Get Mystery Box with random crypto!

Fuad Muna (Fuya)

የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya) F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya)
የሰርጥ አድራሻ: @fuadmu
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.67K
የሰርጥ መግለጫ

የኛ እዉነታ የሌሎችን ስጋ ለብሶ ሲቀርብ!
በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት!
ለአስተያየትዎ
@fuadmubot
ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14
ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-22 14:43:17
ደሴ!!! ደሴ!! ደሴ!!

ደሴ ኦርደር መቀበል ጀምረናል።
.
ደሴ እና አካባቢዋ ያላችሁ አንባቢዎች ከዚህ ሰዓት ጀምሮ መፅሀፉን @ifadasales ላይ ማዘዝ ትችላላችሁ።

ሌሎች ክፍለሀገሮች ላይም በቅርቡ ኦርደር መቀበል እንጀምራለን።

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
2.0K views11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 10:33:57
እንደምን አርፍዳችኋል?
.
ዛሬ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ የፈገግታ መጅሊስ መሰናዷችን በቴሌግራም ቻናሌ ላይ በቀጥታ ይካሄዳል።

በዚህ መሰናዶ የመጀመሪያዎቹን ሶስት ኮፒዎች እናጫርታለን። አሸናፊዎቹ ከእኔ እጅ ሽልማቱን ይወስዳሉ።

የጨረታው ገቢ መፅሀፌን ማንበብ እየፈለጉ ነገር ግን ገንዘብ ለሌላቸው የቻናሌን አንባቢዎች ነፃ ኮፒዎችን መሸለሚያ ይሆናል።

ከህትመት ውድነት አንፃር የመፅሀፉ ዋጋ ከፍ ማለቱ ተማሪ የሆኑ አንባቢዎቼ መፅሀፉን እንዳያገኙ እንዲያደርጋቸው አልሻም።

ዛሬ ምሽቱን ስለኢፋዳ እያወጋን የመጀመሪያ ኮፒዎችን አጫርተን ገቢውን ነፃ መፅሀፍ የመግዛት አቅም ለሌላቸው መሸለሚያ እናደርጋለን።

ኢንሻአላህ!

ከምሽቱ 3:00 ላይ እንገናኝ!

አዲስአበባ ያላችሁ እና ክፍለሀገር ሆናችሁ አዲስ አበባ የሚቀበልላችሁ ያለ ሳያልቅባችሁ @Ifadasales ላይ መፅሀፉን እየገዛችሁ ስንተኛ እንደሆናችሁ የሚገልፅ ቁጥር ተቀበሉ።

ማታ ፈገግታ መጅሊስ ላይ እንገናኝ!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmu
2.1K viewsedited  07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 21:30:20 ማስታወሻ
.
ለጊዜው የመፅሀፉን ኦርደር እየተቀበልን ያለነው አዲስ አበባ ላይ ብቻ ነው። ከፍተኛ ፍላጎት ያለባቸው ከተማዎችን ኦርደር በቅርቡ መቀበል እንጀምራለን። ዝግጅታችንን ስንጨርስ በሰዓቱ እናሳውቃለን።

አዲስ አበባ ያላችሁ አሊያም የሚቀበልላችሁ ያለ የመጀመሪያው እትም ሳያልቅ @ifadasales ላይ ኦርደር አድርጉ።

ኦርደሩን ተቀብለን እንደጨረስን ከ May 1 ጀምሮ በአማካይ ቦታዎች በሚገኙ pick up locations መፅሀፉን ለእናንተ ማድረስ እንጀምራለን።

ኢድ ሙባረክ!
.
@Fuadmu
@Fuadmu

ኢድ ሙባረክ!
2.4K views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 19:40:53 ግልፅ ለማድረግ ያህል

ኢፋዳ መፅሀፍ ነው። የታተመ በወረቀት የሚነበብ
በቴሌግራም @ifadasales ላይ ሂዱ የምንለው መፅሀፉን ለማዘዝ ነው።

@ifadasales ላይ ሄዳችሁ ኢፋዳ ብላችሁ ስትፅፉ መመሪያዎች ይላኩላችኋል።

ከወዲሁ የእርሶን ኮፒ ይዘዙ።

ስንተኛው ገዢ መሆንዎን የሚገልፅ ቁጥር እንልክልዎታለን።

እናመሰግናለን!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
2.5K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 16:54:46
ኢፋዳ በሽያጭ ላይ!
.
ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ መፅሀፉን @Ifadasales ላይ መግዛት ትችላላችሁ።

መፅሀፉን @Ifadasales ላይ የሚሰጣችሁን መመሪያ በመከተል ስትገዙ ስንተኛ ገዢ እንደሆናችሁ የሚገልፅ ቁጥር ይደርሳችኋል።

ኮፒዎቹ ሳይልቁ ቀድማችሁ ኦርደር አድርጉ።

Price 500ETB
.
@Fuadmu
@Fuadmu
2.5K viewsedited  13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 13:59:40
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
2.7K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 13:59:16 የኢድ ስጦታዬ .... ኢፋዳ!
(ፉአድ ሙና)
.
ሰባት አመታት ገደማ በሶሻል ሚዲያ በቻልኩት አቅም በልብወለድ እና ግጥም ስራዎች እኛን የሚመስሉ እና ለእኛ የቀረቡ ውክልናዎችን ለመሳል ሞክሬያለሁ። በአላህ ችሮታም ካሰብኩት በተሻለ መልኩ ስራዎቼን የሚረዳ አንባቢን ታድያለሁ።

አንባቢዎቼ ለእኔ ቁጥር አይደሉም። የተለያየ የእውቀት ደረጃ እና ማንነት ያላቸው ሰዎች ናቸው። በእነዚህ አመታት ውስጥ ተቆራኝተን ቤተሰብ ሆነናል። ፅሁፌን ከማንበብ ባሻገር በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎች ሲኖሩ የሚሳተፉ እና እምነት የሚጥሉ ውብ ቤተሰቦችን አፍርቻለሁ። አልሀምዱሊላህ!

ስፅፍላችሁ የምፅፈው ከእኔ በተሻለ መረዳት እንደምትገነዘቡት እያሰብኩ ነው። እናም ለተወሰነ ጊዜ ከሀገር ውጪ የነበርኩኝ በመሆኑ ምክንያት እንዲሁም ከዚያም ቀደም በአንዳንድ ምክንያቶች ለረዥም ጊዜ ልብወለድ ሳላስነብብ ቆይቻለሁ።

እነሆ አሁን በአላህ ፈቃድ በአጭርም ሳይሆን በረዥም ልብወለድ መጥቻለሁ። አንባቢዎቼ ሁሌም ስትወተውቱት የነበረው ምኞታችሁ ሰምሮ መፅሀፍ አሳትሜያለሁ። «ኧረ ተው መፅሀፍ አሳትም!» ያላችሁት እውን ሆኗል።

ኢፋዳ ብዙ ምኞቶቼን የከተብኩባት የምናብ ጉዞ ናት። ክብራችሁን እንዲመጥን እና በሙስሊምነት ልዕልናችሁ ልክ እንዲሰፋ ሞክሬያለሁ። አላህ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ እኔ ካሰብኩት በተሻለ እና እኔ ካየሁበት በበለጠ መረዳት ይገጥማችሁ ዘንድ ዱዓዬ ነው።

በዚህ የህትመት ዋጋ እጅጉን በተወደደበት እና ታዋቂ ደራሲዎች እንኳን ማሳተም በፈሩበት ሰዓት መፅሀፉ እንዲታተም የሆነው ከዚህ በላይ ኢፋዳን ሳያሳትሙ መቆየት ከእናንተ መዘግየት ይሆናል በሚል እሳቤ ነው።

መፅሀፉ ሌሎች ኢስላማዊ ቅብ ያላቸው መፅሀፍት ላይ ባልተለመደ መልኩ እጅጉን ጥንቅቅ ያለ የውስጥ ዲዛይን እንዲሰራለት ተደርጓል። ለሌሎች መፅሀፍት ማሳያ ይሆናል ብዬ በአላህ ተስፋ አደርጋለሁ።

እነሆ የኢድ ስጦታዬ ኢፋዳ የተሰኘ የረዥም ልብወለድ መፅሀፍ ነው።

ፍትሀዊ ለመሆን ሲባል ከ4ኛው ኮፒ ጀምሮ ያሉትን መፅሀፍቶች ዛሬ ከ11 ሰዓት ጀምሮ @Ifadasales ላይ በሞባይል ባንኪንግ/በባንክ በመላክ በመግዛት የእናንተን ኮፒ ማስያዝ ትችላላችሁ። ስንተኛው ገዢ እንደሆናችሁ የሚገልፅ ቁጥር ይሰጣችኋል። አላህ ቢሻ የመፅሀፉን የኦንላየን ሽያጭ በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ አጠናቀን በምትሰጡን መረጃ መሰረት በቅርቡ በአቅራቢያችሁ ካለ የኢፋዳ Pick up ሎኬሽን መፅሀፉን እንድትወስዱ እናደርጋለን።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉት ኮፒዎች ግን ነገ ማታ በቴሌግራም የፈገግታ መጅሊስ ላይ ለጨረታ ይቀርባሉ። ለአሸናፊዎች መፅሀፉን እኔ ራሴ አስረክባለሁ።

መፅሀፉን @ifadasales ላይ ስትገዙ የሚላክላችሁን መመሪያ በአግባቡ ተከተሉ። ከዚህ ቀደም ለበጎአድራጎት በምትልኩበት አካውንት ክፍያ አትፈፅሙ። @Ifadasales ላይ የሚሰጣችሁን አካውንት ተጠቀሙ።

የመጀመሪያውን እትም ኮፒዎች ሳያልቁ ቀድማችሁ ግዙ።
.
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
2.5K viewsedited  10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 11:18:30 8 ሰዓት ላይ ስጦታው ይከፈታል።

ሁላችሁም ተገኙ። ለጓደኞቻችሁም አጋሩ።

#አዲያናትግንአዱናት
#ኢፋዳ
.
@Fuadmu
@Fuadmu
425 views08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 10:30:46 የሰፕራይዙ ምንነት ስንት ሰዓት ላይ ይገለጥ?
.
@Fuadmu
@Fuadmu
595 views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:11:18
الله أكبر الله أكبر الله أكبر، لا إله إلا الله، الله أكبر الله أكبر، ولله الحمد، الله أكبر كبيرًا، والحمد لله كثيرًا، وسبحان الله بكرةً وأصيلًا، لا إله إلا الله وحدهُ، صدق وعدهُ ونصر عبدهُ وأعز جندهُ وهزم الأحزاب وحدهُ، لا إله إلا الله ولا نعبدُ إلا إياهُ، مُخلصين له الدين ولو كره الكافرون، اللهم صلِ على سيدنا محمدٍ، وعلى آل سيدنا محمدٍ، وعلى أصحاب سيدنا محمدٍ، وعلى أنصار سيدنا محمدٍ، وعلى أزواج سيدنا محمدٍ، وعلى ذرية سيدنا محمدٍ، وسلم تسليمًا كثيرًا
.
@Fuadmu
@Fuadmu
1.9K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ