Get Mystery Box with random crypto!

Fuad Muna (Fuya)

የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya) F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadmu — Fuad Muna (Fuya)
የሰርጥ አድራሻ: @fuadmu
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.67K
የሰርጥ መግለጫ

የኛ እዉነታ የሌሎችን ስጋ ለብሶ ሲቀርብ!
በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት!
ለአስተያየትዎ
@fuadmubot
ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14
ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-29 10:13:01
የአያመተሽሪቅ ቅናሽ!!!


አያመተሽሪቅ ተጀምሯል። እኛም ከኢፋዳ የመሸጫ ዋጋ ላይ 20% ቅናሽ አድርገናል።

ለዚያራ የምትወዷቸው ቤት ጎራ ስትሉ ኢፋዳን ስጦታ እየያዛችሁ ሂዱ።

ለራሳችሁ ያልገዛችሁም የአያመተሽሪቅ ቅናሽ ተጠቃሚ ሁኑ።

አያመተሽሪቅ እስኪያልቅ ድረስ ቅናሹ ይቀጥላል።

@ifadasales ላይ ሞባይል ባንኪንግ ላላችሁ። ሞባይል ባንኪንግ የሌላችሁ ደግሞ በፒካፕ ሎኬሽኖቻችን በመሄድ በካሽ ግዙ።
.
@ifadasales
@ifadasalss
@Fuadmu
3.8K viewsedited  07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 21:12:36
ውቡ የአረፋ ቀን ተጠናቀቀ። አላህ ለባሮቹ መደሰቻ ከሰየማቸው ኢዶች አንዱ .... ኢድ አል አድሀ ተጀምሯል።

አላህ ያጎደልነውን ይሙላ፤ ያጠፋነውን ይማር።

እጅጉን ለምወዳችሁ ቤተሰቦቼ የተዋበ ኢድን እመኛለሁ።

ኢድ ሙባረክ!

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
@Fuadmu
3.7K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 11:36:45
ቀኑ አረፋ ነው። ባለጉዳይ ሁሉ ወደ ጌታው ይማፀናል። ጌታችሁን ተማፀኑት። ይህን ሚስኪን ወንድማችሁንም በዱዓችሁ አትዘንጉት።
.
@Fuadmu
@Fuadmu
3.7K views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 21:00:20 እሷ
(ፉአድ ሙና)
.
ይፈሳል እንባዋ ፣ ትማፀነዋለች ሀዘን ተቀልፃ፣
"ወዴት ነው ‘ምትሄደው?" ትጠይቀዋለች ድንጋጤ ለብሳ።
አይመልስም እርሱ ፣ የያዘው ይዞታል ፣ ቃል አይወጣም ከአፉ፣
"ለማን ነው ‘ምትተወን?" አታውራ ቢለው ነው ለመልስ መስነፉ።
በአስፈሪ በረሀ ፣ ጡት ያልጣለን ህፃን የሚያስተው ጭካኔ፣
ታሰላስላለች ፣ ከየት አመጣ ወኔ?
"አላህ ነው ያዘዘህ?" አይኖቿ ዋተቱ ምላሹን ፍለጋ፣
"አዎ" ሲል መለሰ ፣ ልቧ ተረጋጋ!
"እርሱማ ከሆነ ጥሎ አይጥለንም!" ስትል ተናገረች በኢማን ተውባ፣
የአላህ እርዳታ እንደሚደርስላት በፅኑ አስባ።
.
ትቷቸው ሲመለስ
ልቡን ሊያረጋጋ ፣ ጌታውን ለመነ እጆቹን ዘርግቶ፣
በልጁ ስቅይት ፣ በሚስቱ ተማፅኖ አንጀቱ ተበልቶ።
"ጌታችን ሆይ!
ከቤትህ አቅራቢያ ፣ አንተን ይገዙ ዘንድ፣
አዝመራ ከሌለው ፣ ከሸለቆው ንዳድ፣
ትዕዛዝህን ብዬ ፣ ዘሮቼን አስቀመጥኩ፣
ፍላጎቴን ገደብኩ ፣ መሻትህን ፈፀምኩ።
ጌታችን ሆይ!
የሰዎችህን ልብ ፣ አስናፍቅ ወደነርሱ፣
ከፍሬህ ስጣቸው ፣ ያመስግኑህ ለሱ።
ጌታችን ሆይ!
ድብቁን ታውቃለህ ፣ የምንሰውረውን፣
ተለየሁ ከእነርሱ ፣ ጌታዬ አደራህን!"
.
ከሄደ በኋላ
ስንቋም ተራገፈ ፣ ውሀም ለአመል ጠፋ፣
ጥሙ ጠበሳቸው ፣ ረሀቡም ከፋ።
ስትሮጥ ከጋራው ላይ ፣ ሶፋና መርዋን ስትመላለሰው፣
ቃሏን አሟላላት ፣ ቃሉን የማይጥሰው።
በመልዓኩ ክንፍ ፣ ሲቆፈር አፈሩ፣
"ዙሚ ዙሚ" አሰኛት ፣ ቀናላት ነገሩ።
"ጥሎ አይጥለንም!" ተወዶ እምነቷ፣
ለዓለም ፈውስ ሆነ ፣ ሀጀር ትሩፋቷ።
.
@Fuadmu
@Fuadmu
4.1K views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 11:39:39
ነገሌ ቦረና፤ ነገሌ ቦረና!!!
.

ኢፋዳ ነገሌ ቦረና ገብታለች።
ነገሌ ቦረና ያላችሁ ኢፋዳን መግዛት የምትፈልጉ ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ @ifadasales ላይ ገዝታችሁ ወዲያው ተረከቡ።

በካሽ መግዛት ለምትፈልጉ መፅሀፉ ትልቁ መስጂድ(ኑር መስጂድ) ኢብራሂም ሞባይል አክሰሰሪ የሱቅ ቁጥር 2 ይገኛል።

ለተጨማሪ መረጃ
0979657992
.
@Fuadmu
@Fuadmu
3.9K views08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-21 21:11:47
የጎደሉ አሉ ፕሮጀክት 3 ተመርቋል!!!!
.
ከግንቦት ወር ጀምሮ በሀረማያ ገጠራማው አካባቢ በመገንባት ላይ የነበረው የውሀ ጉድጓዳችን በዚህ መልኩ በስኬት ተጠናቋል።

እኛም ከአዲስ አበባ ተምዘግዝገን በድሬ በኩል ሀረማያ ዘልቀን ዱዓውን ተቀብለን፤ አይነል የቂን አስረግጠን ተመልሰናል። ፕሮጀክቱንም አስመርቀናል።

ለአንድ አይበቃም ያልነውን ለሶስት ያደረሰው ጌታ የተመሰገነ ይሁን።

አንድ ላይ በአላህ ፈቃድ ችለናል። አንድም ሳይሆን ሶስት የጉድጓድ ውሀ አስመርቀናል። አልሀምዱሊላህ።

እንኳን ደስ አላችሁ! ብያለሁ።

.
@Fuadmu
@Fuadmu
5.7K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 12:19:04
ኢፋዳ እየተነበበች ነው። አንባቢዎችም ፎቶዎችን እያጋሩን ነው። እርስዎም ፎቶዎን @Fuadmuna ላይ ያጋሩን!

ያልገዛችሁ ኮመንት ላይ የት እንደሚገኝ መረጃ ታገኛላችሁ። @ifadasales ላይ ብትገዙ ይመረጣል።
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot
825 views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 14:46:20
ሳዑዲ የምትኖሩ የእኔ አንባቢዎች ሳዑዲ የገባው የተወሰነ መፅሀፍ ሳያልቅ ግዙ! ካለቀ በኋላ አልሰማሁም ነበር አይሰራም።
.
@Fuadmu
1.8K views11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 08:57:52
ኢፋዳ እየተነበበች ነው። አንባቢዎችም ፎቶዎችን እያጋሩን ነው። እርስዎም ፎቶዎን @Fuadmuna ላይ ያጋሩን!

ያልገዛችሁ ኮመንት ላይ የት እንደሚገኝ መረጃ ታገኛላችሁ። @ifadasales ላይ ብትገዙ ይመረጣል።
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmu
2.0K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:53:14
አንድ እህታችን በየጎደሉ አሉ ፕሮጀክት ለሶስተኛው የውሀ ጉድጓድ 10 ሺህ ብር አስገብታለች። አላህ ይቀበላት። ምንዳዋን ያብዛው።

የውሀ ጉድጓድ የዚህ ምዕራፍ የመጨረሻ ፕሮጀክታችንን ለመሳካት የቀረውን እጅጉን የተወሰነ ብር @Fuadmuna ላይ አካውንት በመውሰድ አሟሉ። ተሽቀዳዳሚዎች ተሽቀዳደሙ!!

አንድ ላይ በአላህ ፈቃድ ችለናል።
አሁንም እንችላለን!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
2.1K views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ