊሞች ድልን የተነሱበት ... ውድ ሰሀባዎች የተቀጠፉበት ጦርነት! ሙሽሪኮች በበላይነት መንፈስ የበድርን ጦርነት ቂም መወጣታቸው ቢያስደስታቸውም፤ ድላቸው ግን ሙሉ ጠዓምን አልሰጣቸውም።

«ወዮልን! ሙሀመድን ሳንገድል .... ሴቶቻቸውን ሳንማርክማ ምኑን አሸነፍነው?» ሲሉ ራሳቸውን ለዳግም ጥቃት አደራጁ።

የሙሽሪኮች ጦር እየመጣ የመሆኑ ዜና ከውዱ ነብይ ዘንድ ደረሰ። ባልደረባዎቻቸው በከባዱ የቆሰሉባቸው ነብይ ጆሮዎች ይህን ዱብዳ ሰሙ።

ምን ያሉ ይመስላችኋል?

የቆሰለ ሰራዊታቸውን የሙስሊሞችን አለመዳከም ያሳይና አጋሪዎችን ይመክት ዘንድ ተጣሩ። በዚህ ጥሪ ላይ እንዲሳተፉ የተፈቀደላቸው ደግሞ እነዚያው የዕሁድ ተራራ ላይ ከባድ ስቃይ የደረሰባቸው የእሁድ ዘማቾች! ከደረሰባቸው ጉዳት አንፃር በሰው ተደግፈው የሚሄዱ ሰሀባዎች ጭምር ነበሩ።

አጋሪዎቹን ለማስቆም ስቃያቸውን እያስታመሙ ወደ ሀምራ አል አሰድ ተመሙ። በዚህ ጊዜ ሁኔታው ፍርሀት ያለበሳቸው ሙሽሪኮች በቀጣይ አመት ብንጋጠም ይሻላል ብለው ተመለሱ።

አላህ የእነዚህን ለነብሳቸው የማይሳሱ ሰሀቦች ጉዳይ አስመልክቶ በወህይ እንዲህ ሲል ጀብዷቸውን ተረከው።


الَّذِينَ اسْتَجَابُوا لِلَّهِ وَالرَّسُولِ مِن بَعْدِ مَا أَصَابَهُمُ الْقَرْحُ ۚ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا مِنْهُمْ وَاتَّقَوْا أَجْرٌ عَظِيمٌ

እነዚያ መቁሰል ካገኛቸው በኋላ ለአላህና ለመልክተኛው የታዘዙት ከእነሱ ለነዚያ በጎ ለሠሩትና ለተጠነቀቁት ታላቅ ምንዳ አላቸው፡፡


الَّذِينَ قَالَ لَهُمُ النَّاسُ إِنَّ النَّاسَ قَدْ جَمَعُوا لَكُمْ فَاخْشَوْهُمْ فَزَادَهُمْ إِيمَانًا وَقَالُوا حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ

እነዚያ ሰዎቹ ለእነርሱ፡- «ሰዎች ለእናንተ (ጦርን) አከማችተዋልና ፍሩዋቸው» ይሉዋቸውና (ይህም) እምነትን የጨመረላቸው «በቂያችንም አላህ ነው ምን ያምርም መጠጊያ!» ያሉ ናቸው፡፡


فَانقَلَبُوا بِنِعْمَةٍ مِّنَ اللَّهِ وَفَضْلٍ لَّمْ يَمْسَسْهُمْ سُوءٌ وَاتَّبَعُوا رِضْوَانَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ ذُو فَضْلٍ عَظِيمٍ

ከአላህም በኾነ ጸጋና ችሮታ ክፉ ነገር ያልነካቸው ኾነው ተመለሱ፡፡ የአላህንም ውዴታ ተከተሉ፤ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡
(2/172–174)

ይህም ገድል አላህን በምቾት ውስጥ ብቻ ሳይሆን አይታሰብም በሚባልበት ሁኔታ ውስጥ እንኳን ከልብ የማሳደር ምሳሌ ሆኖ ዘመናትን እየተሻገረ አለ።

አላህ ሁሌም በወደደው መንገድ ላይ ከሚቆሙ፤ እምነታቸውን በንፍቅና እና በክህደት ከማያበላሹ ደጋግ ባሮቹ ዘንድ ያድርገን።
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.2K views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 17:39:59
ለሶስተኛው ፕሮጀክት የቀረውን ገንዘብ ቶሎ አሟልተን ወደ ሰርፕራይዛችን ብንሻገር ምን ይላችኋል?

እናንተ ንፁህ ውሀን መጠጣት ትወዳላችሁ?
እነሱስ?

እና የቻልነውን ያህል በዚህ ውብ ወር እንሰድቅ እና ሶስተኛውን የውሀ ጉድጓድ እናሳካው። የተሰበሰበው ብር ግማሽ ደርሷል።

@Fuadmuna ላይ ጎራ እያላችሁ አካውንት ውሰዱ! ያስገባችሁም ስክሪንሾት (ደረሰኝ) መላክ አይረሳ!

አንድ ላይ እንችላለን!
ኢንሻአላህ!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
94 views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 16:53:14
ብስራት በረመዳን 12
ፕሮጀክት 3 ሊጀመር ነው
.
የጎደሉ አሉ ስንል የጀመርነው የሰደቀተል ጃሪያ ዘመቻ በጅማ ዞን ሶኮሩ ወረዳ ካስገነባነው አንድ የውሀ ጉድጓድ አልፎ በምስሉ ላይ በምትመለከቱት መልኩ በሀረማያ ሁለተኛውን ፕሮጀክት ወደማገባደድ እየተጠጋ ይገኛል።

የፕሮጀክት 2 የቁፋሮ ስራ ተጠናቆ፤ በአላህ ፍቃድ ውሀውም ተገኝቷል። አሁን ላይ የአፈሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ በኮንክሪት የመገንባት ስራ እየተካሄደ ይገኛል።

አልሀምዱሊላህ!

ሶስተኛ ፕሮጀክት ይኖረናል ብለን አስበን የነበረ ባይሆንም ለቀደሙት ፕሮጀክት የተጠየቀ 50 ሺህ ብር ዘግይቶ የደረሰን ስለሆነ የቀረውን ብር ሞልተን የውሀ ጉድጓዳችንን ለጊዜው በዊትሩ ብንቋጨው ብለናል።

ስለሆነም ለፕሮጀክት 3 የቀረውን ገንዘብ በቻላችሁት ፍጥነት @Fuadmuna ላይ አካውንት በመውሰድ እንዲሁም ካስገባችሁ በኋላ ስክሪን ሾት በመላክ ለስኬት እናበቃው ዘንድ እጠይቃችኋለሁ።

በረመዳኑ ለራሳችሁም ለጎደሉባችሁም ለጎደለባቸው የሚሰራ ውብ የሰደቀተል ጃሪያ አሻራ ያኑሩ።

ከረመዳን በኋላ ፊታችንን ወደ ሰርፕራይዙ ስለምናዞር ከወዲሁ ይህን ፕሮጀክት እንቋጨው ዘንድ በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ።

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ረመዳን ሙባረክ!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
@Fuadmu
አካውንት ለመውሰድ
@Fuadmuna
1.1K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 12:28:30
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
12 views09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 12:22:12
አንድ እህት ያለችበትን ተጨባጭ የሚያሳይ ፅሁፍ አጋርቻችሁ ነበር። አድራሻዋን የምትፈልጉ በውስጥ ብዬ የነበረ ቢሆንም በምትፈልጉት ፍጥነት ምላሽ ላልሰጥ ስለምችል እዚህ ላስቀምጥላችሁ። በቅርብ ያላችሁም ጎራ እያላችሁ አብሽር በሏት።

የታማሚ እናቷ ስም ፋጡማ ኢብራሂም የሚኖሩበት ቦታ አየርጤና
ዲያሊሲስ የምታደርገው አይናለም ሆስፒታል (አየርጤና)
CBE አካውንት
Fatuma Ebrahim 1000154046155

«እናቴ የኩላሊት ታማሚ ነች በዲያሊሲስ ነው ያለችው። ሁለት አመት ሆናት ዲያሊሲስ ከጀመረች ። እስከዛሬ ቤት ሽጠን እንዲሁም በደጋግ ሰዎች እርዳታ እዚህ ደርሳለች። ለሷ ብለን ያለንን ሽጠን አዲስ አበባ እያሳከምናት ነው። ወጪው ምን ያህል እንደሚሆን መገመት አይከብድህም ... »

ስትል በቻልነው አቅም እናግዛት ዘንድ ጠይቃለች። እንግዲህ ወሩ ረመዳን ነው። ተሽቀዳዳሚዎች ተሽቀዳደሙ። የአቅማችሁን ሰዳችሁ አለንልሽ አይዞን በሏት።

.
@Fuadmu
@Fuadmu
735 views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 14:08:24
ይህ በውስጥ በኩል የደረሰኝ የእርዳታ ጥያቄ ነው።

«እናቴ የኩላሊት ታማሚ ነች በዲያሊሲስ ነው ያለችው። ሁለት አመት ሆናት ዲያሊሲስ ከጀመረች ። እስከዛሬ ቤት ሽጠን እንዲሁም በደጋግ ሰዎች እርዳታ እዚህ ደርሳለች። ለሷ ብለን ያለንን ሽጠን አዲስ አበባ እያሳከምናት ነው። ወጪው ምን ያህል እንደሚሆን መገመት አይከብድህም ... »

ስትል በቻልነው አቅም እናግዛት ዘንድ ጠይቃለች። እንግዲህ ወሩ ረመዳን ነው። ተሽቀዳዳሚዎች ተሽቀዳደሙ። የአቅማችሁን ሰዳችሁ አለንልሽ አይዞን በሏት።

አድራሻዋን @Fuadmuna ላይ መውሰድ ትችላላችሁ።
.
@Fuadmu
@Fuadmu
1.2K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 17:23:49
ከአፍጥር በፊት ...

የጎደሉ አሉ ፕሮጀክት 2 በሀሮማያ የመጀመሪያ ቀን ቁፋሮ ሲጀመር የሚያሳይ ምስል ተጋብዛችኋል።

ሂደቱን እየተከታተልን እናሳውቃለን።

አንድ ላይ እንችላለን!

መልካም ኢፍጣር መዳረሻ!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.8K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 11:18:09
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.9K views08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 10:40:29
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.1K views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ