Get Mystery Box with random crypto!

እሷ (ፉአድ ሙና) . ይፈሳል እንባዋ ፣ ትማፀነዋለች ሀዘን ተቀልፃ፣ 'ወዴት ነው ‘ምትሄደው?' ት | Fuad Muna (Fuya)

እሷ
(ፉአድ ሙና)
.
ይፈሳል እንባዋ ፣ ትማፀነዋለች ሀዘን ተቀልፃ፣
"ወዴት ነው ‘ምትሄደው?" ትጠይቀዋለች ድንጋጤ ለብሳ።
አይመልስም እርሱ ፣ የያዘው ይዞታል ፣ ቃል አይወጣም ከአፉ፣
"ለማን ነው ‘ምትተወን?" አታውራ ቢለው ነው ለመልስ መስነፉ።
በአስፈሪ በረሀ ፣ ጡት ያልጣለን ህፃን የሚያስተው ጭካኔ፣
ታሰላስላለች ፣ ከየት አመጣ ወኔ?
"አላህ ነው ያዘዘህ?" አይኖቿ ዋተቱ ምላሹን ፍለጋ፣
"አዎ" ሲል መለሰ ፣ ልቧ ተረጋጋ!
"እርሱማ ከሆነ ጥሎ አይጥለንም!" ስትል ተናገረች በኢማን ተውባ፣
የአላህ እርዳታ እንደሚደርስላት በፅኑ አስባ።
.
ትቷቸው ሲመለስ
ልቡን ሊያረጋጋ ፣ ጌታውን ለመነ እጆቹን ዘርግቶ፣
በልጁ ስቅይት ፣ በሚስቱ ተማፅኖ አንጀቱ ተበልቶ።
"ጌታችን ሆይ!
ከቤትህ አቅራቢያ ፣ አንተን ይገዙ ዘንድ፣
አዝመራ ከሌለው ፣ ከሸለቆው ንዳድ፣
ትዕዛዝህን ብዬ ፣ ዘሮቼን አስቀመጥኩ፣
ፍላጎቴን ገደብኩ ፣ መሻትህን ፈፀምኩ።
ጌታችን ሆይ!
የሰዎችህን ልብ ፣ አስናፍቅ ወደነርሱ፣
ከፍሬህ ስጣቸው ፣ ያመስግኑህ ለሱ።
ጌታችን ሆይ!
ድብቁን ታውቃለህ ፣ የምንሰውረውን፣
ተለየሁ ከእነርሱ ፣ ጌታዬ አደራህን!"
.
ከሄደ በኋላ
ስንቋም ተራገፈ ፣ ውሀም ለአመል ጠፋ፣
ጥሙ ጠበሳቸው ፣ ረሀቡም ከፋ።
ስትሮጥ ከጋራው ላይ ፣ ሶፋና መርዋን ስትመላለሰው፣
ቃሏን አሟላላት ፣ ቃሉን የማይጥሰው።
በመልዓኩ ክንፍ ፣ ሲቆፈር አፈሩ፣
"ዙሚ ዙሚ" አሰኛት ፣ ቀናላት ነገሩ።
"ጥሎ አይጥለንም!" ተወዶ እምነቷ፣
ለዓለም ፈውስ ሆነ ፣ ሀጀር ትሩፋቷ።
.
@Fuadmu
@Fuadmu