Get Mystery Box with random crypto!

Fuad Muna (Fuya)

የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya) F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya)
የሰርጥ አድራሻ: @fuadmu
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.67K
የሰርጥ መግለጫ

የኛ እዉነታ የሌሎችን ስጋ ለብሶ ሲቀርብ!
በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት!
ለአስተያየትዎ
@fuadmubot
ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14
ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-03-22 20:25:31
በረመዳኑ የመጀመሪያው ለይል
ብስራት ልንገራችሁ!
.
የጎደሉ አሉ ብለን የጀመርነው ዘመቻ ፕሮጀክት 1 በጅማ ዞን ሶኮሩ ወረዳ በመስጂድ ግቢ ውስጥ እየተገነባ የነበረው የውሀ ጉድጓድ ግንባታ ተጠናቋል።

እኛም ባሳለፍነው ቅዳሜ በአካል ከአዲስ አበባ በ 220 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሶኮሩ ወረዳ ተጉዘን ፕሮጀክቱን ጎብኝተናል። በቦታው የነበረውን ስሜት እንዲሁም የፕሮጀክቱን ሂደት የሚያሳይ ቪዲዮ ጊዜ ካገኘሁ በቅርቡ ካልሆነም ከረመዳን በኋላ ኤዲት አድርጌ እለቅላችኋለሁ።

ሁለተኛ ብስራት!

የጎደሉ አሉ ፕሮጀክት 2 የቦታ መረጣ ተካሂዶና የመጀመሪያ ክፍያ ፈፅመን ሀሮማያ ላይ የቁፋሮ ስራ ተጀምሯል። አልሀምዱሊላህ!

እንዲሁ የጀመርነው ዘመቻ ፍሬ አፍርቶ በርካታ በውሀ ችግር የሚንገላቱ ሰዎችን ችግር በመቅረፍ ለጎደሉብን ውብ ነፍሶች የሰደቃ ስጦታ ይሆንልን ዘንድ ላገራልን ጌታ እልፍ ምስጋና ይገባው።

ፎቶ:– የጎደሉ አሉ ፕሮጀክት 1 ጅማ ሶኮሩ
.
@Fuadmu
@fuadmu
1.4K views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 13:33:21
ተጣሪ ይጣራል!
(ፉአድ ሙና)
.
እነሆ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ታላቁ እንግዳችን የረመዳን ለይል አንድ ብሎ ይጀምራል። ከዚህ ለሊት ጀምሮ በሁሉም የረመዳን ለሊቶች ላይ ተጣሪ ይጣራል።

በመልካምነት ላይ ጉጉ የሆኑ ነፍሶችን
يا باغي الخير أقبل
«እናንት መልካም ፈላጊዎች ሆይ በመልካምነታችሁ በርቱ!» ሲል ወደ መልካምነት ይጋብዛል።

ወደ ክፋት እና አመፅ የዘነበሉ ነፍሶችን
يا باغي الشر أقصر
«እናንተ የጥፋት እጆች ሆይ ተሰብሰቡ!» ሲል ይገስፃል።

ይህ ጥሪ ረመዳኑን ሙሉ ይመላለሳል። በእርግጥ ጆሮዎች አይሰሙትም። አማኞች ግን በጥሪው መኖር ቅንጣትን አይጠራጠሩም። ምክንያቱም ይህን የተናገሩት لا ينطق عن الهوى ብሎ አላህ ከስሜታቸው እና ከዝንባሌያቸው ሳይሆን ከእርሱ የመጣላቸውን ብቻ እንደሚናገሩ የመሰከረላቸው የአለማቱ ጌጥ የእውነተኞች አይነታ ውዱ ነብያችን (ሰዐወ) ናቸውና!

አላህ ለጥሪው ተግባራዊ ምላሽ ሰጥተው ሁሌም በሚወደው መንገድ ላይ ከሚቆዩ ባሮቹ ያድርገን!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
540 views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 11:05:13
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
843 views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 16:41:25 እንኳን ደስ ያላችሁ!
የጀነት በሮች ሊከፋፈቱ ነው!
.
ጨረቃን የፈጠራት ጌታ ውጪ ካላት .... ለረመዳን የቀሩን 3 የማይሞሉ ሰዓታት ናቸው። ከጥቂት ሰዓታት በኋላ መስፈሪያ ይቀየራል። የኢባዳ ምንዛሬ ጣራ ይነካል። አላህ በዚህ ውብ ንግድ ላይ በእጅጉ ከሚያተርፉት ባሮቹ ያድርገን።

ረመዳን የአዲስ ማንነት መጀመሪያ ልዩ እድል ነው። ከረመዳን በፊት ባለው እኛ እና በረመዳን እኛነታችን መካከል ትልቅ ልዩነት ሊኖር ግድ ይላል። በረመዳን የምንሰበስበው የተቅዋ ስንቅ ቀሪውን አመት በክብር ያቆየን ዘንድ ይከጀላል።

ከዛሬ በኋላ የማስነብባችሁ አጫጭር ጥቅሶች ወደ ቁርዓን አንቀፆች ይቀየራሉ። እናንተም ኮመንት ላይ በእለቱ ካነበባችሁት አንቀፅ ያሻችሁን ኮመንት አድርጉ። ምልልሳችን በቁርዓን ብቻ ቢሆን ይዋባልና!

አላህ ቢሻ ከረመዳን በኋላ ልዩ ስጦታ ይኖረኛል። እንዲሳካልኝ በረመዳን ዱዓችሁ አግዙኝ። ሰው ነኝና ሌሎች ብዙ ሀጃዎችም ስለማይጠፉ በዱዓ አንረሳሳ።

ረመዳናችሁ የተዋበ ይሆን ዘንድ እመኛለሁ።

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.4K views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 11:14:25
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.7K views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 13:46:11
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.2K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 14:41:19
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
528 views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 19:52:05 ወልቂጤ ላይ ቆንጆ ሆቴል ጠቁሙን እስኪ
1.2K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 12:00:22
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.6K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 09:29:35
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
1.3K views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ