Get Mystery Box with random crypto!

ብስራት በረመዳን 12 ፕሮጀክት 3 ሊጀመር ነው . የጎደሉ አሉ ስንል የጀመርነው የሰደቀተል ጃሪያ | Fuad Muna (Fuya)

ብስራት በረመዳን 12
ፕሮጀክት 3 ሊጀመር ነው
.
የጎደሉ አሉ ስንል የጀመርነው የሰደቀተል ጃሪያ ዘመቻ በጅማ ዞን ሶኮሩ ወረዳ ካስገነባነው አንድ የውሀ ጉድጓድ አልፎ በምስሉ ላይ በምትመለከቱት መልኩ በሀረማያ ሁለተኛውን ፕሮጀክት ወደማገባደድ እየተጠጋ ይገኛል።

የፕሮጀክት 2 የቁፋሮ ስራ ተጠናቆ፤ በአላህ ፍቃድ ውሀውም ተገኝቷል። አሁን ላይ የአፈሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ በኮንክሪት የመገንባት ስራ እየተካሄደ ይገኛል።

አልሀምዱሊላህ!

ሶስተኛ ፕሮጀክት ይኖረናል ብለን አስበን የነበረ ባይሆንም ለቀደሙት ፕሮጀክት የተጠየቀ 50 ሺህ ብር ዘግይቶ የደረሰን ስለሆነ የቀረውን ብር ሞልተን የውሀ ጉድጓዳችንን ለጊዜው በዊትሩ ብንቋጨው ብለናል።

ስለሆነም ለፕሮጀክት 3 የቀረውን ገንዘብ በቻላችሁት ፍጥነት @Fuadmuna ላይ አካውንት በመውሰድ እንዲሁም ካስገባችሁ በኋላ ስክሪን ሾት በመላክ ለስኬት እናበቃው ዘንድ እጠይቃችኋለሁ።

በረመዳኑ ለራሳችሁም ለጎደሉባችሁም ለጎደለባቸው የሚሰራ ውብ የሰደቀተል ጃሪያ አሻራ ያኑሩ።

ከረመዳን በኋላ ፊታችንን ወደ ሰርፕራይዙ ስለምናዞር ከወዲሁ ይህን ፕሮጀክት እንቋጨው ዘንድ በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ።

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ረመዳን ሙባረክ!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
@Fuadmu
አካውንት ለመውሰድ
@Fuadmuna